Get Mystery Box with random crypto!

ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ nikuyebetekerstiandemtsi — ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ nikuyebetekerstiandemtsi — ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ
የሰርጥ አድራሻ: @nikuyebetekerstiandemtsi
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.87K
የሰርጥ መግለጫ

ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ
የዩቲዩብ ቻናሉን ምዕመናን ሰብስክራይብ ያድርጉ የበለጠ ጠንክረን እንድሰራ ይረደናል
https://www.youtube.com/channel/UCYc6W7aFPzYIkK0F1a4VSlQ
ማንኛውንም መረጃ በዚህ ማድረስ  ትችላላችሁ
@Nikutewahedo
@Niku_tewahedo

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-02-18 16:50:45
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በአፍሪካ ሕብረት የነግህ ምስጋና  መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ቃለ በረከት አስተላለፉ


ቅዱስነታቸው አዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ከሚገኘው 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ጋር ተያይዞ በሕብረቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በዛሬው ዕለት በተከናወነው ለፈጣሪ የሚቀርብ የነግህ ምስጋና መርሐ ግብር ላይ ልዑካንን አስከትለው የተገኙ  ሲሆን በጉባኤው ላይ  በርካታ ነጥቦችን በማንሳት  ቃለ በረከት አስተላልፈዋል ።

በአባታዊ መልእክታቸውም በሀገራችን ተፈጥሮ የነበረው ጦርነት በሰላም እንዲፈታ የአፍሪካ ሕብረት ያደረገውን ጥረት አድንቀውና  በአደራዳሪነት የደከሙትን በሙሉ አመስግነው  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል  የተከናወነውን ጸሎት በአባትነት መርተዋል።

ምንጭ:- የቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
776 views13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 14:52:27
ሰበር መረጃ
ዛሬ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ ስምምነቱን ሳይሸራረፍ እንደሚቀበሉና ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በቅዱስ ሲኖዶስ በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተው አረጋግጠዋል።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አሕመድ በተገኙበት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ/ም በተደረገው ውይይት የተስማማንባቸውን (10) ዐሥር ነጥቦች ያለመሸራረፍ ለመፈጸም እንዲሁም ቀጣዩን ተግባር በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ለማከናወን ተስማምተናል ሲሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
1.7K views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 14:49:04
ዛሬ በእነ መ/ር ምህረተአብ መዝገብ ከዚህ ቀደም ዋስትና ተሰጥቷቸው ፖሊስ ግን ባልፈታቸው ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ፍ/ቤት ቀርበን ነበር።

ፌዴራል ፖሊስ ዋስትና በተፈቀደላቸው ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ብሎ አልሳካለት ሲል እና ፍ/ቤት ሲያስጨንቀው ተጠርጣሪዎቹን በአምቡላንስ ጭኖ ትላንት ማታ ለአዲስአበባ ፖሊስ አቀበላቸው።

አዲስአበባ ፖሊስ ፌዴራል ፖሊስ የጠቀሰውን ተመሳሳይ ድርጊት ጠቅሶ 'ግን ርእሱን ቀይሬዋለሁ' (ፌዴራል ፖሊስ ሽብር ነበር ያላቸው እኔ 'ሁከት' ብየዋለሁ በሚል) ፍ/ቤት በድጋሚ አቅርቧቸዋል!!

ዛሬ ጠዋት (በኢትዮጵያ የፍርድ ቤት ታሪክ ሪከርድ ይመስለኛል) በአንድ መዝገብ 19 ጠበቆች ቀርበን ተከራክረናል!!

የጠበቆች ቡድን አሁን ላይ 98 ባለሙያዎች ደርሰናል(አስፈላጊ ከሆነ 'ትይዩ ፍትህ ሚኒስትቴር ' እያደራጁ ነው ወይ የሚያስብል አቅም አለ...ተዋህዶ የልጅ ሃብታም ናት)

በእረፍት ቀናቸው በአንድ የስልክ ጥሪ ችሎት ከተፍ ብለው የሚያስደምም ክርክር ያቀረቡትን እነኚህን ንቁ ጠበቆች አመስግኑልን!!

ከዚህ ቀደም ተጠርጣሪዎች ፍ/ቤት የቀረቡት በተመሳሳይ ጉዳይ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ለመመርመር መዝገቡ ለሰኞ ከሰአት ተቀጥሯል!!

