Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 174.19K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 391

2022-05-21 11:54:30 ከሞጣ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የሞጣ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት በከተማዋ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለማስተካከል በአሁኑ ሰዓት የጸጥታ መዋቅሩ በሙሉ አቅም እየሰራ ይገኛል፡፡ ስለሆነም መላ ህዝባችን ፦

1ኛ. ማንኛውም ህዝብ/ግለሰብ በቡድን ሆኖ በከተማዋ መንቀሳቀስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

2ኛ. ማንኛውም ሰው በህግ የሚፈለጉ አካላትን ደብቆ ወይም አከራይቶ ቢገኝ ተጠየቂ መሆኑን አውቆ ችግር ፈጣሪዎችንና ተፈላጊዎችን አሳልፎ እንዲሰጥ እናሳስባለን፡፡

3ኛ. ለህግ ማስከበር ሲባል ከጥዋቱ 12፡00 ሰዓት በፊትና ከምሽቱ 12፡30 ሰዓት በኋላ ስምሪት ከተሰጣቸው የጸጥታ ሃይሎች ውጭ እንቅስቃሴ ገደብ የተቀመጠ መሆኑን እያሳሰብን ይህንን በሚተላለፉ አካላት ላይ የጸጥታ ሃይላችን እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል፡፡

4ኛ. ስምሪት ከተሰጠው የጸጥታ ሃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

5ኛ. የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ነገር ለማባባስ የሚሰሩና የጸረ ሰላም እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግለሰቦችን እንዲመክሩ እየጠየቅን የከተማችን ወጣቶችና መላ ህዝቡ ከጸጥታ መዋቅሩ ጎን እንዲቆሙ ጥሪያችንን እያቀረብን ከላይ የተጠቀሱ ክልከላዎችን በመተላለፍ ለሚወሰድ እርምጃ ምክርቤቱ ኃላፊነት አይወስድም፡፡

ግንቦት 13/2014ዓ.ም
የሞጣ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት
30.2K views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:54:02
በባለሙያ እና በመሳሪያ የተደራጀ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ
የብሬስ ህክምና ለማስጀመር ነፃ የማማከር አገልግሎት እና የአከፋፈል መንገድ
ለተማሪዎች ልዮ ቅናሽ( መታወቂያ መያዝ እንዳይረሱ )
ሁሉንም ህክምና በተመጣጣኝ ዋጋ እንሰጣለን
ቁጥር 1- 4ኪሎ ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ ላይ
ቁጥር 2- ኮተቤ 02 ጆሲ ሙል ላይ
ለበለጠ መረጃ  በ0911-42-42-42
0970-51-71-51 ይደውሉልን
በቲሊግራም - https://t.me/shalomdentalclinic
Face book- @shalomdentalclinic
28.9K views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:53:42
Smart Charger
የቻርጅ ካሜራ

