Get Mystery Box with random crypto!

. ዜና እረፍት እማሆይ ብርሃን ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ!! በታላቁ ዲማ ቅ | ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ

. ዜና እረፍት
እማሆይ ብርሃን ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ!!

በታላቁ ዲማ ቅዱስ ገዳም በምናኔ እና ጸሎት የኖሩት እማሆይ ብርሃን የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 አከባቢ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

እማሆይ ብርሃን በጥንታዊውና በታሪካዊው በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም በትህትና እና ጸሎት መኖሪያቸውን አውላላ ሜዳ ላይ የቤታቸውን ጣሪያ ሰማይ መኝታቸውን ምድር አድርገው አምላከ ጊዮርጊስ እየተማጸኑ መኖር ከጀመሩ ከ30 ዘመናት በላይ ሆኗቸዋል።

በእነዚህ ዘመናት ባዶ ሜዳ ላይ ተቀምጠው ዝናብ ሲዘንብ እሳቸው የተቀመጡበት ቦታ ደረቅ ሆኖ እሳቸውንም ሆነ የተቀመጡባትን አካባቢ ዝናብ ሳያገኘው ፤ ቱልት የተባለውን ቅጠል ብቻ እየተመገቡ በጸሎት ኖረዋል።

በዋልድባ ገዳም የሚኖሩ አባቶች ከሰማይ በቀስተ ደመና አምሳል ብርሃን ሲወርድላቸው አይተው መጥተው እማሆይ በረከትዎ ይድረብን ብለው በጸሎታቸው ተባርከው ምስክርነታቸውን ሰጥተው እጅ ነስተው ወደ በዓታቸው ዋልድባ ተመልሰዋል፡፡

ሥርዓተ ቀብራቸው በታላቁ ገዳም በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በዕለተ ቀኑ በቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት ይፈጸማል።

የእናታችን የእማሆይ ብርሃን በረከት ይደርብን።