Get Mystery Box with random crypto!

በሲዳማ ክልል ባለፉት አምስት ወራት 82 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው አልፏል በዘንድሮዉ በጀ | TIKVAH-MAGAZINE

በሲዳማ ክልል ባለፉት አምስት ወራት 82 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው አልፏል

በዘንድሮዉ በጀት ዓመት አስከ ታህሳስ አጋማሽ ባለዉ ጊዜ በሲዳማ ክልል በተለያዩ ቦታዎች 132 የትራፊክ አደጋዎች ተከስተዋል። በአደጋውም 82 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፤ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረትም ሲወድም 91 ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋዉ ካለፈዉ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ እንዳለዉ ተገልጿል፤ አብዛኛዉ አደጋ የተከሰተዉ ከሀዋሳ ወደ ዲላ በሚወስደዉ አስፋልት መንገድ ላይ ሲሆን በተለይ በአለታ ጩኮ ከተማና አካባቢዉ ላይ በርካታ ጉዳት መድረሱና ንብረት መውደሙ እንዲሁም በአንድ ቀን ብቻ በአከባቢው 12 ሰዎች በአደጋዉ መሞታቸው ተገልጿል፡፡

በርካታ የትራፊክ አደጋዎች እየተከሰቱ ያሉት ባለሁለት ጎማ ሞተር ሲሆን፣ እስከ አምስት የሚደረርስ ትርፍ ሰዉ በመጫንና ከተፈቀደዉ ፍጥነት በላይ በማሽከርከር መሆኑ የተነገረ ሲሆን የአሽከርካሪዎች ብቃት ማነስ፣ ሀሰተኛ መንጃ ፈቃድ፣ ጠጥቶና ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር፣ አልፎ አልፎ የመንገድ መበላሸትና ሌሎችም ለአደጋዉ መንስኤ ምክንያት ናቸው ተብሏል፡፡

የገጠሩ ማህበረሰብ በአብዛኛዉ ለትራንስፖርት የሚጠቀመዉ ባለ ሁለት ጎማ ሞተር እንደመሆኑ መጠን አደጋዉን ለመቆጣጠር አመቺ አለመሆኑንና መፍትሄ ካልተበጀለት አደጋዉ እየጨመረ እንደሚሄድ ተጠቁሟል።

Credit: - EPA

@tikvahethmagazine