Get Mystery Box with random crypto!

'የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አመራሮች እና የፀጥታ ሀይሉ ጋር በጋራ በመሆን በተ | Natnael Mekonnen

"የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አመራሮች እና የፀጥታ ሀይሉ ጋር በጋራ በመሆን በተሰራ ስራ የተሻለ ውጤት ማምጣት መቻሉን ብርጋዴር ጀነራል አበባው ሰይድ ተናገሩ "።

ጀነራል አበባው ታደሰ የማእከላዊ ኮማንድፖስት ዋና ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ሹማ አብደታን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችና የሰሜን ሸዋዞንና የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አመራሮች በተገኙበት በተሰሩ የሰላም ስራዎች ላይ በከሚሴ ከተማ ገምግመዋል።

ብርጋዲየር ጀነራል አበባው ሰይድ እንደተናገሩት የሁለቱን አጎራባች ዞኖች በጋራ በማድረግ በተደረገ ግምገማ ጥሩ ውጤት የታየ ሲሆን እስካሁን በሁለቱ ዞኖች አስቸግሮ የነበረ የፀጥታና ደህንነት መደፍረስ የሰላም ማስከበር እንቅፋት የሆኑ የሁለቱን ዞኖች የብሄረሰብ ግጭት በማስመሰል ባለፋት ጊዜያት መንገድ እስከመዘጋት ድረስ የሚያደርስ ሁለቱን ብሄረሰብ የማያቋርጥ ግጭት ለማስገባት በሸኔና ፅንፈኞች አለመረጋጋት እንዲፈጠር ሲሰሩ ነበር ያሉት ጀነራሉ በዚህም የሁለቱ ዞኖች አመራሮችና የፀጥታ ሀይሉ ጋር በጋራ በመሆን በተሰራ ስራ የተሻለ ውጤት መምጣት መቻሉን ገልፀዋል።

የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ እንደገለፁት በተሰጠው አቅጣጫ የሁለቱ ዞን አመራሮች ችግሮችን እንዲፈቱ በተቀመጠው መሰረት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል።በዚህም የሁለቱን ህዝቦች አንድነት ወንድማማችነት ትስስር የሚያጠናክር የቀጠናውን ሰላም ለማምጣት ሊለውጥ የሚችል ስራ መሰራቱን ገልፀው በዚህም በተሰራ የህዝብ ግንኙነት ሰራ ከ62ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማወያየት መቻሉን ገልፀዉ የህግ ማስከበር ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ በበኩላቸው የማእከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት አጠቃላይ በቀጠናው የተሰሩ የህግ ማስከበር ስራዎች በዝርዝር የተገመገመ ሲሆን አቅጣጫ ተቀምጧል በሁለቱ ህዝቦች ጥርጣሬ እንዲፈጠር ሲሰሩ የነበሩ ፅንፈኞ መኖሩን ገልፀዉ ከሁለቱም ዞኖች የአመራር ድክመት መኖሩን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው የሁለቱን አጎራባች ህዝቦች ለመለየት የመሳሪያ ነጋዴዎችና ፅንፈኞች ላይ በተሰራ የህግ ማስከበር በሁለቱም በኩል በተሰራው ስራ ችግሮች እንዲፈቱ አመራር በአዲስ የማደራጀት በተሰራ ስራ የህዝባችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል ።

መረጃው የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው።