Get Mystery Box with random crypto!

እንዳው ስለ ፍትህ ስርአቱ የተወሰነ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ በሚል ፡ ፓስተር ቢኒያም ሽታዬ(ሌላው በ | ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ

እንዳው ስለ ፍትህ ስርአቱ የተወሰነ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ በሚል

ፓስተር ቢኒያም ሽታዬ(ሌላው በጎ ስራው እንዳለ ሆኖ በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እጅግ መልካም ንግግሮችን በመናገር ይታወቃል) የካቲት 02/2015 ነበር "ሁከት እና ብጥብጥ ለማስነሳት ሞክረሃል" በሚል በአዲስ አበባ ፖሊስ እጁ የተያዘው፡፡

በፍርድቤት ታሪክ ሪከርድ በሆነ የጠበቆች ብዛት በቡድን ቀርበን ተሟግተንለት በ5000 ብር ዋስ እንዲለቀቅ ከተወሰነለት ጀምሮ እነሆ 9 ቀናት አልፈዋል፡፡ፓስተሩ አሁንም ድረስ እስር ቤት ነው ያለው፡፡

ፓስተር ቢኒያም ከእስር እንዲለቀቅ የተወሰነው ውሳኔ እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ በፖሊስ ይግባኝ ቀርቦበት ውሳኔው ጸንቷል።

ምን ዋጋ አለው?!..

."ፖሊስ ሊለቀው ፈቃደኛ አይደለም!" ብለን ድጋሚ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ክስ አቀረብን፡፡
እኛ(ጠበቆች) በሌለንበት ፖሊስ በጎን ችሎት ገብቶ ፓስተሩን ለቅቄዋለሁ ብሎ ችሎቱን አሳሳተ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌዴራል ፍርድቤት የፈታውን እስረኛ ፖሊስ እራሱኑ ክስ ጠቅሶ(ሁከትና ብጥብጥ) አዲስ አበባ ፍርድቤት በድጋሚ ዛሬ ጠዋት አቀረበው፡፡እዛም ጠበቆች ቡድን አባላት ቀርበው ተከራከሩ፡፡

ዛሬ ጠዋት ፓስተር ቢኒያም በ2000 ብር ዋስ እንዲለቀቅ ተወሰነ፡፡
ባለቤቱ እኔ ይህን ፖስት በምጽፍበት ሰአት ገንዘቡን እያስያዘች ነው፡፡
አሁን ደግሞ ኦሮሚያ ፍርድቤት ይወስዱት ይሆናል፡፡

በዚህ ሰሞን ደግሞ በአንደኛው "ጁሪስዲክሽን"(የፍርድቤት የስልጣን ክልል) የተለቀቀ እስረኛን ወደ ሌላ ጁሪስዲክሽን መውሰድ እስረኛን በየክልሉ እንደ ህዳሴ ዋንጫ ማዞር ፋሽን አድርገውታል፡፡ ይሄ እንግዲህ አዲስ ፈሊጥ መሆኑ ነው፡፡

##

ጋዜጠኛ አቤል ገብረኪዳን(Ab bella) ከታሰረ ሰነበተ፡፡

ህገመንግስታችን ላይ(የአሁኑ ብቻ ሳይሆን የጃንሆይም ህገመንግስት ጭምር) አንድ ተጠርጣሪ እጁ ከተያዘ በኋላ በ48 ሰአት ውስጥ ቅርብ በሚባለው ፍርድቤት መቅረብ አለበት በማለት ይደነግጋል፡፡

በነገራችን ላይ 48 ሰአት መጠበቅ ግዴታ አይደለም፡፡
እንደው ወንዝ ቢሞላ፡መንገድ አላሻግር ቢል ፖሊስ እስረኛውን ፍርድ ቤት ለማቅረብ ቢቸገር የተቀመጠ የጊዜ ገደብ ነው፡፡
የድሮ ፖሊሶች (የጃንሆይ ዘመን) ይቺ 48 ሰአት እንዳታልፍባቸው በበቅሎ በፈረስ ወደ ፍርድቤት እስረኛ ይዞ ለመድረስ ይጋጋጡ እንደ ነበር በታሪክ ተምረናል..ይሄም ድሮ ሆኖ እነደ ባለ አስር ሳንቲሙ ዳቦ 'ነበር ' ሆነ ማለት ነው እንግዲህ፡፡

አቤል ገብረኪዳን የታሰረው የካ ፖሊስ ጣቢያ(መምሪያ) ነው፡፡

የካ ፍርድቤትና የካ ፖሊስ ጣቢያ በመካከላቸው ያለው ርቀት ከ20 የአዋቂ እርምጃ አይበልጥም፡፡እንደውም በሀገሪቷ ውስጥ ካሉ ፍርድቤቶች(ምናልባትም በመላው አፍሪካ) ለፖሊስ ጣቢያ "ዘ ኒረስት" የሚባለው ፍርድቤት የየካው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት መሰለኝ፡፡
ይሁን እንጂ ለቤተክርስትያን በመቆርቆሩ የታሰረውን አቤል እስከ አሁን ፍርድቤት እንኳን አላቀረቡትም፡፡

…ምን እንደምል አላውቅም..የኋሊት ጉዞውን ሽምጥ

ተያይዘነዋል፡፡