Get Mystery Box with random crypto!

Reyan Records

የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records R
የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records
የሰርጥ አድራሻ: @reyan_records
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 346

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2022-11-20 20:10:20
ይሄ አይደል ሰበቡ?
....በመሀላችን እየገባ አንዳችን ለአንዳችን ምን እንደሆን ያስረሳን...ልክ ደህና አላህን ፈሪ (የተባለውን) ሰው መላውን አጥቶ ረሀብ ሲቆላው ምግብ ሰጥቶ ጌታውን የነሳው:ጀነትን በብልጭልጯ ቀይሮት እንደማለት ነው ....!

በሌላ ጎን ዱንያ ተደፍታባቸው...ቤታቸው ጨለማ የሆኑትን በብርሀን የሚሞላ...አኼራንም በማስተካከል ሂደት ጉልህ ሚና የሚጫወት ብር
ሱብሀነላህ "የበሽታው መድሀኒት ራሱ በሽታው ነው! " ሚሉት ነገር ለገንዘብ ብቻ እስኪመስለኝ አጂብ

(Glamor)
50 viewsGlamor, 17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 07:36:20 ስሜት ከንጉሶች ባሮችን ያወጣል ትዕግስት ደግሞ ከባሮች ንጉሶችን ያወጣል።
               -- Al Ghazali --
16 viewsGlamor, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-19 21:37:36 #የኔ እይታ 22

ከአንድ አመት በፊት አንድ ጓደኛዬ በጣም ያስጨነቃት ጉዳይ እንዳለ እና ዱአ እንዳደርግላት ደውላ ነገረችኝ።እስከዛሬ የሚገጥማትን ነገር ካወራችኝ በኋላ ስለነበር ዱአ አርጊልኝ የምትለኝ ያኔ ሀጃዋን ሳትነግረኝ ስትቀር ግራ ተጋብቼ"እና ምን እንደሆንሽ ሳትነግሪኝ ነው እንዴ?"አልኳት ለመጀመሪያ ግዜ ሀጃዋን ከኔ መደበቋ አስገርሞኝ።
"ልቤ በጣም ተሰብሯል! እራሴን ጠልቼዋለሁ። እውነት የምትወጂኝ እና የምታስቢልኝ ከሆነ እስከዛሬ ካደረግሽልኝ በተለየ ሁኔታው ከልብሽ ዱአ አድርጊልኝ!"አለችኝ እያለቀሰች
"እሺ ግን ንገሪኝ ምን እንደሆንሽ እያስጨነቅሽኝ ነው"አልኳት እምባዬ ጉንጬ ላይ እየፈሰሰ(አንድ ነፍስ ከሆንን ቆይተናል)
"አቦ አታስጨንቂኝ በቃ አላህ ጋር ተጣልቼ ነው"አለችኝ ሁሌም አላህ ጋር ያለን ግንኙነት ሲበላሽ እንደዚህ ነው የምንባባለው።
"እሺ አብሽሪ አላህ ልብሽን ይጠግነው"አልኳት አላህን ማመፅ ያለውን ህመሞ እያሰብኩ።ከነገረችኝ ቀን በኋላ ለራሴ ወንጀል ተነስቼ የማላውቀውን በተከታታይ ለይል ሰላት እየሰገድኩ በእምባ ታጥቤ አላህ ከወንጀል እንዲያፀዳት እና ነውሯን እንዲሰትርላት ለመንኩት።
ከ 3 ወር በኋላ "ዱአሽ ደርሷል ከአላህ ያጣላኝን ወንጀል ካቆምኩ ወር አለፈኝ።አሁን አላህ ፊት ቁሜ ዱአ ማድረግ አልሳቀቅም!አላህ እንደማረኝ ነው የሚሰማኝ" አለችኝ።
"አላህ ባንቺ ልመና ምክንያት ነው የማርኳት ያለኝ ይመስል በደስታ ሰከርኩ።
ከአንድ ወር በኋላ መስጂድ ቀጥራኝ......የፍርሀት በሚመስል ድምፅ" ምን እንደምልሽ አላውቅም ግን ያንን ወንጀል በምሰራበት ሰአት አላህ ጋር ለካ ቅርብ ሁኜ ነበር። አሁን ከወንጀሉ ስርቅ እና እንደማረኝ ሳስብ አላህ ጋር የነበረኝ ጥብቅ ግንኙነት ጠፋ። እሰግዳለሁ፣ቁርአን አነባለሁ፣ ዱአ አደርጋለሁ...ግን ያኔ ማረኝ፣ነውሬን ሸሽግልኝ፣ከዚህ ወንጀል አውጣኝ እያልኩ በእምባ ታጥቤ ስለምነው ምንም እንኳን በወንጀል ብበሰብስም ከወንጀሌ ተፀፅቼ የማነባት የእንባ ጠብታ አላህ ጋር ታቃርበኝ ነበር"
"እና ወደ ወንጀሎ መልሳት ብዬ ደግሞ ለይል ሰላት ልስገድ?"አልኳት ብስጭት ብዬ
"አላውቅም ግን አላህን ከወንጀል አርቀኝ እያልኩ ያለቀስኩባቸው አመታት በጣም ደስ ይሉ ነበር። የአመታት ዱአዬ ውጤት አላህ ጋር የነበረኝን ቅርበት ያሳጣኝ መሰለኝ!"ስትለኝ ግራ ተጋብቼ "ሰው እንዴት ከወንጀል ከነፃባቸው ግዚያቶች ይልቅ ወንጀል ውስጥ የነበረበት ግዜ አላህ ጋር የተሻለ ሊሆንለት ይችላል?"አልኳት በመገረም
"አየሽ ላንቺ ዱአ አድርጊልኝ ብዬ የነገርኩሽ ለአመታት ብቻዬን እያለቀስኩ አላህን መሀርታ ከጠየቅኩ በኋላ ነው። ከነበርኩበት ወንጀል መውጣት ከብዶኝ ላንቺ ከነገርኩሽ ከትንሽ ግዜ በኋላ የአመታት ልመናዬ እና ያንቺ ዱአ ተጨምሮ ነው መሰል ከነበርኩበት ወንጀል ተላቀቅኩ። ከዛ በኋላ አላህን እያለቀሱ መለመን፣ በወንጀል ስብር ብሎ ከአለማት ጌታ ፊት በሀፍረት መቆም ሳቆም ልቤ ደነዘዘ። ከሰወች ሁሉ ወንጀኛ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ያረገኝ የነበረው ወንጀል ከኔ ሲርቅ እራሴን እንደ ጥሩ የአላህ ባሪያ እያሰብኩ ከተውበት እና ቅጣቱን ፈርቶ ከማልቀስ ተዘናጋሁ። ወደነበርኩበት ወንጀል መመለስ ባልፈልግም ያኔ ተሰብሮ ከጌታው ደጅ የማይጠፋውን ለተውበት የተገራ ልቤን ማጣቴ ግን በጣም አሳዝኖኛል" አለችኝ። ምን እንደምላት ግራ ገብቶኝ ዝም አልኩ።

ከወዱዱ ጌታ ከአንተ ለመቃረብ፣
በማያልቅ ፍቅርህ ዘላለም ለመኖር፣
ልክ እንደ መላዕክት አንተን አለማመፅ፣
ልክ እንደ አቢዶች ለይሉን ሀይ ማድረግ
ብቸኛው ጦሪቃ ይመስለኝ ነበረ።
ዛሬ ነው የገባኝ፤ ድንበርህን አልፎ፣
በወንጀል በስብሶ፣ ሰላም ከሞላበት
ከመስጂዱ ወለል በአፉ ተደፍቶ፣
ወንጀሌ ከበደኝ፣አንተን ማመፅ በቃኝ!
ነውሬን ሸሽግልኝ፣ ለሰው አታጋልጠኝ!
ብሎ ከአንጀት ማልቀስ፣በፀፀት መገረፍ፤
ወደ አንተ እንደሚያቀርብ፣ሰደቃ እንደመስጠት፤

ይሄ ስሜት ተሰምቷችሁ የምታውቁ ትኖሩ ይሆን?

rehima Hussein
36 viewsGlamor, 18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-19 14:53:17 እንባችንን ዉጠን፣ ዉጠን የት አደረስነዉ ...? በእለት እየፈላ ሁለመናችንን የገሻሸረዉ እሱስ ቢሆን...⁈
47 viewsGlamor, 11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-18 16:32:40 (ነሱሀ አወል)
.....

〖አንዳንድ እውነታወችን ማመን ይሳነኝ ይዟል...በእርግጥ ሰወች ሊሆን ማይፈልጉት ሆኖ ሲገኝ ባለማመን እራሳቸውን ይጋርዱታል ያን እያወቅሁ ሳለሁ...

በድንገት ከህይወቴ ስለተሰረዙ ልቦች እውነትነት ለመቀበል ልቤን ይበርደኛል...ነገአቸውን፣ የስኬት ማማቸውን ልቋደስ የዛሬ ችግራቸውን ስካፈላቸው የነበሩ ልቦች ርቀው ሄደዋል...ምናልባትም ላይመለሱ ምናልባትም ሌላ የስሜታቸው አጃቢ የውድቀታቸው አድማጭ አግኝተው...ብቻ ቁም ነገሩ አለመኖራቸው ላይ ነው።

እውነትን መቀበል የሚመረኝ ሰው አይደለሁም ። ነገር ግን ስንብት የሌለው መለያየት ሲሆን እውነታን ልክድ ዳር ዳር ይለኛል። ልቤን በይመጣሉ እሸነግለዋለሁ። ትላንት ላይ ትዝታ አለ መልካም መአዛ ያለው ትዝታ... የማይበርድ ትዝታ...የመልካም ልቦች ፋና ያለበት ትላንት...!

አውቃለሁ እኮ...!
አንድ ሲሄድ ሌላ ይተካል የሚተካው ግን ሌላ አካል ሌላ ስብእና የተሻለ አሊያ ያነሰ ግን የአንድን ሰው ልዩ ነገር የአንዱ ማማር ሊተካው አይችልማ...ይሄም እውነታ ነው ልቤ እያወቀው የሚክደው...እና እስቲ ለማገገም የምንጠቀማቸው ጤናአዳም እንተውና ቅድሚያ እውነታውን እንቀበል ሌላው እዳው ገብስ ነው።〗

ትለኝ ነበር ከህይወቷ የተነኑ ነፍሶች እያንገበገቧት። አሁን ላይ እሷም የለችም እውነታን እንድቀበል ተዋናይ ሆና ያሳየችኝ ፊልም እንደሁ እንጃ!...የለችም!...እውነታን በመቀበል ሂደት ውስጥ...!
12 viewsGlamor, 13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-18 07:04:46 ልጅ ያለ ሰአቱ ከትምህርት ቤቶ ይመለስና መምህሬ ይህን ደብዳቤ ለእናትህ ብቻ እንድትሰጥ ነግሮኛል አላት እናትም ደብዳቤውን ተቀብላ ካየችው በኋላ በእንባ ታጅባ  ጮክ ብላ ታነብ ጀመረ ፦ልጅሽ ብልህና በጣም ጎበዝ ነው ይህ ትምርት ቤት ለእሱ አይመጥነውም እሱን ለማስተማር በቂና ጥሩ አስተማሪዎች የሉንም  ስለዚህ እባክሽን አንቺው  ራስሽ በቤት ውስጥ አተስተምሪው ይላል አለችው።

ከአመታት ቡሀላ እናት ሞተች ይሄ ልጅ አድጎ የክፍለ ዘመኑን ታላቅ ፈጠራ የሆነውን አንፖልን ፈጠረ አንድ ቀን ቤት ውስጥ እቃዎችን  ሲያስተካክል በልጅነቱ ከአስተማሪው  ለእናቱ የተላከውን ደብዳቤ አገኘ በትዝታ ወደ ኋላ ተመልሶም እናቱን እያሰበ ማንበብ ጀመረ፦  ልጅዎ የአይምሮ ህመምተኛ  ነው ከእንግዲህ በኛ ትምህር ቤት ውስጥ እንዲማር አንፈቅድለትም ተባሯል ይላል።ወዲያውኑ የእናቱ ብልሀት ገባው። በማስታወሻ ደብተሩ ላይ ቶማስ አልቫ ኤድሰን የአምሮ በሽተኛ የነበረ ጀግና እናቱ ግን ወደ ክፍለ ዘመኑ ምጡቅ የአእምሮ ባለቤትነት የቀየረችው ጀግና ልጅ ሲል  ፃፈበት።

ምርጦቼ  እኛም ትውልዱ አይረባም የሚሉንን አሳፍረን ለሀገር መልካም ታሪክ እንፅፍ ዘንድ የጎበጠውን የሚያቀኑ የተሰበረውን የሚጠግኑ መንገድ ከፋቾችን በዙሪያችን ያብዛልን።

https://t.me/Reyan_Records
24 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 23:30:40
ሞት ሆይ...
""""""""""""""""""""""""""""

ቀን ፊቱን አዙሮ...
ህይወቴ ደብዝዞ ፣ሰላሜ ሲጓደል
በውጣ ውረዴ፣ ችግር ሲደላደል

በእጄ የያዝኩት፣ ከድቶኝ ሲያመልጠኝ
አሜኬላው በዝቶ፣ እንቅፋት ሲግጠኝ
በሰቀቀን ኑሮ፣ ሰርክ ስውተረተር
የደስታዬ ልኬት፣ በሀዘን ሲመተር

ድንገት

ሞት ሆይ የት ነህ?..... ካልኩህ
በክብር ጠርቼ፣ ለአፍታ እየጠየኩህ

በመቃተት ሆኜ...
መምጫህን ናፍቄ፣ የት ነህ? ብልህ እንኳን
"እዚህ ነኝ!! አትበለኝ፣ እለፍ የኔን ድንኳን

ግዴለም አትስማኝ...
ሞት ሆይ ከኔ እለፍ፣ ስጠራህ አትምጣ
ከተስፋ ማህፀን...
ነፍሴ ሰላም ትውለድ፣ በትዕግስት አምጣ።

/ልጅ ወርቅነህ.. /
  
   
62 viewsGlamor, 20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 21:05:08 ሙሉ ነገር እየጎደለ ሲሔድ የበፊት ክብሩን፣ ጥንካሬውን አጥቶ አቅመ አናሳ ይሆናል!!!
62 viewsGlamor, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 16:55:46 አንዳንዶች እውነታን ቆፍጠን ብሎ መናገር ትህትና ቢስነት ይመስላቸዋል!
49 viewsGlamor, 13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 06:06:44 "ሞት አስፈሪ እጆቹን ሲጭን ሁሉም ነገር ለዛውን ያጣል"
Muawiya
37 viewsGlamor, 03:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