ፈጣሪ ይረዳናል !!
ወደ ኋላ የምንለው ነገር የለም!!
1.3K views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 20:39:02
1.5K views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 20:39:02 [ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዛሬው ዕለት ከተናገሩት የተወሰደ]

"ከሁለት ቀናት በፊት ሰላም መፈጠሩን ማወጃችን ይታወሳል። በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የምንሰማቸው ነገሮች ሁሉ እንደገና ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍል አባቶችን ከልጆች ልጆችን ከአባቶች የሚያሻክሩ ነገሮችን እየሰማን ነው

"ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ አዲሱ ሲኖዶስ በሚል አዲስ ስም እስካሁን ከሚጠቀሙበትም ለየት ባለ ስም የተሰጠ መግለጫ በሚል በሰጡት ባስተላለፉት ሁሉም በአንድነት ጵጵስናው የሚመለከታቸውም የማይመለከታቸውም የኤጲስ ቆጶስነቱ ደረጃም በስምምነቱም በጋራ የጠፋ ወይም የተሻረ የተደመሰሰ መሆኑን እያወቁም የቅድስናውን ልብስ በመልበስና ሌሎችም የስምምነቱ አካል ሆነው ስምምነቱን ያነበቡት ሳይቀሩ በአንድ ላይ ስምምነቱን ጥሰውታል ቀኖናውን እንደገና ደግመው ጥሰውታል። ሀይማኖቱንም ሕጉንም መልሰው መላልሰው ጥሰውታል።ሹመታቸው ሕጋዊ እንደሆነና በምንም ይሁን በምን የማይሻር መሆኑንም መልእክት አስተላልፈዋል። ይህ ከዕለት ወደ ዕለት የሚታይ የሚሰማ ከንቱ ክስ ሆኗል። ከሃይማኖታዊ ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘትን ተጎናጽፏል። በሃይማኖታዊ መንገድ በሰላምና በፍቅር በክርስቶስ ደም የተመሠረተችውን ቤተ ክርስቲያን ከመጠበቅ በክርስቶስ ደም የተዋጁትን ምእመናን ከማስተማር ይልቅ በኃይልና በጉልበት ሁሉንም በነገረ ሰሪነት ግጭት በመፍጠር ሁሉንም ለመቆጣጠር ከዕለት ወደ ዕለት ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ"

"አስተሳሰባቸው አነጋገራቸው ሁሉ በእኩል ደረጃ እንደሆኑም ተናግረዋል። 25 የተባሉትም የትናንትና ካህናት አገልጋዮች አሁንም ኤጲስ ቆጶሳት እንደሆኑ ተደርጎ ተንጸባርቋል። ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይህንን አድርገው ቀኑን ሙሉ አንመጣም ሲሉ ዉለው 10 ሰዓት ላይ ግን ለማንም ለማን መጣን ሳይሉ ቤታቸው ውስጥ[ቤተ ክህነት] ገብተዋል። ... ቤተ ክርስቲያንም እስቲ ሁሉንም ነገር በትዕግሥት እንየው በማለት ዝም ብለን እየተመለከትን ነው። ስለዚህ ሕግን የጣሰ ሰው ስምምነትን ያፈረሰ ሰው ዛሬም ደግመው ደጋግመው እውነት ለማስመሰል ሐሰትን በሚለፍፉ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ድፍረት የሚመለከተው አካል ሊመለከተውና አሁንም በቃ ሊለው ይገባል ብለን መልእክታችንን እናስተላልፋለን።"
1.6K views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 17:44:25
OMN የ25ቱ ሰዎች ሹመት እንዳልተነሳ 'አዲሱ ሲኖዶስ' ገለጸ ብሎ ለጥፏል!
መብቱ ነው።


እኔም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እነኚህን 25 ሰዎች እና ሶስት የቀድሞ ሊቃነጳጳሳትን እንዲሁም ጠበቃቸውን (ቃል አቀባያቸው) ጭምር ኢትዮጵያ ውስጥ ወዳሉ የትኛዎቹም አቢያተ ክርስትያናት እንዳይደርሱ እስከ የካቲት 17/2015 አ.ም ድረስ እንዳገዳቸው ማስታወስ ግዴታዬ ነው!
2.2K viewsedited  14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 14:09:56
2.4K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 14:09:50 “እግዚአብሔር ጾምና ጸሎቱን እንዲሰማ በእውነተኛ ንስሓ፣ በፍቅርና በይቅርታ መንፈስ ሆነን መጾምና መጸለይ አለብን፡፡” ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የ2015 ዓ.ም ጾመ ኢየሱስን በተመለከተ አባታዊ መመሪያና መልእክት አስተላለፉ።

