Get Mystery Box with random crypto!

Reyan Records

የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records R
የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records
የሰርጥ አድራሻ: @reyan_records
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 346

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2022-11-09 23:03:06
መርሳትን ምመርጠው
ለራሴ ራሱ መድገም ስለምፈራ ነው? ወይስ እያስመሰልኩ?..... ከሰዎች ምንም ያህል ብሸሽ ከራሴም ብለያይ...... ግን ግን አንተ ጋር ስሆን ምንም ነገር መርሳት አቆማለው....ግን አንተ ጋር እንደታመምኩ አምናለው ምኔንም እንደሆነ ጭምር ...ላንተ ሲሆን የሚለየው ሰሚም፣ አዋቂውም ፣ ተመልካቹም ስለሆንክ ይሆን እንዴ?........ ብቻ ስላለኸኝ እድለኛ ነኝ የማስበውን ያክል ባልቀርብክም እንኳን ወደኔ ነይ ያልከኝ ጥግ እንኳን ልደርስ መንገዱን ባልጀምርም እንኳን... ከእውነታው ጋር ምጋፈጠው አንተ ጋር ብቻ ስለሆነ! ...አልሀምዱሊላህ

(glamor)
39 viewsGlamor, 20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 19:09:03 የሴቶችን ድንግልና የሚወስደው ማን ነው?
ይህን ፅሁፍ ለማዘጋጀት ያነሳሳኝ አብዛኛውን ጊዜ አንዳንድ ወደ እስልምና እንጣራለን የሚሉ ሰዎች ህግጋቱን ሁሉ ሴቶች ላይ ጫን አድርገው ወንዶችን ብዙም ሲሉ አይሰማም፡፡
ሰሞኑን አላዋቂዎች ብዙ ሲሳለቁ እና እራሳቸውንም መግለጫ ሰጪ አድርገው ሲያዩ ተመልክተናል፡፡ የሴት ልጅ ድንግልና በብዙ መንገድ ይሄዳል፡፡ ለምሳሌ ሴት ልጆችን በገዛ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው በመደፈር ሁሉ ያጡታል፡፡ ሴት ልጆች ሲደፈሩ ያውም ደፋሪያቸው እየታወቀ “በቃ ዝም በይ” አይነት ማስጠንቀቂያዎች ይሰጧታል፡፡ ድንግልና ያለ ግንኙነትም ሊጠፋ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ዑለማዎችም ሀኪሞችም ይገልፃሉ። ስለዚህ ድንግልና የሌላት ሁሉ ብልግና ፈፅማለች ማለት ዝቅ ሲል አላዋቂነት ከፍ ሲል ብልግና ነው። በሌሎችም መንገዶች ድንግልና ይሄዳል፡፡
አብዛኛዎቹ ሴቶች ልጅ በነበሩበት ሰኣት በጣም አይን አፋር እና ድንጉጥ ናቸው፡፡ ወንድን መቅረብ አይፈልጉም፡፡ ሴቶቹን ወደ መጥፎ ነገር የሚመሩዋቸው መጥፎ ሴት ጓደኞች እና ምላሳም ወንዶች ናቸው፡፡
መቼም ወንድ ከሌለ ሴቶች በራሳቸው ድንግልናቸውን አጠፉት አይባልም፡፡ አንድ ሴት ልጅ ድንግልናዋን ስታጣ እሷን ብቻ ከመውቀስ በምላሱ አታሎ፣ አጭበርብሮ ድንግልናዋን የወሰደባትን ለምን በደንብ አይኮንኑትም?
አስገራሚው ሴት ልጅ ስትሰራ ከነበረችው መጥፎ ነገር ቶብታለች ሲባል “እሷ እኮ…. ነበረች…. መጠንቀቅ ነው …. ምን ይታወቃል” እና የመሳሰለውን ትንኮሳዎች ይተበተባሉ፡፡
ወንድ ልጅ ግን ለምሳሌ አንዴ በድፍረት 21 ወይንም 22 አመት የሚጠጋው ወንድ ለጓደኞቹ “ከ180 እስከ 200 ሴቶች ጋር ግንኙነት ፈፅሚያለሁ” እንዳላቸው ሲናገሩ ሰምቻለሁ (የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የእኔ ኡመቶች ወንጀል ይማራል ግልፅ የሚያወጣው ሲቀር ብለዋል፡፡ ወንጀልን እንደቁም ነገር እና ጀብዱ የምታወሩ ሰዎች አላህን ፍሩ)፡፡ ለምሳሌ ይህን ሁሉ ሴት የነካካ ወንድ ቶብቷል ቢባል “አቤት እሱ እኮ ሷሊህ ነው፡፡ አቤት አኽላቁ፡፡ አቤት እሱን ያገኘች” ተብሎ ይለፈፋል፡፡
ለምን?
አላህ በተከበረው ቁርኣን ላይ
- ዝሙትን በተመለከት ተከልከሉ ሲል ለወንዱም ለሴቱም ነው፡፡
- ዝሙት ከፈፀሙ ያላገቡ ከሆኑ 100 ጅራፉ ይገረፉ ሲል ወንዱንም ሴቷንም ነው፡፡
- ዝሙትን የፈፀሙት ያገቡ ከሆነ በድንጋይ ተቀጥቅጠው ይገደሉ ሲል ወንድንም ሴትንም ነው፡፡
ታድያ ለምን ይሄን ያህል ሁለቱንም የሚመለከተውን ህግ ሴቶች ላይ ብቻ ጫን ማለት አስፈለገ፡፡ እንጨት ለምሳሌ በራሱ አይቀጣጠልም እሳት ሲቀላቀልበት ቢሆን እንጂ፡፡ ስለዚህ ወንድ እና ሴት በፈፀሙት ወንጀል አንዱን ብቻ ጠንከር አድርጎ መውቀሱ በተለይ ከኢስላም ውጭ ያሉ ሰዎች “ኢስላም ሴትን ይበድላል” እንዲሉ የሚያደርጋቸው ይህ ነው፡፡
ፍትሀዊ የሆነ ሀይማኖት ይዘን ፍትህ የሌለ አስመስለን አናቅርበው፡፡ ያለ እውቀት መናገር ሁሌም ጣጣው ከሚታሰበው በላይ ነው፡፡
የቶበቱ ሰዎችን አስመልክቶ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ወደ አላህ የተመለሰ ወንጀል እንደሌለበት ነው፡፡” ብለው ሲያበቁ ወደ አላህ የተመለሱ ሰዎችን እያጣጣሉ መናገር መሀይምነትን በይፋ የሚያሳይ ነው፡፡
አስገራሚው ግልፅ ቢድኣና ሺርክን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የሌላቸውን ጥንካሪ እና ድፍረት ወንጀል ላይ የወደቁት ላይ ሲያደርጉት እንመለከታለን፡፡
ወንጀል በድብቅ የሰራ ሰው አይቡ ይደበቅለታል፡፡ ቢድኣን እና ሺርክን በአደባባይ የሚፈፅም ደግሞ በአደባባይ ሙስሊሞች እንዲጠነቀቁት መልስ ይሰጥበታል ይህ ነው ፍትህ እና ሚዛናዊነት፡፡
ዛሬ የቢድኣ ካዝና ለሆኖ ሰዎች ጥብቅና ቆመው እነሱን አናስነካም፡፡ እነሱን የነካ “አይባቸውን እንዳወጣ ነው” ሲሉ ይቆዩና ተደብቀው ወንጀል የሚሰሩ ሰዎችን “ተከታትለን በካሜራ እናጋልጣለን” ብለው ስሜት አምላኪነታቸውን ያሳዩናል፡፡
እንዲህ አይነት መሀይማን ጉዳታቸው እጅጉን የከፋ ነው፡፡

ፅሁፌን ስጨርስ ሴቶችን እንደነ መርየም ድንግልናችሁን ጠብቁ ስንል፣ ወንዶችንም ልክ እንደነ ኡስማን ኢብን አፋን ሁኑ ከዝሙት ራቁ፡፡ ወንድ እና ሴቶች ሆይ! አላህን ፈርታችሁ ቶሎ ተጋቡ፡፡ በኢስላም ትዳር ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ከትዳር ያለ አስገዳጅ ሀጃ በመዘግየታችሁ ምንም የምትጨምሩት ነገር የለም፡፡ የምታጡት ነገር ቢብስ እንጂ፡፡
ስለ ትዳር የበሰሉ ሃያእ ያላቸውን ታላቆችን አማክሩ፡፡

ፀሀፊ ሳዳት ከማል
51 viewsGlamor, 16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 18:58:29 አንፍረድ!
[የረጅም ግዜ ብሶት የወለደው... ]
:
ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከሕልማቸው ተስፋን ያጡ ወጣቶች እንዲሁም ጎልማሶች ሐያታቸውን በራሳቸው ሲቋጩት እያየን ነው። (እየተለማመድነው ነገር...)

በሰው ተከቦ ሰው እንደማጣት፣ ለመራመድና ለመጠንከር በመጣጣር ውስጥ ከድባቴ (depression) ጋር መታገል እጅግ ፈታኝ ነው። ያደክማል... ለዛም ነው ደፍረው "ጌታዬ ያንተ ቀጠሮ አያሻኝም በቅቶኛል" ሲሉ እጅ የሚሰጡት.... ስታወራው ዝም የሚልህ ወዳጅህ፣ ሲርቅህ የራሱ ጉዳይ ያልከው ወንድምህ፣ በስህተቱ ምን አገባኝ የምትልለት ጓደኛህ እንደሰማይ የራቀው ተስፋውን ይበልጥ እያራቅክበት እንደሆነ ተረዳው። አንተን ችግር አይነካህም ማለት አይደለም አውቃለሁ። ግን ደሞ ያንተ ብሶት፥ ነገ ራሱን አጥፍቶ ከምትገናኘው የፀፀት ጅራፍ ይቀላልና... ረጅም እድሜህን አብሮህ በመከራና በደስታ ሲጋራህ የነበረ ወዳጅህ ሲርቅ ጠይቀው.... "ሁሌ ለምን እኔ?" የሚለውን የፉክክር ቃል ተወው...

የሚሰማው እንደሌለ ማሰብ፣ የኑሮ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች፣ የቤተሰብ ብዙ መጠበቅ፣ (ዛሬ እንደሰማነው ከሆነ) ብድር፣ በስራ ላይ ውጤታማነትን ማጣት፣ በፍቅር ግንኙነት ስኬታማ አለመሆን ና የመሳሰሉት ተደማምረው እጅን ወደአንገት ያሰድዳሉ። ከአጀል መድረስ ጋ አንነካካም፣ የሆነው ሆኖ ግን ሰበቢያው ያሳስበናል።

በየካፌው የዞራችሁ መሆናችሁ፣ ፈገገ ማለቱ አሊያም ፊቱ መውዛቱ ለደህንነቱ ማረጋገጫ አይደለም። ብቻዬን ልሁን ሲልህ እሺ ማለትህ መልካም ጓደኝነት አይሆንም። ሐጃህ ያውጣህ ማለትም የሙእሚን ባህሪ አልነበረም። ጠንካራ ነበርና የዛሬ የውስጥ ብሶቱን ጠንክሮ ያልፈዋል ማለት አይደለም። ሺህ ጓደኞች አሉት፣ የሚያወራው ሰው አያጣም ስትል በቸልታ አትለፈው። ሺህ ሰዎች ኖረውት አንድ  አዳማጭ የሌለው እልፍ ነው።

በሩሑ ላይ ጨክኖ የሔደ ሰው እዚያ ያደረሰውን ችግር ማሰብ ይቻልሐል? የኔ ያልከው፣ አውቀዋለሁ የምትለው ጓደኛህ ምን አሳር ቢገጥመው ነው እንዲህ ያደረገው? (ሐሳቡ አይኖርህም )
ችሎ ችሎ ሲያመልጥህ ... ፀፀት አይበቃህም። የሱ ጓደኛ መባልህ ሐሳቡን ካላቀለለው ወዴት ነው ጓደኝነትህ? ጓደኝነት ሰጥቶ መቀበል አይደለምና ፍርድህን ለአላህ አኑረህ ለጓደኛህ ኑረው።

ሳይረፍድ... እየሳቀ ሳያታልልህ... ድብርቱ አቅሉን ሳይወስደው...  እየፋፋ ሳያመልጥህ... ነብሱን ቁማር ሳይበላ... ፀፀት ደጃፍህ ሳይዘልቅ... ኑሮህን ሐዘን ሳይወርሰው.... ለጓደኛህ ጓደኛ ሁን!