Full HD 1080P
Motion Detection
Remote Wireless Camera
Download App

ዋጋ፦ 3000 ብር

ውስን ፍሬ ነው የቀረው
< Limited Stock

Telegram - t.me/qnashcom
Website - www.qnash.com
ጥራት ዋስትና ቅናሽ

ማሳሰብያ
ሱቃችን ሲመጡ ትክክለኛ የኛ ሱቅ መሆኑ ያረጋግጡ እንዳንድ ሰወች 329 ነው እያሉ የማይሆን ዕቃ በማይሆን ዋጋ እየሸጡ ስለሆነ ጥንቃቄ አድርጉ የራሳችን ሎጎ መኖሩን እና 329 መሆኑ ያረጋግጡ
ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3 ተኛ ፎቅ 3 ከሊፍት እንደወረዱ በግራ በኩል
ስልክ:
0946966440
0905464599
+251118639952
26.5K views08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:51:35 #Ethiopia : በኦሮሚያና በአጎራባች ክልሎች የሸኔ የሽብር ቡድን ከሌሎች የጥፋት ኃይሎች ጋር በመተባበር ህዝባችን ላይ እያደረሰ የነበረውን ጥቃት ለመቀልበስ መንግስት የተሳካ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች በአልሸባብ የሽብር ኃይል ላይ እየተወሰደ የሚገኘውም እርምጃ ውጤታማ በሆነ መንገድ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በአዲስ አበባና በዙሪያው ኦሮሚያ ከተሞች በቡድን ተደራጅተው በልዩ ልዩ የዝርፊያ ወንጀሎች ላይ የተሰማሩ፣ የጦር መሳሪያና የገንዘብ ዝውውር አቀባባይ በሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች፤ እንዲሁም በወያኔ ሰርጎ ገቦች ላይም መንግስት ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡ በሁሉም ክልሎች እየተካሄደ በሚገኘው ኦፕሬሽን በርካታ ግለሰቦችና ቡድኖች ከነ ትጥቆቻቸዉ፤ ከዘረፉት ንብረትና ቀጣይ ሊፈፅሙ ያቀዷቸዉ ጥፋቶችን ካሰፈሩባቸው ሰነዶች ጋር በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ እየተደረገ ነው። ጉዳያቸውም ተገቢውን ሂደት ጠብቆ እየተጣራ ለፍርድ እንዲቀርቡ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የዜጎች ነፃነትና ዲሞክራሲም መስፈን የሚችለዉ የትኛውም ጉልበት አለኝ የሚል አካል ከህግ በታች መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ነፃነትንና መብትን ከለላ በማድረግ የሚፈፀም የትኛውም አይነት እኩይ ተግባርን መንግስት አይታገስም፡፡ መንግስት በሆደ ሰፊነት በተደጋጋሚ ጊዜ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ከቁብ ያልቆጠሩ ኃይሎችን መግታት የሚቻለው የህግ የበላይትን በማስከበር ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ዜጋና የተለየ አመለካከት ያላቸው ወገኖችም መብትና ጥቅሞቻቸዉን ማስከበር የሚችሉት የህግ የበላይነት ሲረጋገጥና ሰላም ሲሰፍን ብቻ ነው፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት!
20.4K viewsedited  18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:37:32
"ከሰሞኑ በአማራ ክልል በህገወጥ የጦር መሳሪያና ገንዘብ ዝውውር፤ በቡድን ተደራጅቶ ግለሰቦች ያፈሩትን ሃብትና ንብረት በመዝረፍና በማውደም ላይ የተሰማሩ፤ በነፍስ ግድያ የሚጠረጠሩ፣ አንዱን ህዝብ ከሌላው ጋር በማጋጨት ክልሉ እንዳይረጋጋ በሚያደርጉ ቡድኖች ላይ መጠነ ሰፊ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡ " - መንግስት

#Ethiopia : መንግስት፣ በሁሉም ክልሎች እየተካሄደ በሚገኘው ኦፕሬሽን በርካታ ግለሰቦችና ቡድኖች ከነ ትጥቆቻቸዉ፤ ከዘረፉት ንብረትና ቀጣይ ሊፈፅሙ ያቀዷቸዉ ጥፋቶችን ካሰፈሩባቸው ሰነዶች ጋር በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ እየተደረገ ነው። ጉዳያቸውም ተገቢውን ሂደት ጠብቆ እየተጣራ ለፍርድ እንዲቀርቡ እየተደረገ ይገኛል ብሏል፡፡

መንግስት ፣ በፋኖ ስም የሚነግዱ የዝርፊያ ቡድኖች በህዝባችን ላይ ከፍተኛ ክህደት የፈፀሙ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች እና የተላላኪዎቻቸው ዓላማ ማስፈፀሚያ መሆናቸው ነው ያለ ሲሆን መላው ህዝባችን ይህንን እኩይ ሴራ በመገንዘብ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመደገፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ይጠይቃል ብሏል።

የሚዲያና የጋዜጠኝነት ካባ ደርበው ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የሚወሰደውን የማያዳግም እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል፡፡(የመንግስት ኮሙኒኬሽን)
22.0K views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 20:18:43 የዜጎችን ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የሀገርን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ብቸኛው መፍትሄ የህግ የበላይነትን ማስከበር መሆኑን መንግስት ገለፀ

