Get Mystery Box with random crypto!

Reyan Records

የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records R
የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records
የሰርጥ አድራሻ: @reyan_records
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 346

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 18

2022-10-11 17:58:25
34 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 12:17:09
ስርዝ ድልዝ
(Glamor)
:
አለማመን ኩራት ድርቀት ...ያጨቀያት ነብስ በሁሉ ነገሯ አላህን አላህን ስታምፅ ትኖራለች (ስራዋ እንደመከነ) ልቧም ስክነትን እንዳጣ ... ለልብ ህክምና በመፈለግ ውስጥ ደግሞ እስልምናን ያሀኘ ሰው በትክክልም ጌታውን ያገኛል ኢስላምን ማወቅ፡ መተግበር፡ እጅ እና እግርንም ለአላህ አሳልፎ መስጠት ለልብ ሰላምን ይሰጣል ልብ ሰላም ካገኘች ወድያ ድርቀትም ይረጥባል ፣ኩራትም በመተናነስ ይተካል አለማመንም ኢስላምን በመቀበል ውስጥ ይከስማል ታድያ ኢስላምስ ያለፈውን መሰረዣ መደለዣ አይሆንም?!
:
49 viewsGlamor, 09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 12:11:06
ትብብር

የዚህ admission card ባለቤት ካርዱን ባስ ውስጥ ወድቆ ስለተገኝ በዚ ስልክ ደውላ ማግኝት ስለምትችል 0910222366 ማስታወቂያውን ያያቹ ደግሞ ልጅቷ ጋር እንዲደርስ ሼር በማረግ ተባበሩ

[ልጅቷ ያለID ስለማያስፈትኗት እባካችሁ ቶሎ ቶሎ ሼር እናርግላት]

ኢትዮጵያዊነት መልካምነት

"SHARE". @ETHIO_ARSENAL
45 viewsGlamor, 09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 08:47:45
ወላሂ ዝም ብላቹ join በሉ
ጥርሳችሁ እስኪ ሰበር ነዉ ምትስቁት ግን በዋላ ጥርሳቹ ተሰብሮ ክፈል የለም
6 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 23:53:51 "እኛ ሃገር ሳይሆን ልቦችን ልንከፍት ነው የመጣነው" ይህ የሙሐመድ አል ፋቲህ ንግግር ነው