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ በመልእክታቸው እንደገለጹት ባለፉት ሳምንታት የነበረውን የቤተ ክርስቲያን ፈተና በማውሳት የሦስቱን ቀን ጾማችንና ጸሎታችን ሰምቶ ችግራችን አስወግዶ ለዚህ ለአበቃን እግዚአብሔርን ምስጋና ይገባዋል ያሉ ሲሆን ብፁዕነታቸው አሁንም ስላደረገልን መልካም ነገር እግዚአብሔርን እያመሰገንን የዐቢይ ጾምን ጾም በተሰበረ ልብ፣ በንስሐ መንፈስ፣ በይቅርታና ከልብ በመፈቃቀር መጾምና መጸለይ አለብን ብለዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም በ2015 ዓ.ም በሚጾመው ዐቢይ ጾም የሰዓታት፣ የስብሐተ ነግህ፣ የቅዳሴ እና የስብከተ ወንጌል አገልግሎቶች ከወትሮው በተለየ መልኩ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አባታዊ መመሪያና መልእክት አስተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው አክለው እግዚአብሔር ጾምና ጸሎቱን እንዲሰማ በእውነተኛ ንስሓ፣ በፍቅርና በይቅርታ መንፈስ ሆነን መጾምና መጸለይ እንዳለብን እንዲሁም በአግልጋዮች፣ በምእመናንና በሁላችን መካከል ከልብ የመነጨ ፍቅር ሊኖር እንደሚገባ አባታዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ አእላፍ ቀሲስ በላይ ጸጋዬ ከጾሙና ጸሎቱ ጎን ለጎን ጊዜያችን ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገትና ሰላም የሚጠቅም ሥራ በመሥራት ማሳለፍ አለብን ብለዋል።

በዕለቱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ አእላፍ ቀሲስ በላይ ጸጋዬን ጨምሮ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የ7ቱ ክፍላተ ከተሞች ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆችና ሠራተኞች፣ በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ የሁሉም ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ካህናት አገልገልጋዮች ተገኝተዋል። መረጃው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነው፡፡
2.2K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 13:29:55
“ልጆቼ ኑ” መዝ 110፡10

ታላቅ የሽኝት እና የአደራ መርሐ ግብር

በ 2015 ዓ.ም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚገቡ ተማሪዎች በሙሉ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታላቅ የአደራ እና የሽኝት መርሐ ግብር አዘጋጅታለች

በመርሐ ግብሩ

• ትምህርተ ወንጌል
• በብጹአን አባቶች የአደራ መልዕክት ይሰጣል
• ስለ ወጣትነት እና የኮሌጅ ሕይወት ምክር ይሰጣል
• በሀገር አቀፍ ፈተና ትልቅ ውጤት ያመጡትን ልጆቿን ቤተክርስቲያን ትሸልማለች

ቀን፡ የካቲት11/2015 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከ 7፡30 ጀምሮ
ቦታ፡ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ

አዘጋጆች
ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት እና ማኅበረ ቅዱሳን
286 views10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 13:29:55 የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ፍቅርን እንደ ዓይን ብሌን ስንጠብቃት በእጅጉ የምትጠቅመንን ያህል ስንተዋት ደግሞ በእጅጉ ትጎዳናለች፡፡ በፍቅር እጦት የሚደርሰው ጉዳት በተወሰነ ነገር ብቻ ሳይሆን በነፍስም ሆነ በሥጋ፣ በምድርም ሆነ በሰማይ እጅግ በጣም የገዘፈና የሰፋ ነው፡፡

በሀገራችን የሆነውና እየሆነ ያለውም ይኸው ነው፡፡ ፍቅርን ባጣንባቸው ዓመታት ከየት ወዴት እንደደረስን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚገነዘበው ነው፡፡ ያተረፍነው ነገርም ምን እንደሆነ የምናውቀው ነው፡፡

ይሁንና የፍቅር እጦት ምን ያህል እንደጎዳን ራሳችን ተገንዝበን ወደ ሰላሙ መንገድ መመለሳችን የተሻለ አማራጭ መሆኑን ሳንመሰክር አናልፍም፡፡ የተጀመረው የፍቅርና የሰላም ጉዞም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ልባዊ ምኞታችንና ጸሎታችን ነው፡፡

ይህንን ሰላም እንዲመጣ ያደረጉ ወገኖችም ሁሉንም ሳናመሰግን አናልፍም፡፡ ምክንያቱም በሰዎች መካከል ፍቅርንና ሰላምን የሚያደርጉ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሚባሉ ጌታ እንደ አስተማረን ብፅዕና ይገባቸዋልና ነው፡፡ (ማቴ.፭፥፱)

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የፍጹም ፍቅር መገኛ የሆነው ቅዱስ ወንጌል የሚያስተምረው ፍቅር ራስን ማፍቀር ወይም መውደድ ሳይሆን ራስን መጥላት ባልንጀራን ግን መውደድ እንደሆነ ነው፡፡ “ወንጌላዊ-ፍቅር ፍጹም ነው” የሚያሰኘውም ቅሉ ይህ ነው፡፡

ለሁለት ሺህ ዘመናት ያህል በቅዱስ ወንጌል አስተምህሮ ላይ የተገነባው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ባህልም ይህን ፍቅር ጠብቆ የሚጓዝ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የኢትዮጵያ አበው መነኮሳት ከነበራቸው ፍቅርና ትሕትና የተነሣ፣ የሹመት ሽሚያ አያውቁም ነበር፡፡ ከዚህ አንጻር ትልቁን ሥልጣን ይቅርና የአንድ ገዳም መሪ ለመሆንም በእግር ብረት ታስረው በግድ ካልሆነ በቀር እሺ ብለው በፈቃደኝነት ሹመትን አይቀበሉም ነበር፡፡

ራሱን በራሱ መሾም ወይም እኔን ሹሙኝ ብሎ መናገርና የሌላን ድጋፍ መጠየቅ ለኢትዮጵያውያን መነኮሳት ጭራሽ ነውርና ጸያፍም ነበር፡፡ ከዘመነ ብሉይ ጀምሮ ለሦስት ሺህ ዘመናት የዘለቀው ሃይማኖታችን ምንም ዓይነት መለያየት ሳያጋጥመው አንድ ሆኖ ሊዘልቅ የቻለው ያም በመሆኑ ነው፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያናችን ጠንካራ አንድነት ለሕዝቡም በመትረፉ የሀገሪቱን አንድነትና ነጻነት አስጠብቆ እስከ ዘመናችን ሊደርስ ችሎአል፡፡ በዚህም ቤተ ክርስቲያናችን የሕዝብንና የሀገርን አንድነትና ነጻነት ለማስጠበቅ ያደረገችውና የምታደርገው ጥረት ሊያስመሰግናት እንጂ ሊያስወቅሳት አይገባም፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ከቅርብ ቀናት ወዲህ በቤተ ክርስቲያናችን ተከሥስቶ የነበረውን ሕጋዊ ያልሆነ ድርጊት የቤተ ክርስቲያናችንን ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና ባሕላዊ መርሕን የናደ፣ እንደዚሁም በኢትዮጵያ ይቅርና በዓለም ታሪክ ተደርጎ የማያውቅ ድርጊት እንደሆነ ቤተ ክርስቲያናችን በአጽንዖት ስትገልጽ ቆይታለች፡፡

ይህንን የቤተ ክርስቲያን ድምፅ በመስማትና በመቀበል ሕዝበ ክርስቲያንና ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለእግዚአብሔር ባቀረቡት ኀዘንና ጸሎት እንደዚሁም ባደረጉት መጠነ ሰፊና ዙርያ መለስ የሆነ የድጋፍ ርብርብ ስሕተቱ ሊታረም ችሏል፡፡

