Get Mystery Box with random crypto!

Reyan Records

የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records R
የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records
የሰርጥ አድራሻ: @reyan_records
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 346

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 19

2022-10-06 22:45:14 እያባበሏት እያባበሏት
<< አታልቅሺ! >> ብለው አድፍጠው ገደሏት
ስታልቅስ ሲያስቆሟት
ሳግ ጠንቶ አመማት
በሳግ አነባች ተነፋረቀች
እንባ ተለያት እንባ ናፈቀች።

እናልቅስ? አልኳት
ቀልድ መሰሏት
ሳቀች በእንባዋ
እያዘንኩላት በሁኔታዋ
ዳግም ጠየቅኳት
እናንባ? አልኳት

እንዳልፈለገ እንዳላወቀ << በሽተኛ! ንቅል >>
<< እብድ ነህ! >> አለች << አበድኩ! >> እንዳትል!

ተቆጣች ብዬ መች እኔ ፈራሁ
እናልቅስ? እያልኩ ሀዘኗን ጠራሁ።
ፊቷ ተቆጣ አይኗ አበጠ
ልቧ በእልህ እንባ አማጠ።
ዱብ…ዱብ… አለ ታምቆ የፈላ
ስድ አፅናኝ ቃል መንታ ዘለላ።

የምር እንባዋ እስኪመጣ
ዝም……መርዟ ሲወጣ
እስክትጨርስ እስኪበቃት
አለቀስቆምኳት!

አለቀሰች!
አነባች!
ያፈነችው ተነፈሰ
ሲቀላት ቃሏ ደረሰ።
<< ኡፍ…>> አለች በረዥሙ። ለመጀመርያ ጊዜ ያለቀሰች መሰላት።
<< ለምንድን ነው ግን አንተ አልቅሺ ብለህ ሆዴን ያባባኸው? >>
እያባበልኩ እንዳልገልሽ
አሳምሜ ከህመምሽ ላገዝፍሽ
ፈልጌ!
<< እሺ ምን ተጠቀምክ? >>
እኔንጃ! ለመጠቀም ተብሎ ሰው ከእንባው እንዲታረቅ ይደረጋል? መጠየቅ ልምዴ ጠየቅኳት።
<< ግራ ነገር ነህ! የማትገባ! >>
ለዚህ አይደል ስድ አፅናኞች የማይጨማለቁብኝ!
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
19 viewsGlamor, 19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 22:35:53 ቅኔው ከገባህ የሚከተለውን ንግግር መቼም አትረሳውም...

<<የኛ ችግር.... በነብዩ {ሰ.ዐ.ወ} ጊዜ የነበሩ ሰዎች "ጀነትን ይፈልጉ" ነበር!... አሁን ላይ ያሉ ሙስሊሞች ግን "ጀነትንም ጭምር ይፈልጋሉ"... ልዩነቱን ልብ በል>>

-ሙሀመድ ሆብሎስ
53 viewsGlamor, 19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 06:50:00 ━━━━✦✗✦━━━━
ይድረስ ለረቢዑ

ረያን አቡዲ
━━━━✦✗✦━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
@Mejnun_Leyla_poem
9 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 19:50:11 እርሱ የሩሔ አስገኚ...
(ነጃት ሀሰን)
:
የህይዎት ትንፋሽ ገፈታትሮ እዚህ ሳያቆመኝ በፊት...አክብጄ ለልቤ የነገርኳቸው "እውነት"ኣዎች አሁን ላይ ስለቆመችው እኔዋ የጨመሩት ምን ነው? እላለሁ።

ልቤ እስክትበር እየሮጥኩ ከዘበኛው ቀድሜ የትምህርት ቤታችን በር ላይ የተገኘሁባቸው ወቅቶች... ከሌላው ተማሪ ያከሉልኝ ነገር አለ?
ላይብረሪ የተወዘፍኩባቸው የመዓት ለሊቶች የሩሔን ገፅ ለማንፃት መች አገዙኝ? ኧረ አካሌንስ አሳርፍበት ጎጆን እፈጥርባቸው ዘንድ መች በቁ?

ትናንቴን እሱን ብጠራበት 'ኑሮ' እላለሁ... ለይሌን በስሙ ብጎህህ... ጠዋቴን በስሙ ብቀድስ... ሩጫዬን በስሙ ብሞሽር... ልፋቴን በስሙ ብጀቡን..."ኑሮ" እላለሁ...በኑሮ መዓት ተከብቤ!!