"የነብያችን የትንቢት ቃል በሙራድ ቤት ተወለደ" ወንድ ልጅ የተወለደላቸው ሡልጣን ሙራድ ደስታቸውን የገለፁበት ቃል ነበር። ቀናት ቀናትን ወልደው አመታት ነጎዱ። ልጅም ዲነል ኢስላምን በጥልቅ ያውቅ ዘንድ በበርካታ ዑለማዎች ትምህርት ይሰጠው ጀመር። እናቱ ዘወትር ማለዳ እጁን ይዛ የቆስጠንጢኒያን አጥሮች እያሳየችው "ልጄ ሆይ! ያ የቆስጠንጢኒያ አጥር ነው ድል አድርገህ በመክፈት የነቢዩን ትንቢት የምታረጋግጠውም አንተ ነህ" እያለች ግብና ዓላማውን እንዳይዘነጋ አድርጋ ኮትኩታ አሳደገችው። የሴቶች ማህፀን የሙሐመድ አል ፋቲህ አይነትን ጀግናን ትናፍቃለች በተርቢያ ኮትኩታ በአላማ አንፃ የምታሳድግን እናት አለም ተርባለች!
ቆስጠንጢኒያ በጠንካራ ግንቦች የታጠረች የሮሞች መናገሻ ከተማ ናት። በየግንቦቹ መካከል ታላላቅ ሰው ሰራሽ ሀይቆች ይፈሷታል። የባህር በሮቿ በትላልቅ ፀረ መርከብ ጦሯ የታጠሩ በመሆናቸው ለወራሪዎች ፍፁም አይመችም። በእያንዳንዱ ግንብ ላይም በሺዎች የሚቆጠሩ የሮም ጦረኞች ሁሌም በተጠንቀቅ እንደቆሙ ነው።
እስልምና ወደ አውሮፖ እስዳይስፋፋ ዋናው ፈተና የሆነችውም እሷው ናት። ለዚህም ነው የኮንስታንቲኖፖል በድል መከፈት እስልምናን ወደ አውሮፓ ለማስፋፋት ወሳኝ ምዕራፍ የሆነው።
ከ22 በላይ የሙስሊም መሪዎች ይህቺን ከተማ ለመክፈት ከበባ ቢያደርጉም አንዳቸውም ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል። ከታላቁ ሰሐባ አቡ አዩበል አንሷሪ እስከ ነጎድጓዳማው መብረቅ ባየዚድ ከሱልጣን ሙሐመድ አልብ አርሰላን እስከ ሱልጣን መሊክሻህ ከኡመያድ ኺላፋ እስከ አባሲያ ኺላፋ ሁሉም የሙስሊም መንግስታቶች የአለማችን መገናኛ የሆነችውን ኮንስታንትኖፕልን ለመክፈት ከተማዋንም ከበዋል። በመስጂድ ሚናራዎች ተውባ አዛን ከየጨቅጣጫው የሚሰማባት ከተማ ለማድረግ ለአመታት ለፍተዋል ግና ሳይሳካላቸው በአጥሯ ስር ወድቀው ይህችን ዓለም ተሰናበቱ።
"ቆስጠንጢያን ትከፍታላችሁ - ምን ያምር አሚር ነው አሚሯ፣ ምን ያምር ጦር ነው ያም ጦሯ” በማለት ነብያችን የተናገሩትን ትንቢት ሊፈፅም የዓለም ከተሞች ሁሉ ቁንጮ የሮማን ኢምፓየር ዋና ከተማ፣ የሁለት አህጉሮች እና የአራት ባህሮች ማሳለጫ የአሁኗ ኢስታንቡልን ለመክፈት አይበገሬው ጀግና፣ እጅግ ሚስጥረኛው የጦር ስልት አዋቂ የሙጃሒዶች መሪ ከዕድሜው የማይጠበቀውን ሊሰራ የነብዩን ትንቢት ሊፈፅም በ19 ዓመቱ የአባቱን ዙፋን ተረከበ። ወታደሮቹን አደራጅቶ በ 19 አመቱ ቆስጠንጢኒያን ድል አድርጎ ከፈተ።
ከድሉ በኋላ ሱልጣን ሙሐመድ አል ፋትህ የዑስማንያ ስርወ መንግስት መናገሻ ከተማ አደረጋት። ስሟንም "ኢስላም ቡል" ብሎ ሰየማት "የኢስላም በር" እንደማለት ነው።
የምዕራቡ አውሮፓ ክርስቲያኖች በሙስሊሞች ድል በጣሙኑ ተገርመዋል፣ ተደናግጠዋልም አዝነዋል። ከኢስላም ቡል አንድ ሐይል ተነስቶ እንደሚያጠፋቸው በደራሲዎቻቸው፣ በጋዜጠኞቻቸውና በመንግስቶቻቸው እየተለፈፈ የክፋት ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨቱን ተያያዙት።
የአውሮፓ መሪዎችም ብዙ ሰዓታት የወሰዱ ስብሰባዎችና ምክክሮችን በተለያዩ ቀንና ቦታ ከማድረግ ወደ ኋላ ብለው አያውቁም። በመካከላቸው ያሉትን ችግሮች ትተው ሙስሊሞች ላይ በጋራ እንዲዘምቱ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ግፊቶች ተበራከቱባቸው። ፓፓ ኒኮላ አምስት በቆስጣንጢኒያ መውደቅ ከፍተኛ ፀፀትና ንዴት ተሰምቷቸዋል።

የአውሮፓ የታሪክ ፀሐፊዎች "የመሀከለኛው ዘመን ታሪክ መጨረሻና አዲሱ ታሪክ መጀመሪያ" ብለው ይጠሩታል።

ፅሑፎቼን አንብቦ ለሌሎች ወንድምና እህቶች ሼር በሚያደርግ ሰው ላይ ሁሉ የአላህ እዝነት ይስፈን
21 viewsGlamor, 20:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 10:31:05
42 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 06:57:34 ቢሻራ ...

