Get Mystery Box with random crypto!

አንድ መጽሃፍ ቅዱስ በ5 ቢሊዮን ብር! *** በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ መሰረት፣ መጽሐፍ ቅዱስ | ንቁ የቤተክርስቲያን ድምፅ

አንድ መጽሃፍ ቅዱስ በ5 ቢሊዮን ብር!
***
በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ መሰረት፣ መጽሐፍ ቅዱስ በመላው ዓለም በብዛት የተሸጠ እና በስፋት የሚሰራጭ መጽሐፍ ተደርጎ ተመዝግቧል፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ በልዩ ልዩ ቋንቋና ዕትም የሚታተም እንደመሆኑ መጠን እስከአሁን ድረስ በዓለም ላይ ምን ያህል መጽሃፍ ቅዱስ እንደታተመ በትክክል ማወቅ ባይቻልም ከ6 ቢሊዮን በላይ ቅጂዎች እንደታተሙ ይገመታል፡፡

ኮዴክስ ሳሶን (Codex Sassoon) የተባለ ከ1000 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረ ዕብራይስጥኛ መጽሃፍ ቅዱስ በሐራጅ እስከ በ50 ሚሊዮን ዶላር (5 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር) ሊሸጥ ነው የሚል ዜና ዛሬ በዋሽንግተን ፖስት ተጽፎ አነበብኩ፡፡ በዓለም ላይ እስከ አሁን ድረስ ከተሸጡ መጽሃፎች በዋጋ ውድ እንደሆነ እየተነገረለት ነው፡፡ ዋጋው ይህ ባይሆንም በእርግጥ ውድ ነው፡፡ እኔ በዓለም መደነቅ እየተገረምኩ የታላቁን መጽሃፍ ቅዱስ ሰማያዊ ዋጋና የተከፈለውን ገንዘብ አሰብኩና ዝም አልሁ፡፡ ዝም።

መጽሃፍ ቅዱስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ቀኖና 81 መጻህፍት፣ በካቶሊክ ዕምነት ቀኖና 73 መጻህፍት እና በፕሮቴስታንት ዕምነት ቀኖና 66 መጻህፍት ያሉት የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ በዓለማችን ላይ ብቸኛው የተሟላ መጽሃፍ ቅዱስ ከ800 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረውንና በግዕዝ ተጽፎ የሚገኘው የእኛው የኢትዮጵያ መጽሃፍ ቅዱስ እንደሆነ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?