Get Mystery Box with random crypto!

በደብረ ብርሃን ከተማ አንዲት እናት 4 ህጻናትን በሰላም ተገላገለች በደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪና | TIKVAH-MAGAZINE

በደብረ ብርሃን ከተማ አንዲት እናት 4 ህጻናትን በሰላም ተገላገለች

በደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪና የጤና ባለሙያ የሆነችው አፀደ ገብረሃና በደብረ ብርሃን በደብረ ብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተደረገላት የቀዶ ህክምና 2 ሴት እና 2 ወንድ ልጆችን በሰላም ተገላግላለች።

በሆስፒታል ይህ በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ሀኪም ዶክተር ዳግም ሽመላሽ፤ ታህሳስ 20/2015 ዓ.ም አንዲት እናት 4 ህፃናትን በቀዶ ህክምና ማዋለዳቸውን ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት እናትና ህፃናቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

የህፃናቶቹ ወላጆች ካለቸው ገቢ አንፃር አሁን ላይ ባለው የኑሮ ሁኔታ ልጆቹን ለማሳደግ የሚቸገሩ በመሆኑ ደጋፊ አካል እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡

@tikvahethmagazine