Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር መረጃ ዛሬ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ ስምምነቱን ሳይሸራረፍ | ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ

ሰበር መረጃ
ዛሬ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ ስምምነቱን ሳይሸራረፍ እንደሚቀበሉና ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በቅዱስ ሲኖዶስ በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተው አረጋግጠዋል።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አሕመድ በተገኙበት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ/ም በተደረገው ውይይት የተስማማንባቸውን (10) ዐሥር ነጥቦች ያለመሸራረፍ ለመፈጸም እንዲሁም ቀጣዩን ተግባር በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ለማከናወን ተስማምተናል ሲሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተዋል።