Get Mystery Box with random crypto!

በምእራብ ሐረርጌ ጭሮ ከተማ በሚገኘው በደብረ ሲና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ዝርፊያ መፈጸ | ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ

በምእራብ ሐረርጌ ጭሮ ከተማ በሚገኘው በደብረ ሲና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ዝርፊያ መፈጸሙ ተገለጸ፡፡

በምእራብ ሐረርጌ ጭሮ ከተማ በሚገኘው በደብረ ሲና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የካቲት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ኪዳን እናደርሳለን ባሉ ከሕገ ወጡ ተሿሚ ወገን በሆኑ 4 ግለሰቦች አማካኝነት ከቤተ ክርስቲያኑ ሽቶ፣ ዕጣንና መብዓት ይዘው ሲወጡ መያዛቸውን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሁኔታውን የተመለከተው የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ጥይት በመተኮስ ምእመናን ተሰብስበው ሁለቱ ግለሰቦች ሊያዙ ችለዋል፡፡ ዝርፊያ የፈጸሙት ግለሰቦችን ምእመኑ ለከተማው ፖሊስ ያስረከበ ቢሆንም የከተማው ፖሊስ ግን ግለሰቦቹ ይህንን አያደርጉም አውቃችሁ ነው በሚል ያለምንም ማጣራት ግለሰቦቹን መልቀቁ ተገልጿል፡፡

በአንጻሩ የቤተ ክርስቲያኑን ጠባቂ ለምን ወደ ሰማይ ተኮስክ በሚል ማሰራቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