Get Mystery Box with random crypto!

ሰሞኑን የሚስተዋለው ቅዝቃዜ እስከ ጥር መጨረሻ ሊቀጥል እንደሚችል ተጠቆመ። አዲስ አበባን ጨምሮ | TIKVAH-MAGAZINE

ሰሞኑን የሚስተዋለው ቅዝቃዜ እስከ ጥር መጨረሻ ሊቀጥል እንደሚችል ተጠቆመ።

አዲስ አበባን ጨምሮ በአንዳንድ ከፍተኛ የአገሪቱ ሥፍራዎች የሚስተዋለው ቅዝቃዜ እስከ ጥር መጨረሻ ሊቀጥል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ቅዝቃዜው ከባህር ጠለል በላይ ከ2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በላይ ከፍታ ያላቸው ሥፍራዎች ላይ የሚስተዋል መሆኑን የኢንስቲትዩቱ የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ የምርምር ክፍል ዴስክ ኃላፊ ሙሉዓለም አበራ ገልጸዋል።

በእነዚህ ሥፍራዎች የሌሊትና ማለዳ እንዲሁም የምሽት ቅዝቃዜ የተስተዋለባቸው ሲሆን ለቅዝቃዜው ዋነኛ መነሻው ከምስራቅ አውሮፓ ተነስቶ የአረቡን መሬት አቋርጦ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው  ቀዝቃዛና ደረቅ አየር መሆኑን ተናግረዋል።

ይህም ቅዝቃዜ ለቀጣይ አንድ ወራት በመካከለኛው፣ በምስራቅና በደቡብ የአገሪቱ ከፍተኛ ሥፍራዎች  ላይ እንደሚቀጥልና የመጠናከር ባህሪ ሊኖረው እንደሚችልም የአየር ትንበያ ጠቅሰው አስረድተዋል። (ENA)

@tikvahethmagazine