የዜጎችን ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የሀገርን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ብቸኛው መፍትሄ የህግ የበላይነትን ማስከበር መሆኑን መንግስት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፥ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የሚታየውን ህገወጥነትና የሰላም መደፍረስ እንዲሁም ስርዓት አልበኝነትን መንግስት እንዲቆጣጠር ህዝቡ በተደጋጋሚ በአንድ ድምፅ ሊባል በሚችል መልኩ ሲጠይቅ መቆየቱን አንስቷል።

ከሰሞኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ውስጥ የፌደራልና የክልል የፀጥታ ኃይሎች እየወሰዱት ያለው ህግ የማስከበር እርምጃ የዚሁ አካል መሆኑን ነው ያስታወቀው።

በሁሉም ክልሎች እየተካሄደ በሚገኘው ኦፕሬሽን በርካታ ግለሰቦችና ቡድኖች ከነትጥቆቻቸዉ፣ ከዘረፉት ንብረትና ቀጣይ ሊፈፅሙ ያቀዷቸዉ ጥፋቶችን ካሰፈሩባቸው ሰነዶች ጋር በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ እየተደረገ መሆኑንም የገለፀው መግለጫው፥ ጉዳያቸውም ተገቢውን ሂደት ጠብቆ እየተጣራ ለፍርድ እንዲቀርቡ እየተደረገ ይገኛል ብሏል።

መንግስት በሆደ ሰፊነት በተደጋጋሚ ጊዜ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ከቁብ ያልቆጠሩ ኃይሎችን መግታት የሚቻለው የህግ የበላይትን በማስከበር ብቻ ነው ያለው መግለጫው፥ ሁሉም ዜጋና የተለየ አመለካከት ያላቸው ወገኖችም መብትና ጥቅሞቻቸውን ማስከበር የሚችሉት የህግ የበላይነት ሲረጋገጥና ሰላም ሲሰፍን ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የዜጎችን ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የሃገርን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ብቸኛው መፍትሄ የህግ የበላይነትን ማስከበር ነው!

በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የሚታየውን ህገወጥነትና የሰላም መደፍረስ እንዲሁም ስርዓት አልበኝነትን መንግስት እንዲቆጣጠር መላ ህዝባችን በተደጋጋሚ በአንድ ድምፅ ሊባል በሚችል መልኩ ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡ ቀደም ሲል ብሔራዊ የፀጥታ ም/ቤት እነዚህን ጉዳዮች በመገምገም አስፈላጊው እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ማስታወቁም የሚታወስ ነው፡፡ ከሰሞኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ውስጥ የፌደራልና የክልል የፀጥታ ኃይሎች እየወሰዱት ያለው ህግ የማስከበር እርምጃ የዚሁ አካል ነው፡፡

በኦሮሚያና በአጎራባች ክልሎች የሸኔ የሽብር ቡድን ከሌሎች የጥፋት ኃይሎች ጋር በመተባበር ህዝባችን ላይ እያደረሰ የነበረውን ጥቃት ለመቀልበስ መንግስት የተሳካ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች በአልሸባብ የሽብር ኃይል ላይ እየተወሰደ የሚገኘውም እርምጃ ውጤታማ በሆነ መንገድ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ በአማራ ክልል በህገወጥ የጦር መሳሪያና ገንዘብ ዝውውር፤ በቡድን ተደራጅቶ ግለሰቦች ያፈሩትን ሃብትና ንብረት በመዝረፍና በማውደም ላይ የተሰማሩ፤ በነፍስ ግድያ የሚጠረጠሩ፣ አንዱን ህዝብ ከሌላው ጋር በማጋጨት ክልሉ እንዳይረጋጋ በሚያደርጉ ቡድኖች ላይ መጠነ ሰፊ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡ በአዲስ አበባና በዙሪያው ኦሮሚያ ከተሞች በቡድን ተደራጅተው በልዩ ልዩ የዝርፊያ ወንጀሎች ላይ የተሰማሩ፣ የጦር መሳሪያና የገንዘብ ዝውውር አቀባባይ በሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች፤ እንዲሁም በወያኔ ሰርጎ ገቦች ላይም መንግስት ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡ በሁሉም ክልሎች እየተካሄደ በሚገኘው ኦፕሬሽን በርካታ ግለሰቦችና ቡድኖች ከነ ትጥቆቻቸዉ፤ ከዘረፉት ንብረትና ቀጣይ ሊፈፅሙ ያቀዷቸዉ ጥፋቶችን ካሰፈሩባቸው ሰነዶች ጋር በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ እየተደረገ ነው። ጉዳያቸውም ተገቢውን ሂደት ጠብቆ እየተጣራ ለፍርድ እንዲቀርቡ እየተደረገ ይገኛል፡፡