@yeruh_weg
22 viewsGlamor, 15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 22:11:14 ድሮ ድሮ በሩቁ ሳውቃት፣ እሷን በሆንኩ ብዬ እመኝ ነበር… የምሰማው የህይወቷ ድሎት፣ ምናል እንደሷ በኖርኩ ያስበለኝ ነበር… ነገር ግን ቀረብ ብዬ ከኛ የተደበቀውን የህይወቷን ቁምስቅል በራሴ ስሰማው… ለካ እኔ ነበርኩ በድሎት ስኖር የከረምኩት…

መድ
19 viewsGlamor, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 07:12:33
ለምን ልማር?
የመማር ፋይዳ ምንድን ነው?
ባልማርስ ምን እሆናለው?
የተማሩ የት ደረሱ?
12አመት ከምማር ብሰራ ኖሮ?
የሚሉ ጥያቄዎች የብዙ ተማሪዎች ጥያቄዎች ከሆኑ ሰነበቱ። በርካታ መምህራን እና የትምህርት ባለሙያዎች የዘንድሮ ተማሪ የመማር ፍላጎት የለውም። ተነሳሽነቱ በጣም ቀንሷል። እያሉ ሲያማሩ ይሰማሉ። ተማሪዎቹም ስለ ትምህርት ሲነሳ የቤተሰብ አስገዳጅነት ባይኖር ባይማሩ ደስታቸው መሆኑን ይገልፃሉ።
የከዋክብት ወግ (Galaxy Talk) የተማሪዎች መድረክ "ለምን ልማር?"
በሚል ርዕስ ከላይ ያነሳናቸውን ሃሳቦች አዝናኝ እና  አነቃቂ በሆነ መልኩ ቁም ነገር ለማስጨበጥ በአይነቱ ልዩ መርሃ ግብር አሰናድቷል።
በመሆኑም ተማሪዎች ፣ ወላጆች ፣ መምህራን እና የትምህርት ባለሙያዎች በዚህ መድረክ ላይ እንዲገኙልን እንጋብዛለን።
#መግቢያ -በነፃ
#ለመመዝገብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ።
https://docs.google.com/forms/d/1Hls03YXWjm4o29kNFq8m7nIJXT6AtxSYwUURvFPPnP0/edit
0911947764 0966104412
@galaxyplc
28 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 07:28:43 < " የአዕምሮ ባርነት ሲሉ ምን ለማለት ነው። በየትኛው መንገድ ነው በአእምሮ ባርነት ውስጥ የተዘፈቅነው? >

