Get Mystery Box with random crypto!

ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ nikuyebetekerstiandemtsi — ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ nikuyebetekerstiandemtsi — ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ
የሰርጥ አድራሻ: @nikuyebetekerstiandemtsi
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.87K
የሰርጥ መግለጫ

ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ
የዩቲዩብ ቻናሉን ምዕመናን ሰብስክራይብ ያድርጉ የበለጠ ጠንክረን እንድሰራ ይረደናል
https://www.youtube.com/channel/UCYc6W7aFPzYIkK0F1a4VSlQ
ማንኛውንም መረጃ በዚህ ማድረስ  ትችላላችሁ
@Nikutewahedo
@Niku_tewahedo

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-10 08:49:29 የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ስልጠና ለጀማሪዎች ለሁለት ወር

በዚህ ዙር ላይም #20 ተማሪዎች ብቻ ስለምንመዘግብ ቀድመው ይመዝገቡ

1. የስልጠናው ጥቂት ማብራሪያ
የትምህርቱ ዋና ዓላማ
→ የግእዝ ቋንቋን ተምረው ለማያውቁ ሰዎች ከመጀመሪያው አስጀምሮ ማሳወቅ እና ቋንቋውንም መደበኛ በሆነ መልኩ ከፊደላት አመጣጥ እስከ ግስ መገሰስ ለመማር የሚፈልጉትን አነሣሥቶ ጥንታዊ የሆነ ቋንቋችንን ለዘመኑ ትውልድ በሚመቸው በዘመናዊና ቀላል በሆነ የተመቻቸ አቀራረብ ማስተማር ነው። የተዘጋጀውም በሀገር ውስጥና በውጭም ለሚገኙ ወገኖቻችን ቋንቋውን ለማወቅ ፍላጎት ኖሯቸው ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች የመማር ዕድል ሳያገኙ ለቀሩ ጀመሪ ሰዎች ነው።
የትምህርቱ አሰጣጥ
→ ኮርሱ መሠረታዊ የሆኑ ትምህርቶች የያዘ ሲሆን በ4 ምዕራፎች ተከፋፍለው ይሰጣሉ። የትምህርት ጊዜያት ሰኞ እና ሀሙስ ሲሆን ከንጋቱ 1:3ዐ ሰዓት ላይ ትምህርቶች በየግላችሁ ይላክላችኋል።
ስለዚህም የዕለቱ በሚመችዎት ማንኛውም ሰዓት ላይ ገብተው መከታተል ይችላሉ።
→ ትምህርቶች የሚሰጡባቸው መንገዶች በጽሑፍ(pdf) ፣ በድምፅ(voice record) ሲሆን አጠቃላይ ዘመኑን በዋጀ መልኩ ይሰጣል ማለት ነው።

→ ውይይቶች፣ መልመጃዎች፣ የቤት ሥራዎች እንዲሁም የምዘና ፈተናዎች ይኖራሉ።

ትምህርቱን ላጠናቀቁ ተማሪዎችም የማጠናቀቂያ Certificate (የምስክር ወረቀት) ይሰጣል።

በስልጠናውም ፍጻሜ ከ70 በላይ የግእዝ መማርያ መጽሐፍት በPDF ይደርሶታል።

ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ 250BIRR(የኢትዮጵያ ብር) ነው።

ለመመዝገብ ከፈለጉ @asrategabriel ላይ ያናግሩን
ለበለጠ መረጃ 0914946589
ላይ ዘወትር በስራ ሰዓት ብቻ ይደውሉ

ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም
809 views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 13:52:39 በቡስካ ኢትዮጵያ የሚገኘው የአቡነ ሙሴ ጸሊም ገዳም ገድል እና ጉብኝት

