Get Mystery Box with random crypto!

ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ nikuyebetekerstiandemtsi — ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ nikuyebetekerstiandemtsi — ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ
የሰርጥ አድራሻ: @nikuyebetekerstiandemtsi
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.87K
የሰርጥ መግለጫ

ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ
የዩቲዩብ ቻናሉን ምዕመናን ሰብስክራይብ ያድርጉ የበለጠ ጠንክረን እንድሰራ ይረደናል
https://www.youtube.com/channel/UCYc6W7aFPzYIkK0F1a4VSlQ
ማንኛውንም መረጃ በዚህ ማድረስ  ትችላላችሁ
@Nikutewahedo
@Niku_tewahedo

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-02-15 21:50:23
የዛሬ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ፍ/ብሔር ምድብ ችሎት የዛሬ ውሎ እና ትእዛዝ ይህንን ይመስላል።
1.7K views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 21:46:22
ይሄን ልጅ የትም ልናገኝ አልቻልንም ይቅርታ
1.5K views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 21:45:10
በእሥር ላይ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያንን በተመለከተ በጥቂት ቀናት ጉዳያቸው ታይቶ እንደሚፈቱ ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
1.4K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 21:40:03 እግዚአብሔር ይመስገን ስለሁሉም
1.4K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 19:37:58
ዛሬ ማምሻውን የተደረሰው ስምምነት ዝርዝር:

#በትክክል "በኦሮሚያና ክልል በኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት፣ ቅዳሴ እና ሌሎችም አገልግሎቶች እንዲሰጡ የተጀመረው ስራ የህዝቡን ጥያቄ በሚመልስ መልኩ እንዲጠናከር፣ ለዚህም በዚህ በፊት ከተደረገው በተጨማሪ አስፈላጊው በጀትና የሰው ሀይል እንዲመደብ።"

በትክክል ያሉ ችግሮችን በመረዳት መፍትሄ ማስቀመጥ ማለት ይሄ ነው።

#ተመስገን
2.2K views16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 19:32:21
- "በቅርቡ በቤተ ክርስቲያናችን ተከስቶ የነበረው ችግር በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሰረት ተፈቷል"--- የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

- "ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ እግዚአብሔርን ታመሰግናለች"--- ብፁዕ አቡነ አብርሃም

#ተመስገን

*አሁን የታሰሩትን ፍቱ፣ ላለፉት ይቅርታ ጠይቁ፣ ሰላም ፍጠሩ።
2.0K views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 17:04:40 https://www.youtube.com/live/wMgJaj5pn4o?feature=share
2.1K views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 16:59:24 ሆኖም ግን የ2015 ዓ.ም የጾመ ነነዌ ሳምንት ቤተ ክርስቲያን በውስጥ ጠላቶች የተፈተነችበት ወቅት በመሆኑ የእምነቱ ተከታዮች የደረሰውና እየደረሰ ያለው ፈተና ከባድ ቢሆንም ልጆቿ በእምነት ጸንተው፣ በያሉበት ጥቁር ልብስ በመልበስ፣ በእንባ እና በጸሎት ከኃያሉ ከእግዚአብሔር ፊት የቆሙበት ወቅት መሆኑን ታሪክና ትውልድ የማይረሳው ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰው ልብ በሚሰብር ፈተና ተስፋ ሳንቆርጥ በእምነት በሚደረግ ጸሎት የበለጠ በእግዚአብሔር ፊት እንድንቆም እንድንበረታ ያስተምረናልና ልንበረታ ይገባናል ብለዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ አክለው በመካከለኛው ካሊፎርኒያ በተተኪ ትውልድ ላይ ትኩረት በመስጠት ልዩ ልዩ እቅዶችን በማዘጋጀት ሀገራችን ኢትዮጵያ በሰሜን አሜሪካ ለትውልድ የሚተላለፍ ርስትና ቅርስ እንዲኖራት ለማድረግ በኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ስም ታሪካዊ፣ ታላቅና ሰፊ ቦታ ለመግዛት እንደታሰበና በግዢ ስምምነት ውስጥ እንደነበረ ከ3 ወራት በፊት ገንዘብ በማሰባሰብ እርዳታ መጠየቁ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም የገዳሙ ግዢ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅና ቁልፉን እና አስፈላጊ የሆኑ የግዢ ሰነዶችን መረከብ መቻላቸውን በታላቅ ደስታ ብፁዕነታቸው ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ግዢውን ለመፈጸም 3.5 ሚሊየን ዶራል ከግል ድርጅቶች በወለድ እንዲሁም ከግለሰቦች ያለወለድ 1.9 ሚሊየን ያለወለድ በመበደር የተፈጸመ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ስለገዳሙ በተለያዩ የማኅበራዊ ድረ ገጾች በተደረገው ጥሪ መሠረት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በገንዘብ፣ በጸሎት፣ በእውቀት፣ በሙያና ውድ ጊዜያችሁን በመስጠት ላደረጋችሁት እርዳታ በእግዚአብሔር ስም ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል፡፡

ብፁዕነታቸው አክለው በዚህ ታላቅ የገዳም ቦታ ላይ የተሟላ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት መስጠት እንዲቻልና በጥናት የተዘጋጁ እቅዶችን በአጫር ጊዜ ማሟላት እንድንችል የሁላችሁም አስተዋፆ አስፈላጊ በመሆኑ በጸሎት፣ በእውቀት፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ አስፈላጊውን እርዳታ በማድረግ እንድትተባበሩን ሲሉ መንፈሳዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

በተጨማሪም ይህንን ታሪካዊ ገዳም ለማስመረቅና ለማስጎብኘት ይቻል ዘንድ ሚያዚያ 14 ቀን 2025 ዓ.ም /April 22, 2013 G.C/ የቅዳሴ ቤቱ የምርቃት መርሐ ግብር እንዲከናወን መወሰኑን በመግለጽ በዓለም ዙሪያ የሚትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በበዓሉ ላይ በመገኘት ከቅዱሳን በረከት እንዲሳተፉና ገዳሙን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 

መጨረሻም አሁን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከገጠማት ችግር አንፃር ስለገዳሙ ሰፊ ገለጻ ማድረግ አግባብ ባለመሆኑ ወደፊት የግዢ አፈጻጸሙን በተመለከተ ሰፋ ያለ መረጃ  እንደሚሰጡ ብፁዕነታቸው ገልጸዋል፡፡
2.0K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 16:59:24
“የካሊፎርኒያ ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ቁልፍ እና አስፈላጊ የሆኑ የግዢ ሰነዶችን ተረክበናል፡፡” ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (ዶ/ር)

ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (ዶ/ር) የሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳና አሪዞና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ይህንን የገለጹት በኢ/ኦ/ተ/ቤ በካሊፎርኒያ ሊገዛ የታሰበውን የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም አሁናዊ ሁኔታ በተለጹበት ወቅት ነው፡፡

ብፁዕነታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሁን በዓለንበት ዘመን በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ላሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ለሆኑ በእኩልነት የምትሰጠው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ዘመን ተሻጋሪ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ከሐዋርያት የተረከበችውን እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት በመጠበቅና በማስጠበቅ ሁሉንም በእኩልነት፣ በፍቅር፣ በአንድነትና በሰላም በመያዝ ለሀገራችን ኢትዮፕያ ነፃነት፣ ሉዓላዊነት፣ ህልውናና ክብር እንዲሁም ስልጣኔ ዋና መሠረት እንደሆነች በታሪክ የተጻፈ ከመሆኑም በላይ ዓለም የሚያውቀውና የሚመሰክረው እውነት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
1.7K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