ሞት ሆይ...
""""""""""""""""""""""""""""
ቀን ፊቱን አዙሮ...
ህይወቴ ደብዝዞ ፣ሰላሜ ሲጓደል
በውጣ ውረዴ፣ ችግር ሲደላደል
፧
በእጄ የያዝኩት፣ ከድቶኝ ሲያመልጠኝ
አሜኬላው በዝቶ፣ እንቅፋት ሲግጠኝ
በሰቀቀን ኑሮ፣ ሰርክ ስውተረተር
የደስታዬ ልኬት፣ በሀዘን ሲመተር
፧
ድንገት
፧
ሞት ሆይ የት ነህ?..... ካልኩህ
በክብር ጠርቼ፣ ለአፍታ እየጠየኩህ
፧
በመቃተት ሆኜ...
መምጫህን ናፍቄ፣ የት ነህ? ብልህ እንኳን
"እዚህ ነኝ!! አትበለኝ፣ እለፍ የኔን ድንኳን
፧
ግዴለም አትስማኝ...
ሞት ሆይ ከኔ እለፍ፣ ስጠራህ አትምጣ
ከተስፋ ማህፀን...
ነፍሴ ሰላም ትውለድ፣ በትዕግስት አምጣ።
/ልጅ ወርቅነህ.. /