<< " ይህን በቀላሉ ለመረዳት " ሴት" ን መመልከት ትችላለህ። ሴት በአእምሮ ባርነት ከሚሰቃዩት መሀል ግንባር ቀደሟ ናት። ቅጥ ያጣው የዘመናዊ አስተሳሰብ ነፃነት ከየትኛውም ህብረተሰብ በላይ የጎዳው ሴትን ነው። በየትኛውም ዘመን ሴት ታፍራና ተከብራ የምትኖረው የእምነት መፅሀፎች ላይ እና እምነታቸውን በትክክል በሚተገብሩ አማኞች ህሊና ውስጥ ብቻ ነው። በዘመናችን ሴቶች መኖር የሚፈልጉት በሰዎች አስተሳሰብና በየዘመኑ በሚሰጣቸው ፍቺ እንጂ በእምነታቸው መመርያና ፍቺ አይደለም። ይህን ቅድሚያ እንዳያስተውሉ አዕምሯቸው በቁስ ጥገኛ እንዲሆን ተደርጓል። እምነት የሌላቸው ሰዎች በግልፅ እምነት የለንም ሲሉ ይኮነናሉ ነገር ግን አማኝ ነን የሚሉ ሰዎች ከእምነት መመርያቸው ውጪ ሲሆኑ እምነታቸውን እየተቃወሙና መመርያው ትክክል አይደለም እያሉ እንደሆነ አያስተውሉም። የአእምሮ ባርነት ውስጥ እንዳለን ለመገንዘብ ሴትን የወሲብ ምልክት ማድረጋችን መመልከት እንችላለን። አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ሲመለከት ከሰውነት አካላቶቹ በሙሉ ቀድሞ ፈጣን ምላሽ (Active response) የሚሰጠው ብልቱ ነው። ስልኳን ለመቀበል፣ ለመግባባትና ሌሎች ብዙ ጥሩም ይሁን መጥፎ ነገሮችን ለማድረግ የሚያስበው ብልቱ ምላሽ ከሰጠ በኋላ ነው። ለምን ብለን ብንል የአዕምሯችን ቅኝ ገዢዎች የጫኑብን አስተሳሰብ ነው። ሴት አዕምሮዋ በባርነት እንደሚማቅቅ የምታውቀው ስትደፈር ምንም ባለማለቷ ነው። የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ይደፍራታል፣ የፋሽን ኢንዱስትሪው ይደፍራታል፣ የፊልም ኢንዱስትሪው ይደፍራታል፣ የመዝናኛው ኢንዱስትሪ በዘመናዊ መንገድ በወርቅ አልጋ አስተኝቶ በአደባባይ ይደፍራታል። በዚህ ረቂቅ በሆነ ደፈራ ሴቷም ደስተኛ ነች። ለመደፈር እንደ መስፈርት የሆኑትን ክብደቷን፣አካላዊ ቁመናዋን መልኳን በማቆንጀት ጊዜዋን ማባከንና አዕምሮዋ ሳይዳብር በእንጭጩ መተው ስኬት እንደሆነ አምናበት ቀና ብላ ትሄዳለች። መልኳን እንጂ ማንነቷን ማቆንጀት ተራ እንደሆነ በአዕምሮዋ ቅጅ ገዢዎች የተበሰረላትን ብስራት አሜን ብላ ተቀብላለች። ስለ ሴት ጥብቅና እንቆማለን ብለው የሚሉት እንኳ ይህን እውነት መመልከት ተስኗቸዋል። በተሰጣቸው ፍቺ ተስማምተው ሌሎችን ለማሳመን ይጥራሉ። በባርነት ለምትማግዳቸውና በባርነታቸው ለሚደሰቱት የፆታ እኩልነት፣ Affirmative action እያልክ የበታችነትን የሚሰብክ እድል መፍጠር፣ ተቋም ማቋቋም ስላቅ ነው። በሀሳብ ባርነት የተጠፈነገ አዕምሮ ስለ መፅሀፍ ሽፋን እንጂ በመፅሀፉ ውስጥ ስላሉት ገፆችና በገፆቹ ውስጥ ስለ ሚከተቡት ነገሮች አይጨነቅም። ሁላችንም እንዲህ እየኖርን ነው ገፅታችንን እውነት እየቀባን ውስጣችን ግን ባዶ ውሸት። ብንደኸይ፣ ብንገዳደል፣ ብንወነጃጀል አይገርምም። ምክንያቱም በባርነት በወደቀ አዕምሮ ሚዛናዊነት፣ አዲስ ሀሳብና ፈጠራ እንዴት ብሎ ሊኖር ይችላል? " >>
        ~~
44 viewsGlamor, 04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 07:18:36 አንዳንድ ውሻ የሰው እግርን ለመንከስ ሲያስብ እየላሰና እየተላፋ ያዘናጋል!!! ከዛም ንክሻውን ይፈጽመዋል! ያኔ በራሳችን መገረም ሳይኖርብን አይቅርም! ለምን ቢሉ አሳንሰን ያየነው አካል ከኛ ተሽሎና በልጦ ስለተገኘ!!!
99 viewsGlamor, 04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 06:27:22 ~ዘፈን ማዳመጥ መጨረሻው~
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
➧:አንድ ሼኽ እንዲህ ይላሉ. . .➘

:ከፈጅር ሰላት ቡሀላ አንድ የ13 አመት ህፃን እኔ ጋር ይመጣና አባቴ ከባድ ለሆነ ጉዳይ ስለሚፈልግህ በፍጥነት እንድትመጣ ይለኛል