ኹኖ ኹኖ...እርሱ አስኹኖኛል...እርሱ ትንፋሼን አብቅሏል...እርሱ አሁንን አልብሶኛል...እርሱ አለኝታዬ...እርሱ የዘላለም ስጦታዬን ያለልፋቴ የጀባኝ....እርሱ የረሱል ዑመት ያደረገኝ... እርሱ...ሁወ...አሏህ!!
:
29 viewsGlamor, 16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 10:38:46 ማር መምረርን ያዘ ወተቱም ጠቆረ
አይዘንብ ወይ አይፈካ፣ ሰማይ ዳምኖ ቀረ
የሚል እንጉርጉሮን፣ ብቻ እያነበነብን
መኖርን አንመርጥም!
እንገጥማለን እንጂ፣ ወቅቱ እስከሚገጥም
እንገጥማለን እንጂ፣ ግጣሙ እስኪገጥም

@Mejnun_Leyla_poem
48 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 21:27:14 አድምጪኝማ ሀያቲ…
ተያቸው እነሱን… ያውሩ፣ ያሽካኩ፣ ያሸሙሩ… ምንም ይበሉ ተያቸው፣ የነሱ ትችት ኢላሂን የሚያስደስተውን ከማድረግ አያዘናጋሽማ!
እናም አስታውሺ፣ ከጀርባሽ ባነሱሽ ቁጥር ወንጀልሽን አንስቶ ወንጀላቸው ላይ የሚጨምር ጌታ እንዳለሽ አስታውሺ…ይህ ሁሉ ያልፋል…
.
.
ብቻ ታገሺ


መድ

67 viewsGlamor, 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 19:40:56 #ይሁን_ብቻ_ነይ!

እንዳይጠፋሽ መልኬ፡
እንድታይ አብርቼ፣
ጸዳልን ለብሼ ፡ ብርሃን ሸምቼ፣
እጠብቅሻለው፡
ከመንገድ መብራት ስር፡
አትስጊ፡ አይገልጥም፡
የልብ ላይ ቁስል!!!

አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)
71 viewsGlamor, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 22:02:54 (ነሱሀ አወል)
...

አታልቅሺ
ከኑሮሽ ላይ ለተነነ፣
ለደህና እንጂ
አላህ ያለው ሁሉ የሆነ፣
መቸ ጌታሽ...!
ሚበጅሽን ካንቺ ይነጥቃል፣
ካንቺ በላይ ላንቺ ገሩን እሱ ያውቃል።
አብሽሪ!


〖 ከችግር ጋር ምቾት አለ〗
79 viewsGlamor, 19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 06:18:16
በወዶ ዘማች የተምሳሌታዊ ወጣት እንቅስቃሴ የጥበብ ክፍል የተቋቋመው አንጀሻ አርት ግሩፕ አባል ለመሆን የድምፅ ተሰጥኦ ያላችሁና የስብስቡ አባል መሆን ለምትፈልጉ የተዘጋጀ ልዩ ውድድር!

~ በቴሌግራም ከ 2 ደቂቃ ያላነሱ ሶስት የነሺዳ ሙከራዎችን ይላኩ!
~10 ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች ይመረጣሉ!

በመጪዎቹ 3 ቀናት ውስጥ ይላኩ!

T.me/Temsaletawi_Wetat
#ወዶ_ዘማች
#ተምሳሌታዊ_ወጣት
@Reyan_meme_and_islamic_post
14 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 03:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 22:44:42 ስለዳሩል አርቀም ኢስላማዊ ጀመአ ምን ያውቃሉ ?
ዳሩል አርቀም ጀመአ የተለያዩ ኸይር ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ጀመአ ነው ።ለአብነትም
*ለረመዳን አስቤዛ
*ለአረፋ የቲም ህጻናትን ልብስ ማልበስ
*ኡዱህያ ለተቸገሩ ሰዎች መስጠት/ማድረስ
እኒህን ስራዎች ሲሰራ ቆይቷል ።አሁን ደግሞ የአንድ አቅመ ደካማን ቤት ለማሳደስ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል ። እርሶም የዚህ ኸይር ስራ ተካይ ይሆኑ ዘንድ በአሏህ ስም እንጠይቃለን



የሚነዩበትን መንገድ አመቻችተናል ።


"ተማሪ ነኝ ብር የለኝም "
telegram ከምትገቡበት ቀንሳችሁ

"እኔ በግሌ ምረዳው ሰው አለ "

ወንድሜ እህቴ ሰደቃኮ ገንዘብን አታጎልም

የአሏህ ባሮች ሆይ ለምን ያለንን ለመስጠት እንሰስታለን ። አንድ ብርም ትሁን ለአኺራችን ትተቅመናለች።
እርስዎ ለመስጠት ፈቃደኛ ይሁኑ እንጂ እኛ መንገዱን አመቻችተንልዎታል።

*በካርድ 0913219422 ላይ ካርድ በመላክ ያለዎትን ይነይቱ

* በኢትዩጲያ ንግድ ባንክ 1000451773759
45 viewsGlamor, 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