Get Mystery Box with random crypto!

ልጅ ያለ ሰአቱ ከትምህርት ቤቶ ይመለስና መምህሬ ይህን ደብዳቤ ለእናትህ ብቻ እንድትሰጥ ነግሮኛል | Reyan Records

ልጅ ያለ ሰአቱ ከትምህርት ቤቶ ይመለስና መምህሬ ይህን ደብዳቤ ለእናትህ ብቻ እንድትሰጥ ነግሮኛል አላት እናትም ደብዳቤውን ተቀብላ ካየችው በኋላ በእንባ ታጅባ  ጮክ ብላ ታነብ ጀመረ ፦ልጅሽ ብልህና በጣም ጎበዝ ነው ይህ ትምርት ቤት ለእሱ አይመጥነውም እሱን ለማስተማር በቂና ጥሩ አስተማሪዎች የሉንም  ስለዚህ እባክሽን አንቺው  ራስሽ በቤት ውስጥ አተስተምሪው ይላል አለችው።

ከአመታት ቡሀላ እናት ሞተች ይሄ ልጅ አድጎ የክፍለ ዘመኑን ታላቅ ፈጠራ የሆነውን አንፖልን ፈጠረ አንድ ቀን ቤት ውስጥ እቃዎችን  ሲያስተካክል በልጅነቱ ከአስተማሪው  ለእናቱ የተላከውን ደብዳቤ አገኘ በትዝታ ወደ ኋላ ተመልሶም እናቱን እያሰበ ማንበብ ጀመረ፦  ልጅዎ የአይምሮ ህመምተኛ  ነው ከእንግዲህ በኛ ትምህር ቤት ውስጥ እንዲማር አንፈቅድለትም ተባሯል ይላል።ወዲያውኑ የእናቱ ብልሀት ገባው። በማስታወሻ ደብተሩ ላይ ቶማስ አልቫ ኤድሰን የአምሮ በሽተኛ የነበረ ጀግና እናቱ ግን ወደ ክፍለ ዘመኑ ምጡቅ የአእምሮ ባለቤትነት የቀየረችው ጀግና ልጅ ሲል  ፃፈበት።

ምርጦቼ  እኛም ትውልዱ አይረባም የሚሉንን አሳፍረን ለሀገር መልካም ታሪክ እንፅፍ ዘንድ የጎበጠውን የሚያቀኑ የተሰበረውን የሚጠግኑ መንገድ ከፋቾችን በዙሪያችን ያብዛልን።

https://t.me/Reyan_Records