ለተገኘው መንፈሳዊ ውጤትም ጠቅላይ ሚንስትርና መንግሥታቸውን፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሉዓላዊነት እንዲከበር ከፍተኛ መሥዋዕትነት ለከፈለው መላው ሕዝበ ክርስቲያን እንዲሁም ይህ ስሕተት እንዲታረም ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን ተሰልፈው ድምፃቸውን ላሰሙ ኢትዮጵያውያንና የውጭ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በቤተ ክርስቲያናችን ስም ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርብላቸዋለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን ግልጽ ማድረግ የምንፈልገው ከቤተ ክርስቲያናችን ዶግማ፣ ቀኖና እና ሥርዓት መከበር እንደዚሁም ከሉዓላዊ አንድነቷ መጠበቅ በመለስ ያለው ጥያቄ ለማስናገድ ቤተ ክርስቲያናችን ዝግጁ መሆኗን ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ሕዝቦች በቋንቋቸው የመማር፣ የማስተማርና የማምለክ እንዲሁም የመተዳደር መብትን ካሁን በፊትም፣ አሁንም፣ ካሁን በኋላም የምትነፍግበት መሠረት እንደሌለም ሁሉም ሊያውቀው ይገባል፡፡

ይህም በመሆኑ በቋንቋ የመጠቀም መብት በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን ምዕራፍ ፪ አንቀጽ ፭ ከቁጥር ፩ እስከ ፫ ባለው አንቀጽ በሚገባ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ስለሆነም በቋንቋ የመጠቀም ጥያቄ በሕግ ደረጃ ተመልሶ በተግባር እየተሠራበት የሚገኝ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል፡፡

የተወዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ዛሬ ታላቁን ጾም በፍቅር ሆነን የምንጾምበት ወቅት ነው፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው ጾም ማለት ሥጋዊ ፈቃድን በመግታት ከእግዚአብሔር ጋር ጥብቅ ግንኙነት ለማድረግ የሚካሄድ መንፈሳዊ ተጋድሎ ነው፡፡

በጌታችን ጾም በተግባር እንዳየነው ጾም ማለት ዲያብሎስ የሚሸነፍበት በአንጻሩ ደግሞ የእግዚአብሔር ሕዝብ አሸናፊዎች የሚሆኑበት ኃይል ነው፡፡

ስለሆነም ጾም የተጋድሎና የሙዓት ሜዳ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የምንታገለውም ልብሰ ሥጋ ሰውን ሳይሆን ረቂቅ ፍጡር የሆነው ሰይጣን በሰው አድሮ የሚነዛውን አጥፊ ሐሳቡንና ድርጊቱን ነው፡፡ ከዚህም ጋር ሰውነታችን ለዚህ ክፉ መንፈስ ታዛዥ እንዲሆን የሚገፋፉ ጥሉላት መባልዕትን መተው፣ ኃይለ ሥጋን መቈጣጠር፣ ኃይለ መንፈስን ደግሞ ማጎልበት ያስፈልጋል፡፡ በጾም ወቅት የተራቡትን ማጉረስ፣ የታረዙትን ማልበስ፣ የተበደሉትን መካስ፣ ፍትሕና ርትዕ በማኅበረ ሰብ ውስጥ ማንገሥ ያስፈልጋል፡፡

በጾም ወቅት ኅሊናችን ማሰላሰል ያለበት ሰው ምን አለ? ወይም ምን አደረገ? በሚለው ሳይሆን እግዚአብሔር በፊቱ ምን ዓይነት ሰው እንድንሆንለት ይፈልጋል? በሚለው ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ጾማችን በዚህ መንፈስ የተቃኘ ፍቅረ፣ እግዚአብሔርንና ፍቅረ ቢጽን ማእከል ያደረገ፣ መጠራጠርንና አለመተመማንን ያስቀረ፣ የተለያዩትን ያቀራረበ፣ የተሳሳቱትን ያረመ በአንጻሩ ደግሞ ሁላችንን በሰላምና በፍቅር አንድ አድርጎ ያስተሳሰረ ይሆን ዘንድ በዚህ መንፈስ ተነቃቅተን እንድንጾመው አባታዊ ጥሪያችንን ለሕዝበ ክርስቲያኑ እናስተላልፋለን፡፡

በመጨረሻም

በሀገራችን እየታየ ያለው የሰላም ጭላንጭልና ችግሮችን በውይይት የመፍታት ዝንባሌ ለሁለንተና ልማታችንና ለዕድገታችን እንደዚሁም ለተሟላ አንድነታችን ጠቃሚነቱ የጎላ ስለሆነ እግዚአብሔር ለዘለቄታው እንዲያሳካልን ከልብ እንድናዝንና ወደ አምላካችን በተመሥጦ እንድንጸልይ በአጽንዖት በማሳሰብ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

መልካም የጾም ወራት ያድርግልን!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር! አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
የካቲት ፲፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
249 views10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