2023-02-18 23:44:51
ዝም ትልና ከእውነት ጋር ለመቆም መረጃ ትሰበስባለህ ከዛም እንደዚህም አለ ትልህ እና ለህዝብ ታወራለህ
የኦሮሞን ገበሬ ንቀው አሜሪካ 17 ዓመት ያሉት ሰው፤
Ex ኤዎስጣቴዎስ 1997 ዓ.ም ለኦሮሞ ኦርቶዶክሳዊያን እንዲያገለግሉ ከተሾሙት 9 ኦሮሞ ጳጳሳት መካከል አንዱ የነበሩ ሲሆን። የተመደቡትም ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ነበር፡፡
የተመደቡበትን ሀገረ ስብከት (ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ) ላይ 1 ዓመት እንኳን ሳይቆዩ ትምህርት ልማር ይፈቀድልኝ በሚል ምክንያት በ1998 ምዕራብ ሐረርጌን ጥለው አሜሪካ ሄዱ ። ቅዱስ ሲኖዶስ ለ4ዓመት ብቻ ፈቅዶላቸው ከ4 ዓመት በዃላ ተመልሰው እዛው ኦሮሚያ ክልል እንደሚያገለግሉ በቃልም በደብዳቤም ገልጾላቸው ከሀገር ወጡ፡፡
አሜሪካ እስከ ጥቅምት ወር 2004 ዓ.ም ቆይተው ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ስለታወቀ፥ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ ኦሮሚያ ክልል ጉጂ ሊበን ቦረና ሀገረ ስብከት እንዲመሩ፣ የAfaan oromoo ቋንቋ ተናጋሪ ናቸውና የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ኦርቶዶክሳዊያንን በቋንቋቸው እንዲያገለግሉ መድቧቸው ነበር፡፡
Exአባ ኤዎስጣቴዎስ ግን ትምህርቴን ሳጠናቅቅ እመለሳለሁ ያሉትን ቃላቸው ሳይጠብቁ ወደ ሀገር ቤት (ኦሮሚያ ክልል ጉጂ ሊበን ቦረና ሀገረ ስብከት) አልመለስም ብለው ቀሩ። የተመደቡበት የኦሮሚያ ክልል ጉጂ ሊበን ቦረና ሀገረ ስብከት ያለ ሊቀጳጳስ ቀረ፡፡
ሊቀ ጳጳሱ ተመልሰው ኦሮሚያ ክልል ጉጂ ሊበን ቦረና እንዲያገለገሉ ከተወሰነበት ጥቅምት ወር 2004 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በስልክና በደብዳቤ ተደጋጋሚ መልእክት ሲያደርሳቸው ቢቆይም ከአሜሪካ ተመልሰው ኦሮሚያ ክልል ገጠራማው ጉጂ ሊበን ቦረና ሀገረ ስብከት መስራት ሳይፈልጉ በእንቢታቸው ጸንተው እዛው አሜሪካ እስከ ዛሬ ድረስ ቀርተዋል።
ማለትም ላለፉት 17 ዓመታት ኑሯቸው አሜሪካ ነው።
ቅዱስ ሲኖዶስ ሊያነጋግርዎ ስለሚፈልግ ወደ ሀገርዎ እንዲገቡ” በሚል፦ ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም.፣ ኅዳር 8 ቀን 2004 ዓ.ም.፣ ታኅሣሥ 18 ቀን 2005 ዓ.ም.፣ ግንቦት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. እና ኅዳር 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በጻፈላቸው አምስት ደብዳቤዎችና በስልክም ተደጋጋሚ መልእክት ቢያደርሳቸውም የቅዱስ ሲኖዶሱን ጥሪ ችላ ብለው ቀርተዋል። ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ለስድስተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ለሊቀ ጳጳሱ ባስተላለፈላቸው ጥሪ፣ ሐምሌ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ወደ ሀገር ገብተው ለጽ/ቤቱ እንዲያሳውቁ ደብዳቤ ለኮለቸው ነበር፡፡ “ካልመጡ ግን ቅዱስ ሲኖዶስ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት የሚገደድ መኾኑን ጉባኤው ወስኗል፤” በማለት አስጠንቅቆ ነበር - በቁጥር 245/699/2009 በቀን 18/09/2009 ዓ.ም.፣
ከቅዱስ ሲኖዶሱና ከፓትርያርኩ ተደጋጋሚ ጥሪ በተጨማሪ፣ በሚቀርቧቸው ካህናትና መምህራንም ተደጋጋሚ ምክር ቢሰጣቸውም፣ “ሰዉ በአውሬ እየተበላና በባሕር እየሰጠመ ብዙ መከራ አይቶና ብዙ ገንዘብ ከፍሎ የሚገባባትን ርስት ምድር አሜሪካንን ጥዬ አልወጣም፤ እንዲህ ያለ ሐሳብ ወደ እኔ ይዛችሁ አትምጡ፤” በሚል ወደ ሀገር ቤት ወደተመደቡበት ጉጂ ሊበን ሀገረ ስብከት እንደማይመለሱ ውሳኔያቸውን አሳውቀው በዚያው ቀርተወል። በዃላም በላኩት ሽምግልና አቡነ ኤዎስጣቴዎስ መኖር በፈለጉበት አሜሪካ እንዲጸኑ ቀሩ።
....
እንግዲህ ቤተክርስቲያን ላይ ለፈጸሙት በደል እንደምክንያት ያቀረቡት፦ ''የኦሮሚያ ክልል ያሉ ኦርቶዶክሳዊያንን በቋንቋቸው የሚባርክ ጳጳስ ተገቢው ሁኔታ የለም'' የሚል ነበር።
በተቃራኒው ህገወጡን ተግባር ከፈጸሙት መካከል አቡነ ኤዎስጣቴዎስ የተመደቡበትን የኦሮሚያ ክልል መጀመሪያ ምዕራብ ሐረርጌ ጥለው ወደ አሜረካ የኮበለሉ። በዃላም ቅዱስ ሲኖዶስ ጉጂ ሊበን ቦረና ሀገረ ስብከት እንዲመሩ የወሰነውን ውሳኔ በመጣስ ገጠራማውን የኦሮሚያ ክልል ያሉ ሀገረ ስብከቶችን ንቀው አሜሪካንን ባዕታቸው አድርገው ላለፉት 17 ዓመታት በእንቢታ የቆዩት አንዱ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ነበሩ።
ለ17 ዓመት ለማገልገል የናቁትና የጠሉትን የኦሮሞ ኦርቶዶክስ ጥያቄ ሳይመልሱ ፤ ከአሜሪካ በዓመት አንዴ ወይም ሁለቴ እሱንም ለቅዱስ ሲኖዶስ ስበሰባ ብቅ ለሚሉባት ሀገርና የረሱትን ህዝብ ጥያቄ የዘነጉት ሰው። ዛሬ ተቆርቋሪ መስለው የሚታዩት ዓላማቸው ቤተክርስቲያንን ማፍረስ ለሶስተኛ ወገን መሸጥ ስለሆነ ብቻ ነው።
ለኦሮሞ ኦርቶዶክስ የሚያስብ አባት ገጠር ከተማ ሳይመርጥ በሚችለው ቋንቋ ያገለግል ይመራቸዋል እንጂ የወጣበትን ህዝብ ሸሽቶ አሜሪካ የተቀመጠ አባት በምን ሞራሉ ተቆርቋሪ መስሎ ይቀርባል?
...
ሳጠቃልል፤ Ex አባ ኤዎስጣቴዎስ
ቤተክርስቲያን ውስጥ 40 ዓመት አገልግለዋል ነገርግን አንድም ቀን በAfaan Oromoo ሰብከው ፣ ቀድሰው አያውቁም
18 ዓመት በጵጵስና ቆይተዋል አሜሪካንን ጥለው መጥተው የኦሮሞ ኦርቶዶክስን ለማገልገል ፍቃደኛ አልሆኑም
አንድም የAfaan Oromoo መጽሃፍት ጽፈው ወይንም ተርጉመው አያውቁም
633 views20:44