Get Mystery Box with random crypto!

የትራፊክ ፖሊሱ አንድ የትራፊክ ፖሊስ ሥራውን ከለቀቀ በኋላ በአንድ መስጂድ በኢማምነት ማገልገል | Reyan Records

የትራፊክ ፖሊሱ

አንድ የትራፊክ ፖሊስ ሥራውን ከለቀቀ በኋላ በአንድ መስጂድ በኢማምነት ማገልገል ጀመረ አሉ። በመጀመሪያው ቀን ደዕዋውም በሚከተለው መልኩ ደዕዋ አደረገላቸው.. .
...
~ ወደ አኺራ የምታደርጉት ጉዞ ቀላል እንዳይመስላችሁ ረጅም፣ አድካሚ እና ውጣውረድ የበዛበት መሆኑን ተረዱ።

~ ከመንቀሳቀሳችሁ በፊት ሁለመናችሁን ፈትሹ፣ ትክክለኛ ዕውቀትና መረጃ ይኑራችሁ፤ ወዴት እንደምትንቀሳቀሱ እወቁ፤

~ ጥሩ ስሜት ላይ ሁኑ፣ ትኩረት አይለያችሁ፣ ውስጣችሁን ከአልባሌ ነገሮች አፅዱ፤

~ በእንቅስቃሴያችሁ ጊዜ ሁሉ የተቅዋ ቀበቶ እሠሩ፣ በፍፁም እንዳትዘናጉ፤

~ በፍጥነታችሁ ምልክቶችን ተከተሉ፤ ከልክ በላይ መፍጠንም ሆነ አላስፈላጊ በሆነ መልኩ መዘግየት አደጋ አለው፤

~ ጥፋት አታብዙ፣ ሁሌም ከስህተታችሁ ተማሩ፣

~ ህግ ያከበራችሁ እንደሆነ አትፍሩ ፤ ቀኛችሁን በመያዝ በመንገዱ ላይ ቀጥ ብላችሁ ሂዱ፤

~ በአላህ ፍራቻና እዝነቱን ክጀላ መካከል ሁኑ። ሚዛናችሁን ጠብቁ፤

~ በመንገዱ ላይ ሥርዓት ይኑራችሁ፤ ትከበሩ ዘንድ ሌሎችን አክብሩ፤

~ ሶላት የሚባሉ የኃይል ማደያ ጣቢያዎች አሉ፤ ከደከማችሁ ወደነርሱ ጎራ በሉ፣

~ ራስወዳድ አትሁኑ የወደቀን አንሱ፣ የደከመውን አግዙ።

~ ሁሌም ሁለቱን የመመሪያ መፅሐፎች አጥብቃችሁ ተከተሉ፣ ህግን አትተላለፉ፤
.
ይህን በሚገባ የተገበራችሁ እንደሆነ ሲራጥን በከፍተኛ ፍጥነት የመሻገር ዕድላችሁ ከፍ ይላል ...። ካሰባሁበትም በሰላምና በስኬት ትደርሳላችሁ።
.
መልካም ወደ አኺራ የሚደረግ ጉዞ ይሁንላችሁ።
.
ሁሉም አላህ ባገራለት መልኩ ያስተምር ለማለት ያህል ነው

@Reyan_Records