Get Mystery Box with random crypto!

#አማራባንክ አማራ ባንክ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 8.8 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ማግኘቱን እና | TIKVAH-MAGAZINE

#አማራባንክ

አማራ ባንክ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 8.8 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ማግኘቱን እና ከግብር በፊት 237 ሚሊዮን ብር ማትረፉ ተነግሯል።

የባንኩ የሃብት መጠን 7.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል።በተጨማሪም የተከፈለ የካፒታል መጠን 4.8 ቢሊዮን መሆኑ ተመላክቷል።

አማራ ባንክ አንድ መቶ አርባ አንድ ሺህ የሚሆኑ ባለአክስዮኖች እንዳሉት እና የባንኩ የደንበኞች ቁጥር በአሁን ሰዓት ከአምስት መቶ አምስት ሺህ በላይ ደንበኞች መድረሱ ተገልጿል።

ባንኩ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ከ201 በላይ ያሳደገ መሆኑ የተለጸ ሲሆን በተጨማሪም ባንኩ አዳዲስ ቅርንጫፎችን ለመክፈት ማቀዱንና ያሉትን 8 የኤቲኤም ማሽኖች ቁጥር ወደ 125 ለማሳደግ የማሽን ግዢ መፈጸሙ ተነግሯል።

አማራ ባንክ ከ6.5 ቢሊየን ብር በላይ የተፈረመ ፣ 4.8 ቢሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል እንዲሁም ከ170ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ይዞ በሰኔ 2014 ወደ ስራ የገባ ባንክ ነዉ፡፡

ይህ የተነገረው የባንኩ ባለ አክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ እና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ነው

@tikvahethmagazine