መንግስት ህግና ስርዓትን በማስከበር የዜጎች ደህንነትና የሀገር ቀጣይነትን ለማረጋገጥ እየወሰደ ላለው እርምጃ መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል፡፡ በሁሉም ክልሎች መላው ህዝባችን የጥፋት ሰንሰለቶቹን ከማጋለጥ ጀምሮ አጀንዳውን የሁከትና ብጥብጥ ማስፈፀሚያ ለማድረግ የሚጥሩ ኃይሎችን እየታገለ ይገኛል፡፡ በአንፃሩ የተለያዩ ስያሜዎችን በመስጠት የመንግስትን እርምጃ ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች መኖራቸውን መንግስት አረጋግጧል፡፡ አሸባሪው ህወሃት እና ጀሌዎቹ መንግስት እየወሰደ ባለው እርምጃ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ህገወጥ ቡድኖችን በተለይም በአማራ ክልል የህግ የማስከበር ስራዎችን ለማደናቀፍ የሚሞከሩ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለማባባስ ከወዲሁ አጋርነታቸውን በይፋ እየገለፁ ነው፡፡ ይህ የሚያመለክተን እነዚህ ቡድኖች በተለይም በፋኖ ስም የሚነግዱ የዝርፊያ ቡድኖች በህዝባችን ላይ ከፍተኛ ክህደት የፈፀሙ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች እና የተላላኪዎቻቸው ዓላማ ማስፈፀሚያ መሆናቸው ነው፡፡

መላው ህዝባችን ይህንን እኩይ ሴራ በመገንዘብ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመደገፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መንግስት ይጠይቃል፡፡ ለሃሰተኛ መረጃዎችና የጥፋት መልእክትን ለያዙ ወሬዎች ጆሮ ባለመስጠት የህግ የበላይነትን የማስከበሩን እርምጃ እንደ እስካሁኑ በሙሉ አቅሙ ማገዙን እንዲቀጥልም ጥሪውን ያቀርባል። መንግስት በበኩሉ በህገወጥ ተግባር ላይ በመሳተፍ፤ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር ሆነ ብለው፤ አቅደዉ በሚሰሩ አካላትና ግለሰቦች እንዲሁም የሚዲያና የጋዜጠኝነት ካባ ደርበው ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የሚወሰደውን የማያዳግም እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

የዜጎች ሰላም፣ ደህንነትና የሀገር ቀጣይነት የሚረጋገጠው የህግ የበላይነት ሲከበር ብቻ ነው፡፡ በመላ ኢትዮጰያ የሚገኘው ዜጋ በሰላም ወጥቶ የመግባት መብቱ እንዲከበርና ደህንነቱ እንዲጠበቅ የህግ የበላይነትን ማስፈን ደግሞ ህዝብ ለመንግስት የሰጠው ሃላፊነት ነው። የዜጎች ነፃነትና ዲሞክራሲም መስፈን የሚችለዉ የትኛውም ጉልበት አለኝ የሚል አካል ከህግ በታች መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ነፃነትንና መብትን ከለላ በማድረግ የሚፈፀም የትኛውም አይነት እኩይ ተግባርን መንግስት አይታገስም፡፡ መንግስት በሆደ ሰፊነት በተደጋጋሚ ጊዜ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ከቁብ ያልቆጠሩ ኃይሎችን መግታት የሚቻለው የህግ የበላይትን በማስከበር ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ዜጋና የተለየ አመለካከት ያላቸው ወገኖችም መብትና ጥቅሞቻቸዉን ማስከበር የሚችሉት የህግ የበላይነት ሲረጋገጥና ሰላም ሲሰፍን ብቻ ነው፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት!!
27.8K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 18:44:26
31.1K views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 18:44:16 ኢንጂነሩ - ከሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች በስተጀርባ