አንድ አምላክ በሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኢትዮጵያዊ ጻድቅ የአባታችን የአቡነ ሙሴ ጸሊም ገድል ትሰሙ ዘንድ የመጣችሁ የቤተከርስቲያን ልጆች የሆናችሁ ወንዶችና ሴቶች በሙሉ ፈጽማችሁ በእዝነ ልቦናችሁ ስሙ አድምጡም ::
አባታችን የስሙን ትርጉም ብንመለከት ጸሊም ማለት ጨለማ ጥቁር ማለት ሲሆን ሙሴ ጸሊም መልኩ እጅግ ጥቁር የሆነ ጨለማን የሚመስል ፊት ያለው በትውልዱ ኢትዮጵያው ሲሆን አስቀድሞ በውንብድና ኑሮ ሕይወቱን ይገፋ ነበር፡፡ ሙሴ ጸሊም ከቅዱስ መቃርስ ጋር ከመገናኘቱ በፊት በፀሐይ የሚያመልኩ ጌቶች ያሉትና እርሱ ራሱም በባርነት የሚኖር በፀሐይ የሚያመልክ በነፍሰ ገዳይነቱ የታወቀና የሌቦች ሁሉ አለቃ የከፉ ምግባር ሁሉ ፈጻሚ ነበር:: ማንም በፊቱ ሊቀርብና ሊቋቋመውም አይችልም ነበር ሲበላና ሲጠጣም እንዲሁ ከልክ በላይ ነበር::
አንድ ቀን ራሱን ወደ ሰማይ ቀና በማድረግ ወደ ፀሐይዋ እያየ ፀሐይ ሆይ አንቺ አምላኬ እግዚአብሔር ከሆንሽ ራስሽን ግለጭልኝ ይል ነበር ከፀሐይ ምንም መልስ ሲያጣ አምላክ የኛ ጌቶች ናቸው በልተው ጠጥተው ከጥላ አርፈው የሚውሉ ፀሐይ ግን ሲመሽ ትጠፋለች ለጨለማ ቦታዋን ለቃ ሌሊት አትታይም ጠዋትም ትወጣለች ስትሄድ ትውላለች በማለት ለጓደኞቹ ነገራቸው እነሱም በዚህ በግብፅ በረሃ ውስጥ ገዳም አለ ወደዚያ ግባ አሉት እርሱም አቤቱ እኔ የማላውቅህ ጌታ እንዳውቅህ እርዳኝ አለ ወዲያውም አንድ ድምፅ ወደርሱ መጣ...ሙሉውን በቪዲዮ ለማግኘት

ሙሉውን የገድል እና ጉብኝት ቪድዮ ከታች ባለው ሊንክ መመልከት ትችላላችሁ










1.3K views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 14:11:10
ፖሊስ ዛሬ ጋዜጠኛ አቤል ገብረ ኪዳንን (Ab Bella) አራዳ ፍ /ቤት አቅርቦታል ። 'አድዋ በአል እንዳይከበር በመላው አዲስ አበባ ወጣቶችን ሲያደራጅ ደርሼበታለሁ' ብሏል።
'እስከዛሬ (7 ቀን) የትነበረ ?!' ብለን ጠይቀናል።
ፖሊስ 'እኔ ያገኘሁት ቅዳሜ ነው።ከዛ በፊቴ የት እንደነበረ አጣራለሁ' ብሏል።

ለችሎቱ አቤል በአድዋ ዙሪያ ፖስት ያደረጋቸው ጽሁፎች ፕሪንት ቀርቦ ታይቷል።(የኔን ፖስት ጭምር ሼር ያደረገው ቀርቧል )
ፖሊስ ቅዳሜ ነው የያዝኩት ስላለ ሶስት ቀን ተጨማሪ ተፈቅዷል።
ጠበቃው እኔ ስለሆንኩ ከዚህ በላይ አስተያየት መስጠት አልችልም!
መልካም ቀን
1.5K views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 11:49:01
አንድ መጽሃፍ ቅዱስ በ5 ቢሊዮን ብር!
***
በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ መሰረት፣ መጽሐፍ ቅዱስ በመላው ዓለም በብዛት የተሸጠ እና በስፋት የሚሰራጭ መጽሐፍ ተደርጎ ተመዝግቧል፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ በልዩ ልዩ ቋንቋና ዕትም የሚታተም እንደመሆኑ መጠን እስከአሁን ድረስ በዓለም ላይ ምን ያህል መጽሃፍ ቅዱስ እንደታተመ በትክክል ማወቅ ባይቻልም ከ6 ቢሊዮን በላይ ቅጂዎች እንደታተሙ ይገመታል፡፡

