Get Mystery Box with random crypto!

ባለፉት 3 ዓመታት ከአንድ ሺህ በላይ አርሶ አደሮች የቡና ላኪነት ፈቃድ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ቡ | TIKVAH-MAGAZINE

ባለፉት 3 ዓመታት ከአንድ ሺህ በላይ አርሶ አደሮች የቡና ላኪነት ፈቃድ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የቡና ላኪነት ፈቃድ ከወሰዱት አርሶ አደሮች መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑ ቡናቸውን በቀጥታ ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል፡፡

ባለፈው በጀት ዓመት 302 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ በመላክ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን በዘንድሮ በጀት ዓመት 360 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ዕቅድ መያዙ ተበግሯል።

ባለስልጣኑ የዓለም የቡና ገበያ ተለዋዋጭነትን መሰረት በማድረግ ተጨማሪ የገበያ መዳረሻዎችን የማፈላለጉን ስራ በትኩረት እያከናወነ መሆኑን እንደ ኤዥያ ባሉ አካባቢዎች አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎችን ለማስፋት እንቅስቃሴ መጀመሩን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

@tikvahethmagazine