Get Mystery Box with random crypto!

'እኛ ሃገር ሳይሆን ልቦችን ልንከፍት ነው የመጣነው' ይህ የሙሐመድ አል ፋቲህ ንግግር ነው 'የነ | Reyan Records

"እኛ ሃገር ሳይሆን ልቦችን ልንከፍት ነው የመጣነው" ይህ የሙሐመድ አል ፋቲህ ንግግር ነው

"የነብያችን የትንቢት ቃል በሙራድ ቤት ተወለደ" ወንድ ልጅ የተወለደላቸው ሡልጣን ሙራድ ደስታቸውን የገለፁበት ቃል ነበር። ቀናት ቀናትን ወልደው አመታት ነጎዱ። ልጅም ዲነል ኢስላምን በጥልቅ ያውቅ ዘንድ በበርካታ ዑለማዎች ትምህርት ይሰጠው ጀመር። እናቱ ዘወትር ማለዳ እጁን ይዛ የቆስጠንጢኒያን አጥሮች እያሳየችው "ልጄ ሆይ! ያ የቆስጠንጢኒያ አጥር ነው ድል አድርገህ በመክፈት የነቢዩን ትንቢት የምታረጋግጠውም አንተ ነህ" እያለች ግብና ዓላማውን እንዳይዘነጋ አድርጋ ኮትኩታ አሳደገችው። የሴቶች ማህፀን የሙሐመድ አል ፋቲህ አይነትን ጀግናን ትናፍቃለች በተርቢያ ኮትኩታ በአላማ አንፃ የምታሳድግን እናት አለም ተርባለች!
ቆስጠንጢኒያ በጠንካራ ግንቦች የታጠረች የሮሞች መናገሻ ከተማ ናት። በየግንቦቹ መካከል ታላላቅ ሰው ሰራሽ ሀይቆች ይፈሷታል። የባህር በሮቿ በትላልቅ ፀረ መርከብ ጦሯ የታጠሩ በመሆናቸው ለወራሪዎች ፍፁም አይመችም። በእያንዳንዱ ግንብ ላይም በሺዎች የሚቆጠሩ የሮም ጦረኞች ሁሌም በተጠንቀቅ እንደቆሙ ነው።
እስልምና ወደ አውሮፖ እስዳይስፋፋ ዋናው ፈተና የሆነችውም እሷው ናት። ለዚህም ነው የኮንስታንቲኖፖል በድል መከፈት እስልምናን ወደ አውሮፓ ለማስፋፋት ወሳኝ ምዕራፍ የሆነው።
ከ22 በላይ የሙስሊም መሪዎች ይህቺን ከተማ ለመክፈት ከበባ ቢያደርጉም አንዳቸውም ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል። ከታላቁ ሰሐባ አቡ አዩበል አንሷሪ እስከ ነጎድጓዳማው መብረቅ ባየዚድ ከሱልጣን ሙሐመድ አልብ አርሰላን እስከ ሱልጣን መሊክሻህ ከኡመያድ ኺላፋ እስከ አባሲያ ኺላፋ ሁሉም የሙስሊም መንግስታቶች የአለማችን መገናኛ የሆነችውን ኮንስታንትኖፕልን ለመክፈት ከተማዋንም ከበዋል። በመስጂድ ሚናራዎች ተውባ አዛን ከየጨቅጣጫው የሚሰማባት ከተማ ለማድረግ ለአመታት ለፍተዋል ግና ሳይሳካላቸው በአጥሯ ስር ወድቀው ይህችን ዓለም ተሰናበቱ።
"ቆስጠንጢያን ትከፍታላችሁ - ምን ያምር አሚር ነው አሚሯ፣ ምን ያምር ጦር ነው ያም ጦሯ” በማለት ነብያችን የተናገሩትን ትንቢት ሊፈፅም የዓለም ከተሞች ሁሉ ቁንጮ የሮማን ኢምፓየር ዋና ከተማ፣ የሁለት አህጉሮች እና የአራት ባህሮች ማሳለጫ የአሁኗ ኢስታንቡልን ለመክፈት አይበገሬው ጀግና፣ እጅግ ሚስጥረኛው የጦር ስልት አዋቂ የሙጃሒዶች መሪ ከዕድሜው የማይጠበቀውን ሊሰራ የነብዩን ትንቢት ሊፈፅም በ19 ዓመቱ የአባቱን ዙፋን ተረከበ። ወታደሮቹን አደራጅቶ በ 19 አመቱ ቆስጠንጢኒያን ድል አድርጎ ከፈተ።
ከድሉ በኋላ ሱልጣን ሙሐመድ አል ፋትህ የዑስማንያ ስርወ መንግስት መናገሻ ከተማ አደረጋት። ስሟንም "ኢስላም ቡል" ብሎ ሰየማት "የኢስላም በር" እንደማለት ነው።
የምዕራቡ አውሮፓ ክርስቲያኖች በሙስሊሞች ድል በጣሙኑ ተገርመዋል፣ ተደናግጠዋልም አዝነዋል። ከኢስላም ቡል አንድ ሐይል ተነስቶ እንደሚያጠፋቸው በደራሲዎቻቸው፣ በጋዜጠኞቻቸውና በመንግስቶቻቸው እየተለፈፈ የክፋት ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨቱን ተያያዙት።
የአውሮፓ መሪዎችም ብዙ ሰዓታት የወሰዱ ስብሰባዎችና ምክክሮችን በተለያዩ ቀንና ቦታ ከማድረግ ወደ ኋላ ብለው አያውቁም። በመካከላቸው ያሉትን ችግሮች ትተው ሙስሊሞች ላይ በጋራ እንዲዘምቱ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ግፊቶች ተበራከቱባቸው። ፓፓ ኒኮላ አምስት በቆስጣንጢኒያ መውደቅ ከፍተኛ ፀፀትና ንዴት ተሰምቷቸዋል።

የአውሮፓ የታሪክ ፀሐፊዎች "የመሀከለኛው ዘመን ታሪክ መጨረሻና አዲሱ ታሪክ መጀመሪያ" ብለው ይጠሩታል።

ፅሑፎቼን አንብቦ ለሌሎች ወንድምና እህቶች ሼር በሚያደርግ ሰው ላይ ሁሉ የአላህ እዝነት ይስፈን