ኮዴክስ ሳሶን (Codex Sassoon) የተባለ ከ1000 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረ ዕብራይስጥኛ መጽሃፍ ቅዱስ በሐራጅ እስከ በ50 ሚሊዮን ዶላር (5 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር) ሊሸጥ ነው የሚል ዜና ዛሬ በዋሽንግተን ፖስት ተጽፎ አነበብኩ፡፡ በዓለም ላይ እስከ አሁን ድረስ ከተሸጡ መጽሃፎች በዋጋ ውድ እንደሆነ እየተነገረለት ነው፡፡ ዋጋው ይህ ባይሆንም በእርግጥ ውድ ነው፡፡ እኔ በዓለም መደነቅ እየተገረምኩ የታላቁን መጽሃፍ ቅዱስ ሰማያዊ ዋጋና የተከፈለውን ገንዘብ አሰብኩና ዝም አልሁ፡፡ ዝም።

መጽሃፍ ቅዱስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ቀኖና 81 መጻህፍት፣ በካቶሊክ ዕምነት ቀኖና 73 መጻህፍት እና በፕሮቴስታንት ዕምነት ቀኖና 66 መጻህፍት ያሉት የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ በዓለማችን ላይ ብቸኛው የተሟላ መጽሃፍ ቅዱስ ከ800 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረውንና በግዕዝ ተጽፎ የሚገኘው የእኛው የኢትዮጵያ መጽሃፍ ቅዱስ እንደሆነ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?
1.8K views08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 21:31:25
በምእራብ ሐረርጌ ጭሮ ከተማ በሚገኘው በደብረ ሲና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ዝርፊያ መፈጸሙ ተገለጸ፡፡

በምእራብ ሐረርጌ ጭሮ ከተማ በሚገኘው በደብረ ሲና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የካቲት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ኪዳን እናደርሳለን ባሉ ከሕገ ወጡ ተሿሚ ወገን በሆኑ 4 ግለሰቦች አማካኝነት ከቤተ ክርስቲያኑ ሽቶ፣ ዕጣንና መብዓት ይዘው ሲወጡ መያዛቸውን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሁኔታውን የተመለከተው የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ጥይት በመተኮስ ምእመናን ተሰብስበው ሁለቱ ግለሰቦች ሊያዙ ችለዋል፡፡ ዝርፊያ የፈጸሙት ግለሰቦችን ምእመኑ ለከተማው ፖሊስ ያስረከበ ቢሆንም የከተማው ፖሊስ ግን ግለሰቦቹ ይህንን አያደርጉም አውቃችሁ ነው በሚል ያለምንም ማጣራት ግለሰቦቹን መልቀቁ ተገልጿል፡፡

በአንጻሩ የቤተ ክርስቲያኑን ጠባቂ ለምን ወደ ሰማይ ተኮስክ በሚል ማሰራቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡
950 views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 19:36:39
በሀዲየኛ ቋንቋ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለማገልገል ጉባኤ ዘርግተው በመትጋት ላይ ያሉ ህጻናት እና ታዳጊ ወጣቶች
***

ቅድስት ቤተክርስቲያን አንድ አከባቢ ላይ በመከራም ሆነ በደስታም ጸንታ ትኖር ዘንድ እና በአከባቢ ቋንቋ የሚያገለግሉ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን ማፍራት ትልቅ ሚና አለው።

ሐዋርያዊ አገልግሎት ለማዳረስ እና ውብ የሆነውን የቅድስት ቤተክርስቲያን የነፍስ ማዳን ገጽ ለፍጥረት ለማድረስ ቋንቋን መሰረት ያደረጉ ፈተናዎችን ማጥፋት እና ማጥበብ ግድ ነው።

ህገ ቤተክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ፣ ሐዋርያዊ ሰንሰለት ሳይጣስ እንዲህ አይነት ተግባራት በሁሉም አከባቢዎች ሊሳፋፋ ይገባል።

እግዚአብሔር ይመስገን
1.4K views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 21:54:11
955 views18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 21:53:53 እንዳው ስለ ፍትህ ስርአቱ የተወሰነ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ በሚል

ፓስተር ቢኒያም ሽታዬ(ሌላው በጎ ስራው እንዳለ ሆኖ በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እጅግ መልካም ንግግሮችን በመናገር ይታወቃል) የካቲት 02/2015 ነበር "ሁከት እና ብጥብጥ ለማስነሳት ሞክረሃል" በሚል በአዲስ አበባ ፖሊስ እጁ የተያዘው፡፡

በፍርድቤት ታሪክ ሪከርድ በሆነ የጠበቆች ብዛት በቡድን ቀርበን ተሟግተንለት በ5000 ብር ዋስ እንዲለቀቅ ከተወሰነለት ጀምሮ እነሆ 9 ቀናት አልፈዋል፡፡ፓስተሩ አሁንም ድረስ እስር ቤት ነው ያለው፡፡

ፓስተር ቢኒያም ከእስር እንዲለቀቅ የተወሰነው ውሳኔ እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ በፖሊስ ይግባኝ ቀርቦበት ውሳኔው ጸንቷል።

ምን ዋጋ አለው?!..

."ፖሊስ ሊለቀው ፈቃደኛ አይደለም!" ብለን ድጋሚ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ክስ አቀረብን፡፡
እኛ(ጠበቆች) በሌለንበት ፖሊስ በጎን ችሎት ገብቶ ፓስተሩን ለቅቄዋለሁ ብሎ ችሎቱን አሳሳተ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌዴራል ፍርድቤት የፈታውን እስረኛ ፖሊስ እራሱኑ ክስ ጠቅሶ(ሁከትና ብጥብጥ) አዲስ አበባ ፍርድቤት በድጋሚ ዛሬ ጠዋት አቀረበው፡፡እዛም ጠበቆች ቡድን አባላት ቀርበው ተከራከሩ፡፡

ዛሬ ጠዋት ፓስተር ቢኒያም በ2000 ብር ዋስ እንዲለቀቅ ተወሰነ፡፡
ባለቤቱ እኔ ይህን ፖስት በምጽፍበት ሰአት ገንዘቡን እያስያዘች ነው፡፡
አሁን ደግሞ ኦሮሚያ ፍርድቤት ይወስዱት ይሆናል፡፡

በዚህ ሰሞን ደግሞ በአንደኛው "ጁሪስዲክሽን"(የፍርድቤት የስልጣን ክልል) የተለቀቀ እስረኛን ወደ ሌላ ጁሪስዲክሽን መውሰድ እስረኛን በየክልሉ እንደ ህዳሴ ዋንጫ ማዞር ፋሽን አድርገውታል፡፡ ይሄ እንግዲህ አዲስ ፈሊጥ መሆኑ ነው፡፡

##

ጋዜጠኛ አቤል ገብረኪዳን(Ab bella) ከታሰረ ሰነበተ፡፡

ህገመንግስታችን ላይ(የአሁኑ ብቻ ሳይሆን የጃንሆይም ህገመንግስት ጭምር) አንድ ተጠርጣሪ እጁ ከተያዘ በኋላ በ48 ሰአት ውስጥ ቅርብ በሚባለው ፍርድቤት መቅረብ አለበት በማለት ይደነግጋል፡፡

በነገራችን ላይ 48 ሰአት መጠበቅ ግዴታ አይደለም፡፡
እንደው ወንዝ ቢሞላ፡መንገድ አላሻግር ቢል ፖሊስ እስረኛውን ፍርድ ቤት ለማቅረብ ቢቸገር የተቀመጠ የጊዜ ገደብ ነው፡፡
የድሮ ፖሊሶች (የጃንሆይ ዘመን) ይቺ 48 ሰአት እንዳታልፍባቸው በበቅሎ በፈረስ ወደ ፍርድቤት እስረኛ ይዞ ለመድረስ ይጋጋጡ እንደ ነበር በታሪክ ተምረናል..ይሄም ድሮ ሆኖ እነደ ባለ አስር ሳንቲሙ ዳቦ 'ነበር ' ሆነ ማለት ነው እንግዲህ፡፡

