Get Mystery Box with random crypto!

< ' የአዕምሮ ባርነት ሲሉ ምን ለማለት ነው። በየትኛው መንገድ ነው በአእምሮ ባርነት ውስጥ የተዘ | Reyan Records

< " የአዕምሮ ባርነት ሲሉ ምን ለማለት ነው። በየትኛው መንገድ ነው በአእምሮ ባርነት ውስጥ የተዘፈቅነው? >

<< " ይህን በቀላሉ ለመረዳት " ሴት" ን መመልከት ትችላለህ። ሴት በአእምሮ ባርነት ከሚሰቃዩት መሀል ግንባር ቀደሟ ናት። ቅጥ ያጣው የዘመናዊ አስተሳሰብ ነፃነት ከየትኛውም ህብረተሰብ በላይ የጎዳው ሴትን ነው። በየትኛውም ዘመን ሴት ታፍራና ተከብራ የምትኖረው የእምነት መፅሀፎች ላይ እና እምነታቸውን በትክክል በሚተገብሩ አማኞች ህሊና ውስጥ ብቻ ነው። በዘመናችን ሴቶች መኖር የሚፈልጉት በሰዎች አስተሳሰብና በየዘመኑ በሚሰጣቸው ፍቺ እንጂ በእምነታቸው መመርያና ፍቺ አይደለም። ይህን ቅድሚያ እንዳያስተውሉ አዕምሯቸው በቁስ ጥገኛ እንዲሆን ተደርጓል። እምነት የሌላቸው ሰዎች በግልፅ እምነት የለንም ሲሉ ይኮነናሉ ነገር ግን አማኝ ነን የሚሉ ሰዎች ከእምነት መመርያቸው ውጪ ሲሆኑ እምነታቸውን እየተቃወሙና መመርያው ትክክል አይደለም እያሉ እንደሆነ አያስተውሉም። የአእምሮ ባርነት ውስጥ እንዳለን ለመገንዘብ ሴትን የወሲብ ምልክት ማድረጋችን መመልከት እንችላለን። አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ሲመለከት ከሰውነት አካላቶቹ በሙሉ ቀድሞ ፈጣን ምላሽ (Active response) የሚሰጠው ብልቱ ነው። ስልኳን ለመቀበል፣ ለመግባባትና ሌሎች ብዙ ጥሩም ይሁን መጥፎ ነገሮችን ለማድረግ የሚያስበው ብልቱ ምላሽ ከሰጠ በኋላ ነው። ለምን ብለን ብንል የአዕምሯችን ቅኝ ገዢዎች የጫኑብን አስተሳሰብ ነው። ሴት አዕምሮዋ በባርነት እንደሚማቅቅ የምታውቀው ስትደፈር ምንም ባለማለቷ ነው። የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ይደፍራታል፣ የፋሽን ኢንዱስትሪው ይደፍራታል፣ የፊልም ኢንዱስትሪው ይደፍራታል፣ የመዝናኛው ኢንዱስትሪ በዘመናዊ መንገድ በወርቅ አልጋ አስተኝቶ በአደባባይ ይደፍራታል። በዚህ ረቂቅ በሆነ ደፈራ ሴቷም ደስተኛ ነች። ለመደፈር እንደ መስፈርት የሆኑትን ክብደቷን፣አካላዊ ቁመናዋን መልኳን በማቆንጀት ጊዜዋን ማባከንና አዕምሮዋ ሳይዳብር በእንጭጩ መተው ስኬት እንደሆነ አምናበት ቀና ብላ ትሄዳለች። መልኳን እንጂ ማንነቷን ማቆንጀት ተራ እንደሆነ በአዕምሮዋ ቅጅ ገዢዎች የተበሰረላትን ብስራት አሜን ብላ ተቀብላለች። ስለ ሴት ጥብቅና እንቆማለን ብለው የሚሉት እንኳ ይህን እውነት መመልከት ተስኗቸዋል። በተሰጣቸው ፍቺ ተስማምተው ሌሎችን ለማሳመን ይጥራሉ። በባርነት ለምትማግዳቸውና በባርነታቸው ለሚደሰቱት የፆታ እኩልነት፣ Affirmative action እያልክ የበታችነትን የሚሰብክ እድል መፍጠር፣ ተቋም ማቋቋም ስላቅ ነው። በሀሳብ ባርነት የተጠፈነገ አዕምሮ ስለ መፅሀፍ ሽፋን እንጂ በመፅሀፉ ውስጥ ስላሉት ገፆችና በገፆቹ ውስጥ ስለ ሚከተቡት ነገሮች አይጨነቅም። ሁላችንም እንዲህ እየኖርን ነው ገፅታችንን እውነት እየቀባን ውስጣችን ግን ባዶ ውሸት። ብንደኸይ፣ ብንገዳደል፣ ብንወነጃጀል አይገርምም። ምክንያቱም በባርነት በወደቀ አዕምሮ ሚዛናዊነት፣ አዲስ ሀሳብና ፈጠራ እንዴት ብሎ ሊኖር ይችላል? " >>
        ~~