Get Mystery Box with random crypto!

ውግዘቱ ይነሳልን ልመና ... EX ኤዎስጣቴዎስ በትምህርት ከሁለቱ አማጺ ጳጳሳት የተሻሉ ናቸው። | ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ

ውግዘቱ ይነሳልን ልመና
...
EX ኤዎስጣቴዎስ በትምህርት ከሁለቱ አማጺ ጳጳሳት የተሻሉ ናቸው። የአብነት ትምህርትም አላቸው ቴዎሎጂም ተምረዋል። እና ውግዘት Excommunication ምን እንደሆነ በሚገባ ያውቁታል። በእርግና እድሚያቸው ተወግዘው ከቤተክርስቲያን ህብረት መለየት ጾኑ ህመም ነው። ያውም በቅዱስ ሲኖዶስ መገዘት ትርጉሙን ይረዱታል።
ሁለቱ እንኳን እንዲሁ የኦሮሞ ጳጳስ ኮታ ይሙላ በሚል ነው የተሾሙ የረባ ትምህርት ሳይኖራቸው። በተለይ ሳዊሮስ ከዲያቆንነት በዓመት ልዩነት ውስጥ ነው አመንኩሰው ያጰጰሷቸው 97 ዓ.ም ላይ።

ኤዎስጣቴዎስ እንደዛ አይደሉም ተምረወል። ተግባራቸውን ብኮንንም እውቀታቸውንና ትምህርታቸውን አልክድም። ለዛም ነው ውግዘቱ ይነሳልን ልመና ላይ ያሉት።
...
ከጠ/ሚ አብይ ጋር በነበረው ውይይት ቅድሚያ ውግዘት ይነሳል ልመናው። ከዛም በዃላ በመጥፎ ተግባራቸው ላይ ሆነውም እንኳ ውግዘቱ ይነሳል ልመና ላይ ያሉ። በቅዱስ ሲኖዶስ ተገዝተዋል ታስረዋል። ማለትም በሰማይም በምድርም የታሰሩና የተረገሙ ሆነዋል። ይህ በሃዋሪያዊ ጽኑ ስልጣን የሆነ ነው።