Get Mystery Box with random crypto!

#የኔ እይታ 22 ከአንድ አመት በፊት አንድ ጓደኛዬ በጣም ያስጨነቃት ጉዳይ እንዳለ እና ዱአ እን | Reyan Records

#የኔ እይታ 22

ከአንድ አመት በፊት አንድ ጓደኛዬ በጣም ያስጨነቃት ጉዳይ እንዳለ እና ዱአ እንዳደርግላት ደውላ ነገረችኝ።እስከዛሬ የሚገጥማትን ነገር ካወራችኝ በኋላ ስለነበር ዱአ አርጊልኝ የምትለኝ ያኔ ሀጃዋን ሳትነግረኝ ስትቀር ግራ ተጋብቼ"እና ምን እንደሆንሽ ሳትነግሪኝ ነው እንዴ?"አልኳት ለመጀመሪያ ግዜ ሀጃዋን ከኔ መደበቋ አስገርሞኝ።
"ልቤ በጣም ተሰብሯል! እራሴን ጠልቼዋለሁ። እውነት የምትወጂኝ እና የምታስቢልኝ ከሆነ እስከዛሬ ካደረግሽልኝ በተለየ ሁኔታው ከልብሽ ዱአ አድርጊልኝ!"አለችኝ እያለቀሰች
"እሺ ግን ንገሪኝ ምን እንደሆንሽ እያስጨነቅሽኝ ነው"አልኳት እምባዬ ጉንጬ ላይ እየፈሰሰ(አንድ ነፍስ ከሆንን ቆይተናል)
"አቦ አታስጨንቂኝ በቃ አላህ ጋር ተጣልቼ ነው"አለችኝ ሁሌም አላህ ጋር ያለን ግንኙነት ሲበላሽ እንደዚህ ነው የምንባባለው።
"እሺ አብሽሪ አላህ ልብሽን ይጠግነው"አልኳት አላህን ማመፅ ያለውን ህመሞ እያሰብኩ።ከነገረችኝ ቀን በኋላ ለራሴ ወንጀል ተነስቼ የማላውቀውን በተከታታይ ለይል ሰላት እየሰገድኩ በእምባ ታጥቤ አላህ ከወንጀል እንዲያፀዳት እና ነውሯን እንዲሰትርላት ለመንኩት።
ከ 3 ወር በኋላ "ዱአሽ ደርሷል ከአላህ ያጣላኝን ወንጀል ካቆምኩ ወር አለፈኝ።አሁን አላህ ፊት ቁሜ ዱአ ማድረግ አልሳቀቅም!አላህ እንደማረኝ ነው የሚሰማኝ" አለችኝ።
"አላህ ባንቺ ልመና ምክንያት ነው የማርኳት ያለኝ ይመስል በደስታ ሰከርኩ።
ከአንድ ወር በኋላ መስጂድ ቀጥራኝ......የፍርሀት በሚመስል ድምፅ" ምን እንደምልሽ አላውቅም ግን ያንን ወንጀል በምሰራበት ሰአት አላህ ጋር ለካ ቅርብ ሁኜ ነበር። አሁን ከወንጀሉ ስርቅ እና እንደማረኝ ሳስብ አላህ ጋር የነበረኝ ጥብቅ ግንኙነት ጠፋ። እሰግዳለሁ፣ቁርአን አነባለሁ፣ ዱአ አደርጋለሁ...ግን ያኔ ማረኝ፣ነውሬን ሸሽግልኝ፣ከዚህ ወንጀል አውጣኝ እያልኩ በእምባ ታጥቤ ስለምነው ምንም እንኳን በወንጀል ብበሰብስም ከወንጀሌ ተፀፅቼ የማነባት የእንባ ጠብታ አላህ ጋር ታቃርበኝ ነበር"
"እና ወደ ወንጀሎ መልሳት ብዬ ደግሞ ለይል ሰላት ልስገድ?"አልኳት ብስጭት ብዬ
"አላውቅም ግን አላህን ከወንጀል አርቀኝ እያልኩ ያለቀስኩባቸው አመታት በጣም ደስ ይሉ ነበር። የአመታት ዱአዬ ውጤት አላህ ጋር የነበረኝን ቅርበት ያሳጣኝ መሰለኝ!"ስትለኝ ግራ ተጋብቼ "ሰው እንዴት ከወንጀል ከነፃባቸው ግዚያቶች ይልቅ ወንጀል ውስጥ የነበረበት ግዜ አላህ ጋር የተሻለ ሊሆንለት ይችላል?"አልኳት በመገረም
"አየሽ ላንቺ ዱአ አድርጊልኝ ብዬ የነገርኩሽ ለአመታት ብቻዬን እያለቀስኩ አላህን መሀርታ ከጠየቅኩ በኋላ ነው። ከነበርኩበት ወንጀል መውጣት ከብዶኝ ላንቺ ከነገርኩሽ ከትንሽ ግዜ በኋላ የአመታት ልመናዬ እና ያንቺ ዱአ ተጨምሮ ነው መሰል ከነበርኩበት ወንጀል ተላቀቅኩ። ከዛ በኋላ አላህን እያለቀሱ መለመን፣ በወንጀል ስብር ብሎ ከአለማት ጌታ ፊት በሀፍረት መቆም ሳቆም ልቤ ደነዘዘ። ከሰወች ሁሉ ወንጀኛ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ያረገኝ የነበረው ወንጀል ከኔ ሲርቅ እራሴን እንደ ጥሩ የአላህ ባሪያ እያሰብኩ ከተውበት እና ቅጣቱን ፈርቶ ከማልቀስ ተዘናጋሁ። ወደነበርኩበት ወንጀል መመለስ ባልፈልግም ያኔ ተሰብሮ ከጌታው ደጅ የማይጠፋውን ለተውበት የተገራ ልቤን ማጣቴ ግን በጣም አሳዝኖኛል" አለችኝ። ምን እንደምላት ግራ ገብቶኝ ዝም አልኩ።

ከወዱዱ ጌታ ከአንተ ለመቃረብ፣
በማያልቅ ፍቅርህ ዘላለም ለመኖር፣
ልክ እንደ መላዕክት አንተን አለማመፅ፣
ልክ እንደ አቢዶች ለይሉን ሀይ ማድረግ
ብቸኛው ጦሪቃ ይመስለኝ ነበረ።
ዛሬ ነው የገባኝ፤ ድንበርህን አልፎ፣
በወንጀል በስብሶ፣ ሰላም ከሞላበት
ከመስጂዱ ወለል በአፉ ተደፍቶ፣
ወንጀሌ ከበደኝ፣አንተን ማመፅ በቃኝ!
ነውሬን ሸሽግልኝ፣ ለሰው አታጋልጠኝ!
ብሎ ከአንጀት ማልቀስ፣በፀፀት መገረፍ፤
ወደ አንተ እንደሚያቀርብ፣ሰደቃ እንደመስጠት፤

ይሄ ስሜት ተሰምቷችሁ የምታውቁ ትኖሩ ይሆን?

rehima Hussein