#Ethiopia : ኢንጂነሩ ኅብር ኢትዮጵያ የተባለውን ፓርቲ የግል ንብረቱ አድርጎ እንዳሻው እየዘወረው ነው፡፡ ሰሞኑን ፓርቲውን እንደ ሽፋን በመጠቀም ከኢመደበኛ አደረጃጀት ጋር በድብቅም በግልፅም የሚያደርገው ግንኙነት ኢትዮጵያ በሽብር እንድትታመስ፤ አመፅ እንዲነሳ የልብ መሻት ያለው መሆኑን ያመላክታል። የአማራን ህዝብም “እየተጠቃህ ነው፤ ተነስ፤ ተዋጋ” በሚል ሀገር ተረጋግታ ወደ ልማት እንዳትገባ ፀብ ቀስቃሽ ሀሳብን በየአጋጣሚው ማንሳቱም ከበስተጀርባው ድብቅ ተልዕኮ እንዳለው እያሳበቀበት ይገኛል፡፡

የህብር ኢትዮጵያ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ስም እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም፤ የምርጫ ቦርድንና ሌሎችን የሀገሪቱን የሕግ ማዕቀፎች በሚጻጸር መልኩ በትጥቅ ትግልና በአመጽ መንግስት መቀየር ወይም የሽግግር መንግስት መመስረት ይገባል የሚል አመለካከት ከሚያራምዱ አካላት ጋር ሲመክርና ሲያሴር መገኘቱም አነጋጋሪ እየሆነ ነው፡፡

ኢንጂነሩ የትጥቅ ትግል አደረጃጀቶች ልሳን በሆኑና በስውር ለህወሓት በሚሰሩ ሚዲያዎች ላይ መንግሥት ፋኖን እያጠቃ መሆኑን በማወጅ ህዝቡ ወደ ጦርነት እንዲገባ ገፋፍቷል፡፡ ህዝብ ለአመፅና ለእምቢተኝነት እንዲነሳ ያልሆነውን ሆነ በማለት ግፊት ሲያደርግ፤ ምንም እንኳን የስልጣን ፍላጎቱ ከቁጥጥሩ ውጪ አድርጎት ህሊናው ባይወቅሰው እንኳን ህግ እንደሚጠይቀው ማወቅ ነበረበት።

የህብር ኢትዮጵያ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ምርጫ 2013 ከመካሄዱ በፊት ማይክ በጨበጠ፤ መድረክ ባገኘበት አጋጣሚ ሁሉ ለኢትዮጵያ ችግር ብቸኛው መፍትሄ የሽግግር መንግሥት መመስረት ነው፤ ምርጫው መካሄድ የለበትም በማለት ሲቃወም ከርሞ፤ በምርጫው በመሳተፉ የሚገኘውን የገንዘብ ትርፍ ሲያሰላው ግን ስላላስቻለው ግንባር ቀድም ተፎካካሪ መስሎ ለመታየት መሞከሩ ይታወሳል፡፡ ገንዘቡ እንደ ግል አካውንቱ በሚቆጥረው የፓርቲው አካውንት ሲገባ ደግሞ ያን የዛገና የሰለቸ የሽግግር መንግሥት አጀንዳ ከኋላ ኪሱ አውጥቶ በየመገናኛ ብዙሃን በራፍ ደጅ መጥናቱን ቀጥሎ ነበር፡፡

