Get Mystery Box with random crypto!

ቢሻራ ... ከማዶ ባሻገር የሰገዱላት እሳት ወደመች ዝንተአለም የፋርስ ሃያልነት መገለጫ መንደ | Reyan Records

ቢሻራ ...

ከማዶ ባሻገር የሰገዱላት እሳት ወደመች ዝንተአለም የፋርስ ሃያልነት መገለጫ መንደዱ ምን ይሁን ሚስጥሩ? 
በውነቱ ያ እሳት ተአምር የያዘ  ሚስጥራዊ ማገዶ ነበረው በዛች ሚስጥር መጁሳነት ገነነ ፅልመትን የያዘ ብርሃን አንድ ከተማ ሙሉ እንዳላበራ እስትንፋሱ ቆመ ።
አላሁ አክበር  !!
በርግጥም ያቺ እሳት የጠፋችው   በመሲህ ቢሻራ አህመድ ነው
ረቢእ 12 በጅምሁር ሙአሪኾች በማይለቁ ብራናወች በሙስሊሞች ልቦና ተነቅሳ ቀረች .

የተቀበረች እንስት የቢሻራውን ሀያልነት ትመስክር  !!

የበዳዮች ነፍስ የጣኦት አምላኪያን አንደበት  ስለቢሻራው ውድነት ትናገር! 
ኡመር ቢን ኸጣብ ይመስክር  ፊታቸው የከበረው ኢማም አሊይ  ስለቢሻራው ልእልና ይናገር

በውልደታቸው ዳግም ምድር ተወለደ የኢስራኤላዊያን ሴራ ተጋለጠ
አላሁ አክበር

https://t.me/Reyan_Records