Get Mystery Box with random crypto!

የባሰ አታምጣ አለ ያገሬ ሰው !! አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሲያይ የሚያቅለሸልሸው የጸጥታ አካል ይዘን | ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ

የባሰ አታምጣ አለ ያገሬ ሰው !!

አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሲያይ የሚያቅለሸልሸው የጸጥታ አካል ይዘን የት ልንደርስ ነው ?!

እኔን ይቺን ቲሸርት ለማስወለቅ የተረባረበው የፖሊስ ብዛት ትንሽ ሃይል ቢጨምር አልፈሽጋ ላይ የተወሰደብንን መሬት ማስመለስ ይችል ነበር!!

ደሞኮ የአንዳንዶቹ የንቀታቸው ልክ!!

እንግዲህ መንግስት በአሉን የምታከብርበትንም ሆነ የምትለብሰውን ልብስ እኔ ነው የምመርጥልህ ብሏል!..
ከታሪክ ጋር ግብግብ ነው የተያዘው!!
##
ለማንኛውም እንኳን ለዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ አድዋ ላይ ድል ያደረጉበት 127ኛ አመት የድል በአል አደረሳችሁ!!