Get Mystery Box with random crypto!

' ሌሎችም ትምህርት ይሆናል ' በአዲስ አበባ ሳሪስ ፤ ከካዲስኮ ህንፃ ጀርባ ፍሬህይወት ሁለተኛ | TIKVAH-MAGAZINE

" ሌሎችም ትምህርት ይሆናል "

በአዲስ አበባ ሳሪስ ፤ ከካዲስኮ ህንፃ ጀርባ ፍሬህይወት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተሰጣቸውን ፈጣን ምላሽ አድንቀው ሁሉም በመስኩ ህዝቡን በተመሳሳይ መልኩ እንዲያስተናግድ ጠይቀዋል።

አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል እንደገለፁት በአካባቢያቸው ሊወድቁ የተቃረቡ 3 የኤሌክትሪክ ፖሎች ስለመኖራቸው ለደቡብ ሪጅን ዞን 6 ሱፐርቫይዘር አቶ ታደሰ ጥላሁን ያመለክታሉ። ወዲያውም በሌላ እንዲተኩ ከተቋሙ ምላሽ ማግኘታቸውን ገልፀዋል።

ይህ ፈጣን ውሳኔ ባይወሰን በንብረት እና በሰው ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ እንደነበር አክለዋል።

ሱፐርቫይዙር እና የመሩት ቡድን በስራቸው መመስገናቸውን የገለፁት እኚሁ የቤተሰባችን አባል ለረጅም ጊዜ ከተቋሙ እንዲህ አይነት ፈጣን ምላሽ አገኝተው እንደማያውቁ ገልፀዋል።

ይህ ለሌሎችም ህዝብን ለማገልገል የተቋቋሙ ተቋማት መማሪያ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

@tikvahethmagazine