አቤል ገብረኪዳን የታሰረው የካ ፖሊስ ጣቢያ(መምሪያ) ነው፡፡

የካ ፍርድቤትና የካ ፖሊስ ጣቢያ በመካከላቸው ያለው ርቀት ከ20 የአዋቂ እርምጃ አይበልጥም፡፡እንደውም በሀገሪቷ ውስጥ ካሉ ፍርድቤቶች(ምናልባትም በመላው አፍሪካ) ለፖሊስ ጣቢያ "ዘ ኒረስት" የሚባለው ፍርድቤት የየካው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት መሰለኝ፡፡
ይሁን እንጂ ለቤተክርስትያን በመቆርቆሩ የታሰረውን አቤል እስከ አሁን ፍርድቤት እንኳን አላቀረቡትም፡፡

…ምን እንደምል አላውቅም..የኋሊት ጉዞውን ሽምጥ

ተያይዘነዋል፡፡
967 views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 10:23:01
. ዜና እረፍት
እማሆይ ብርሃን ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ!!

በታላቁ ዲማ ቅዱስ ገዳም በምናኔ እና ጸሎት የኖሩት እማሆይ ብርሃን የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 አከባቢ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

እማሆይ ብርሃን በጥንታዊውና በታሪካዊው በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም በትህትና እና ጸሎት መኖሪያቸውን አውላላ ሜዳ ላይ የቤታቸውን ጣሪያ ሰማይ መኝታቸውን ምድር አድርገው አምላከ ጊዮርጊስ እየተማጸኑ መኖር ከጀመሩ ከ30 ዘመናት በላይ ሆኗቸዋል።

በእነዚህ ዘመናት ባዶ ሜዳ ላይ ተቀምጠው ዝናብ ሲዘንብ እሳቸው የተቀመጡበት ቦታ ደረቅ ሆኖ እሳቸውንም ሆነ የተቀመጡባትን አካባቢ ዝናብ ሳያገኘው ፤ ቱልት የተባለውን ቅጠል ብቻ እየተመገቡ በጸሎት ኖረዋል።

በዋልድባ ገዳም የሚኖሩ አባቶች ከሰማይ በቀስተ ደመና አምሳል ብርሃን ሲወርድላቸው አይተው መጥተው እማሆይ በረከትዎ ይድረብን ብለው በጸሎታቸው ተባርከው ምስክርነታቸውን ሰጥተው እጅ ነስተው ወደ በዓታቸው ዋልድባ ተመልሰዋል፡፡

ሥርዓተ ቀብራቸው በታላቁ ገዳም በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በዕለተ ቀኑ በቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት ይፈጸማል።

የእናታችን የእማሆይ ብርሃን በረከት ይደርብን።
1.1K views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 09:59:30
የባሰ አታምጣ አለ ያገሬ ሰው !!

አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሲያይ የሚያቅለሸልሸው የጸጥታ አካል ይዘን የት ልንደርስ ነው ?!

እኔን ይቺን ቲሸርት ለማስወለቅ የተረባረበው የፖሊስ ብዛት ትንሽ ሃይል ቢጨምር አልፈሽጋ ላይ የተወሰደብንን መሬት ማስመለስ ይችል ነበር!!

ደሞኮ የአንዳንዶቹ የንቀታቸው ልክ!!

እንግዲህ መንግስት በአሉን የምታከብርበትንም ሆነ የምትለብሰውን ልብስ እኔ ነው የምመርጥልህ ብሏል!..
ከታሪክ ጋር ግብግብ ነው የተያዘው!!
##
ለማንኛውም እንኳን ለዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ አድዋ ላይ ድል ያደረጉበት 127ኛ አመት የድል በአል አደረሳችሁ!!
1.1K views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