Get Mystery Box with random crypto!

በከባድ ዝናብ ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ በጎፋ ዞን በቶ ከተማ አስተዳደር ትናን | TIKVAH-MAGAZINE

በከባድ ዝናብ ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

በጎፋ ዞን በቶ ከተማ አስተዳደር ትናንት አመሻሹን የጣለው ከባድ ዝናብ በ3ቱም ቀጠናዎች በመኖሪያ ቤት ፣ በንብረት እና በሰብል ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱ ተገልጿል።

ጉዳቱ በባላ ቀጠና እና መሀል ከተማ አጠቃላይ በ 95 ቤቶች እና ቤተሰብ ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 19ኙ ሙሉ በሙሉ መኖሪያ ቤታቸው ላይ በደረሰው ጉዳት ተፈናቅለዋል ሲል የዞኑ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ገልጿል።

ጉዳት የደረሰባቸው አንድ ህፃን እና አንድ አዛውንት በህክምና ማዕከል እየተረዱ መሆኑንና ዝናቡ በእንስሳትም ላይ ጉዳት ማስከተሉንና የአካባቢው ህብረተሰብ እና የከተማዋ አመራሮች በቅንጅት የደረሰውን ጉዳት ማጣራት ላይ መሆናቸውን ከዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tikvahethmagazine