:ተከትየውም ሄድኩኝ እንደደረስንም አንድ 50 አመት የሚሞላቸው አዛውንት ብቅ ይላሉ ልጄን በጣም እያመማት ነውና እባክህ ቁርአን ቅራባት ይሉኛል፧ ቤት ውሰጥ ስገባም የልጅቷ ፊት ላይ ሻሽ ነገር አለ ለሞት እያጣጣረች መሆኗንም ተመለከትኩ ወዲያውም (ላኢላሀኢለላህ) በይ አልኳት ብዙ ጊዜም ደጋግሜ ላኢላሀኢለላህ በይ አልኳት ምን ትላለች ይህች ወጣት ልጅ➘
ዋ !! ጉዴ ደረቴ ላይ ጠበበኝ.....ዋ!!
ጉዴ ደረቴ ላይ ጠበበኝ ትል ጀመር፡፡

እንደ መብረቅ ሆኖ ከወረደብኝ ነግግሮቿ መሀል ....

SEE MORE

ቀጣዩን ለማንበብ ይንኩት
110 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 03:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 20:12:50
ብለዋቹሀል
133 viewsGlamor, 17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-21 22:08:31 የትራፊክ ፖሊሱ

አንድ የትራፊክ ፖሊስ ሥራውን ከለቀቀ በኋላ በአንድ መስጂድ በኢማምነት ማገልገል ጀመረ አሉ። በመጀመሪያው ቀን ደዕዋውም በሚከተለው መልኩ ደዕዋ አደረገላቸው.. .
...
~ ወደ አኺራ የምታደርጉት ጉዞ ቀላል እንዳይመስላችሁ ረጅም፣ አድካሚ እና ውጣውረድ የበዛበት መሆኑን ተረዱ።

~ ከመንቀሳቀሳችሁ በፊት ሁለመናችሁን ፈትሹ፣ ትክክለኛ ዕውቀትና መረጃ ይኑራችሁ፤ ወዴት እንደምትንቀሳቀሱ እወቁ፤

~ ጥሩ ስሜት ላይ ሁኑ፣ ትኩረት አይለያችሁ፣ ውስጣችሁን ከአልባሌ ነገሮች አፅዱ፤

~ በእንቅስቃሴያችሁ ጊዜ ሁሉ የተቅዋ ቀበቶ እሠሩ፣ በፍፁም እንዳትዘናጉ፤

~ በፍጥነታችሁ ምልክቶችን ተከተሉ፤ ከልክ በላይ መፍጠንም ሆነ አላስፈላጊ በሆነ መልኩ መዘግየት አደጋ አለው፤

~ ጥፋት አታብዙ፣ ሁሌም ከስህተታችሁ ተማሩ፣

~ ህግ ያከበራችሁ እንደሆነ አትፍሩ ፤ ቀኛችሁን በመያዝ በመንገዱ ላይ ቀጥ ብላችሁ ሂዱ፤

~ በአላህ ፍራቻና እዝነቱን ክጀላ መካከል ሁኑ። ሚዛናችሁን ጠብቁ፤

~ በመንገዱ ላይ ሥርዓት ይኑራችሁ፤ ትከበሩ ዘንድ ሌሎችን አክብሩ፤

~ ሶላት የሚባሉ የኃይል ማደያ ጣቢያዎች አሉ፤ ከደከማችሁ ወደነርሱ ጎራ በሉ፣

~ ራስወዳድ አትሁኑ የወደቀን አንሱ፣ የደከመውን አግዙ።

~ ሁሌም ሁለቱን የመመሪያ መፅሐፎች አጥብቃችሁ ተከተሉ፣ ህግን አትተላለፉ፤
.
ይህን በሚገባ የተገበራችሁ እንደሆነ ሲራጥን በከፍተኛ ፍጥነት የመሻገር ዕድላችሁ ከፍ ይላል ...። ካሰባሁበትም በሰላምና በስኬት ትደርሳላችሁ።
.
መልካም ወደ አኺራ የሚደረግ ጉዞ ይሁንላችሁ።
.
ሁሉም አላህ ባገራለት መልኩ ያስተምር ለማለት ያህል ነው

@Reyan_Records
137 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