Get Mystery Box with random crypto!

'እስራኤል ዳንሣ ነኝ' በማለት በሀይማኖት ሽፋን የማታለል ወንጀል የፈፀመዉን ግለሰብ . . . በ | TIKVAH-MAGAZINE

"እስራኤል ዳንሣ ነኝ" በማለት በሀይማኖት ሽፋን የማታለል ወንጀል የፈፀመዉን ግለሰብ . . .

በቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ በሚዛን አማን ከተማ አዲስ ከተማ ቀበሌ ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ግለሰቡ የግል ተበዳይ ማንነት በማጥናትና ስልክ በመደወል "እኔ እስራኤል ዳንሣ ነኝ" በማለት ራሱን የፀሎት ሰው በማስመሰል ልጅህ በቅርብ ቀን ወደ ካናዳ ሀገር እንድትሄድ ፀሎት አድርጊያለው የሚልና የመሳሰሉ ሃሣቦችን ይሰጣል።

ከዚያም የተጀመረውን ህንፃ ግንባታ ለማጠናቀቅ የገንዘብ ድጋፍ አደርጉልኝ በማለት ከግል ተበዳይ በመጀመሪያ ዙር 30 ሺህ ብር በባንክ አካውንት ቁጥሩ ይገባለታል፡፡

ከሌሎች አራት ሰዎችመ ማንነታቸውንና የስራ ቦታቸውን ጥናት በማድረግ መሰል ተግባር በማከናወን 109 ሺህ 500 ብር የማታለል ወንጀል ሲፈጽም ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

@tikvahethmagazine