Get Mystery Box with random crypto!

አንፍረድ! [የረጅም ግዜ ብሶት የወለደው... ] : ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከሕልማቸው ተስፋን ያጡ ወጣ | Reyan Records

አንፍረድ!
[የረጅም ግዜ ብሶት የወለደው... ]
:
ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከሕልማቸው ተስፋን ያጡ ወጣቶች እንዲሁም ጎልማሶች ሐያታቸውን በራሳቸው ሲቋጩት እያየን ነው። (እየተለማመድነው ነገር...)

በሰው ተከቦ ሰው እንደማጣት፣ ለመራመድና ለመጠንከር በመጣጣር ውስጥ ከድባቴ (depression) ጋር መታገል እጅግ ፈታኝ ነው። ያደክማል... ለዛም ነው ደፍረው "ጌታዬ ያንተ ቀጠሮ አያሻኝም በቅቶኛል" ሲሉ እጅ የሚሰጡት.... ስታወራው ዝም የሚልህ ወዳጅህ፣ ሲርቅህ የራሱ ጉዳይ ያልከው ወንድምህ፣ በስህተቱ ምን አገባኝ የምትልለት ጓደኛህ እንደሰማይ የራቀው ተስፋውን ይበልጥ እያራቅክበት እንደሆነ ተረዳው። አንተን ችግር አይነካህም ማለት አይደለም አውቃለሁ። ግን ደሞ ያንተ ብሶት፥ ነገ ራሱን አጥፍቶ ከምትገናኘው የፀፀት ጅራፍ ይቀላልና... ረጅም እድሜህን አብሮህ በመከራና በደስታ ሲጋራህ የነበረ ወዳጅህ ሲርቅ ጠይቀው.... "ሁሌ ለምን እኔ?" የሚለውን የፉክክር ቃል ተወው...

የሚሰማው እንደሌለ ማሰብ፣ የኑሮ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች፣ የቤተሰብ ብዙ መጠበቅ፣ (ዛሬ እንደሰማነው ከሆነ) ብድር፣ በስራ ላይ ውጤታማነትን ማጣት፣ በፍቅር ግንኙነት ስኬታማ አለመሆን ና የመሳሰሉት ተደማምረው እጅን ወደአንገት ያሰድዳሉ። ከአጀል መድረስ ጋ አንነካካም፣ የሆነው ሆኖ ግን ሰበቢያው ያሳስበናል።

በየካፌው የዞራችሁ መሆናችሁ፣ ፈገገ ማለቱ አሊያም ፊቱ መውዛቱ ለደህንነቱ ማረጋገጫ አይደለም። ብቻዬን ልሁን ሲልህ እሺ ማለትህ መልካም ጓደኝነት አይሆንም። ሐጃህ ያውጣህ ማለትም የሙእሚን ባህሪ አልነበረም። ጠንካራ ነበርና የዛሬ የውስጥ ብሶቱን ጠንክሮ ያልፈዋል ማለት አይደለም። ሺህ ጓደኞች አሉት፣ የሚያወራው ሰው አያጣም ስትል በቸልታ አትለፈው። ሺህ ሰዎች ኖረውት አንድ  አዳማጭ የሌለው እልፍ ነው።

በሩሑ ላይ ጨክኖ የሔደ ሰው እዚያ ያደረሰውን ችግር ማሰብ ይቻልሐል? የኔ ያልከው፣ አውቀዋለሁ የምትለው ጓደኛህ ምን አሳር ቢገጥመው ነው እንዲህ ያደረገው? (ሐሳቡ አይኖርህም )
ችሎ ችሎ ሲያመልጥህ ... ፀፀት አይበቃህም። የሱ ጓደኛ መባልህ ሐሳቡን ካላቀለለው ወዴት ነው ጓደኝነትህ? ጓደኝነት ሰጥቶ መቀበል አይደለምና ፍርድህን ለአላህ አኑረህ ለጓደኛህ ኑረው።

ሳይረፍድ... እየሳቀ ሳያታልልህ... ድብርቱ አቅሉን ሳይወስደው...  እየፋፋ ሳያመልጥህ... ነብሱን ቁማር ሳይበላ... ፀፀት ደጃፍህ ሳይዘልቅ... ኑሮህን ሐዘን ሳይወርሰው.... ለጓደኛህ ጓደኛ ሁን!


@yeruh_weg