ከማዶ ባሻገር የሰገዱላት እሳት ወደመች ዝንተአለም የፋርስ ሃያልነት መገለጫ መንደዱ ምን ይሁን ሚስጥሩ? 
በውነቱ ያ እሳት ተአምር የያዘ  ሚስጥራዊ ማገዶ ነበረው በዛች ሚስጥር መጁሳነት ገነነ ፅልመትን የያዘ ብርሃን አንድ ከተማ ሙሉ እንዳላበራ እስትንፋሱ ቆመ ።
አላሁ አክበር  !!
በርግጥም ያቺ እሳት የጠፋችው   በመሲህ ቢሻራ አህመድ ነው
ረቢእ 12 በጅምሁር ሙአሪኾች በማይለቁ ብራናወች በሙስሊሞች ልቦና ተነቅሳ ቀረች .

የተቀበረች እንስት የቢሻራውን ሀያልነት ትመስክር  !!

የበዳዮች ነፍስ የጣኦት አምላኪያን አንደበት  ስለቢሻራው ውድነት ትናገር! 
ኡመር ቢን ኸጣብ ይመስክር  ፊታቸው የከበረው ኢማም አሊይ  ስለቢሻራው ልእልና ይናገር

በውልደታቸው ዳግም ምድር ተወለደ የኢስራኤላዊያን ሴራ ተጋለጠ
አላሁ አክበር

https://t.me/Reyan_Records
12 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 22:24:50
ልዩ ግብዣ! - ዝክረ ኢማም ዩሱፍ አል-ቀረዷዊ

ኢማም ዩሱፍ አል-ቀረዷዊ (ረሂመሁላህ) - ሕይወት እና ፋናቸው
الإمام القرضاوي- حياته وآثاره

ዝክረ ኢማም ዩሱፍ አል-ቀረዷዊ ... በሚል ርዕስ ለየት ያለ የሸይኹን ህይወት ታሪክ፣ ስራቸውን፣ ያሳለፏቸውን የዳዕዋ ሂደቶች፣ ያበረከቷቸውን አስተዋጾና የነበራቸውን ሚና የሚገልፁ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ። ፕሮግራሙ ከሸይኹ ጋር ተገናኝተው ከነበሩ ግለሰቦች ጀምሮ መፅሃፍቶቻቸውን ወደ ሀገሪኛ ቋንቋ የተረጎሙ ፀሃፊያን እንዲሁም የሸይኹን ስራዎች የሚያሳዩ የተለያዩ መረጃዎች በኦዲዮቪዧል የሚቀርቡ ይሆናል። ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም ፎርሙን ይሙሉ።

ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ቦታዎን ይያዙ!
ቦታ፡ ጦር ሃይሎች ኢሙ ታወር አዳራሽ
አዘጋጅ፡ ኢሽራቅ ኢትዮ ኢንተርናሽናል ኢስላሚክ አሶሴሽን

መግቢያ በነጻ!
ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ በዚህ ቅፅ በመመዝገብ ፈጥነው ቦታዎን ይያዙ!

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeyrbmyIPY57J6rKr_2zPhQ6d-zggCafZse_yOsiWSPYIIITg/viewform
25 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 16:46:23 ዛሬ ያጋጠመኝን ነገር መቼም አልረሳውም


ዛሬ ጁመዓ ልሰግድ ወደ ሱመያ መስጂድ ቀደም ብዬ ነበር የሄድኩት እናም ጓደኞቼ አስከሚመጡ ድረስ መስጂዱ በር አካባቢ እየጠበቅኩ በነበረበት ሰዓት የሆነ ልጅ እንዴት ነው መስለም የምችለው ብሎ ጠየቀኝ   ወላሂ እንዴት እንደደነገጥኩ እና ደስ እንዳለኝ አትጠይቁኝ  የተወሰኑ ነገሮች ላይ ካወራን ቡሀላ የሱመያ መስጂድ ኢማም ጋር ወስጄው ሸሃዳ ይዟል ። አልሃምዱሊላህ ወንድማችን የ ፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የነበረ ሲሆን ዛሬ ላይ እስልምናን ተቀብሎ ጁምዓን አብረን ሰግደናል ።

@Reyan_meme_and_islamic_post
43 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