ኢንጂነሩ ዛሬ ዛሬ ለሽግግር መንግሥት አጀንዳው ማስፈጸሚያ በኢመደበኛ አደረጃጀቶች ጀርባ ተሸሽጎ መንቀሳቀሱን የመረጠ ይመስላል፡፡ ይህ አካሄድ ጸረ ኢትዮጵያ አቋም ባላቸው አካላት ከበስተጀርባ በገንዘብ እንደማይደገፍም በምርጫ ወቅት ከተስተዋለው የአፍቅሮተ ነዋይ ጉዳይ በመነሳት “በትንሽ ያልታመን ለትልቅ አይታጭም” እያስባለ ነው፡፡
31.5K views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 18:43:58
የሊንኮቹን ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+kpVVJnBHB5ZhZjI0
29.7K views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 15:06:42 ሽልማቱን በትህትና አልቀበልም

ውድድር በመኖሩ ጥሩ የሰራን በማበረታታት አጥብቄ አምናለሁ ግን ሰው ነኝና ደግሞ የራሴ እሳቤና መንገድ አለኝ::

ውድ የጉማ አዋርድ አዘጋጆች ለሁሉም ድርጅት በቅድሚያ እንዳሳወኩት ሁሉ ለተከበረ ድርጅታችሁ ምንም አይነት የእጩነትና ውድድር ክብር መድረክ አልሳተፍም ብዬ ቀደም ብዬ አሳውቄለሁ:: ለሌላ የሚገባው የስራ አጋሬ ማበርከት ሲገባው ሽልማቱ ለምን እንዲህ ማድረግ እንደተፈለገ አልገባኝም:: እኔና ህሊናዬ ግን ከእውነተኛ አክብሮት ጋር ሽልማቱን አንቀበልም::


ካለብን የፖሊሲ ገደብ የታክስ አከፍፈል ተመንና ለሙያው ያለው ምቾት የማይሰጥ ግንዛቤ እዚ ሙያ ውስጥ መስራታችን እየሰራንም መቆየታችን በራሱ ለሁሉም የሙያ አጋሮቼ ትልቅ አሸናፊነት ነው::

በውድድሩ ስማችሁ አብሮኝ የተጠቀሰ የሙያ አጋሮቼ በችሎታ ከእናንተ እኩል እንደ ደረስኩ ስለታሰብኩ ትልቅ ክብር ተሰምቶኛል:: የውድድር አዘጋጆችም ከሙያ አጋሮቼ እሚተካከል ችሎታ አላት ብላችሁ ስላሰባችሁኝም ከልቤ ደስ ብሎኛል ::

እድሉን አግንቼ እምሰራው የትኛውም ስራ የጥበብ ስራ አክባሪዎች በፈቀዱልኝ ልክ በተለየ የህይወት አጋጣሚ ለማሳለፍ መነገር ያለበትን ታሪክን ለማክተብና ስሜትን ለማጋባት እንደሆነ ብቻ ሁሌም ይታሰብልኝ::

የስራ አድናቂዎችሽ ምን ይሉሻል ዝም ብለሽ ተቀበይ ለምሉኝ ወዳጆቼ ሀሳባችሁን አከብራለሁ ከፍቅር ነውና
.
.
ግን
.
.
እኔና የእውነተኛ የስራዬ ወዳጆች እንተዋወቃለን እኔን ያውቁኛል የኔን እውነቴን በመናገሬ ብሳሳት "ቅሌት /ስህተት/ ብርቄ አይደለም" ለዛም ነው የሚወዱኝ የሚቀበሉኝ ብዬ ማስብን መርጫለሁ::

ስለዚህ በግሌ ከየትኛውም የውድድርና የእጩነት ክብር መድረክ እራሴን አግልያለሁ ወደፊትም:: ይህን ከግል አቋም ለስራዬ ካለኝ የተለየ ትርጉምና የስራዬን ወዳጆች ከማክበር እንጂ ከሌላ በፍፁም እንዳይታይብኝ አደራ እላለሁ አመሰግናለሁ::

ከአርቲስት ሳያት ደምሴ
38.5K views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