Get Mystery Box with random crypto!

(ነሱሀ አወል) ..... 〖አንዳንድ እውነታወችን ማመን ይሳነኝ ይዟል...በእርግጥ ሰወች ሊሆን | Reyan Records

(ነሱሀ አወል)
.....

〖አንዳንድ እውነታወችን ማመን ይሳነኝ ይዟል...በእርግጥ ሰወች ሊሆን ማይፈልጉት ሆኖ ሲገኝ ባለማመን እራሳቸውን ይጋርዱታል ያን እያወቅሁ ሳለሁ...

በድንገት ከህይወቴ ስለተሰረዙ ልቦች እውነትነት ለመቀበል ልቤን ይበርደኛል...ነገአቸውን፣ የስኬት ማማቸውን ልቋደስ የዛሬ ችግራቸውን ስካፈላቸው የነበሩ ልቦች ርቀው ሄደዋል...ምናልባትም ላይመለሱ ምናልባትም ሌላ የስሜታቸው አጃቢ የውድቀታቸው አድማጭ አግኝተው...ብቻ ቁም ነገሩ አለመኖራቸው ላይ ነው።

እውነትን መቀበል የሚመረኝ ሰው አይደለሁም ። ነገር ግን ስንብት የሌለው መለያየት ሲሆን እውነታን ልክድ ዳር ዳር ይለኛል። ልቤን በይመጣሉ እሸነግለዋለሁ። ትላንት ላይ ትዝታ አለ መልካም መአዛ ያለው ትዝታ... የማይበርድ ትዝታ...የመልካም ልቦች ፋና ያለበት ትላንት...!

አውቃለሁ እኮ...!
አንድ ሲሄድ ሌላ ይተካል የሚተካው ግን ሌላ አካል ሌላ ስብእና የተሻለ አሊያ ያነሰ ግን የአንድን ሰው ልዩ ነገር የአንዱ ማማር ሊተካው አይችልማ...ይሄም እውነታ ነው ልቤ እያወቀው የሚክደው...እና እስቲ ለማገገም የምንጠቀማቸው ጤናአዳም እንተውና ቅድሚያ እውነታውን እንቀበል ሌላው እዳው ገብስ ነው።〗

ትለኝ ነበር ከህይወቷ የተነኑ ነፍሶች እያንገበገቧት። አሁን ላይ እሷም የለችም እውነታን እንድቀበል ተዋናይ ሆና ያሳየችኝ ፊልም እንደሁ እንጃ!...የለችም!...እውነታን በመቀበል ሂደት ውስጥ...!