Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 173.42K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 406

2022-05-13 11:55:54
በባለሙያ እና በመሳሪያ የተደራጀ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ
የብሬስ ህክምና ለማስጀመር ነፃ የማማከር አገልግሎት እና የአከፋፈል መንገድ
ለተማሪዎች ልዮ ቅናሽ( መታወቂያ መያዝ እንዳይረሱ )
ሁሉንም ህክምና በተመጣጣኝ ዋጋ እንሰጣለን
ቁጥር 1- 4ኪሎ ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ ላይ
ቁጥር 2- ኮተቤ 02 ጆሲ ሙል ላይ
ለበለጠ መረጃ  በ0911-42-42-42
0970-51-71-51 ይደውሉልን
በቲሊግራም - https://t.me/shalomdentalclinic
Face book- @shalomdentalclinic
10.7K views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 01:53:42
በከፍተኛ ርብርብ የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ውሏል።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ኢንዱስትሪ መንደር ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት አካባቢ ተፈጥሮ የነበረው የእሳት አደጋ በ ሎሚ ሜዳ ወጣቶች፣በፌዴራል እና አዲስ አበባ ፖሊስ እንዲሁም በ አዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ ባለሙያዎች ከፍተኛ ርብርብ በ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
6.7K views22:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 00:59:48
ቃጠሎስ በተውስነ መልኩ ቀንሷል አሁንም እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ህዝቡና የእሳት አደጋ ሰራተኞች በርብርብ ላይ ናቸው::
8.3K views21:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 00:13:22
የእሳቱ እስካሁን አልጠፋም

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ኢንዱስትሪ መንደር ከፍተኛ የእሳት አደጋ የተነሣ ሲሆን ቃጠሎው ተባብሶ በርካታ ሼዶችንና መጋዘኖችን ሙሉ በሙሉ አጥፍቷል።

የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ መኪኖችና አባላት በቦታው የተገኙ ቢሆንም ቦታው አመቺ ባለመሆኑ አደጋውን መቀነስ ባይቻልም ከአካባቢው ወጣቶች ጋር በመተባበር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛሉ።

የወረዳው ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጽ/ቤት እንደገለጸው እሳቱ አሁንም ድረስ ያልጠፋ ሲሆን አሁን ባለው መረጃ ከሦስት በላይ ሼዶች ተቃጥለዋል።
10.8K views21:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 00:01:09
አዲስ አበባ ኮልፌ ኢንዱስትሪ መንደር የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል በቃጠሎ እስካሁን በሰውና በንብረት ላይ የደረሰው አደጋ አልታወቀም ብዛት ያልቸው የእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪኖች እሳቱን ለማጥፋት እርብርብ በማድረግ ላይ ናቸው::
11.4K views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 22:16:37
ሕወሓት የትግራይ ወጣቶችን ለጦርነት መመልመሉን ቀጥሏል - አን ፊትዝ-ጌራልድ (ፕ/ር)

ሕወሓት የትግራይ ወጣቶችን ለጦርነት መመልመል መቀጠሉን የካናዳ ዊልፍሪድ ላውሪየር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር አን ፊትዝ-ጌራልድ ገለጹ።

ቡድኑ በአማራና አፋር ክልሎች ከሚገኙ አካባቢዎች ሙሉ ለሙሉ ለቆ አልወጣም ብለዋል።

የካናዳ ዊልፍሪድ ላውሪየር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሯ አን ፊትዝ-ጌራልድ (ፕ/ር) ሕወሓት በአሳዛኝ ሁኔታ የትግራይ ወጣቶችን ለጦርነት መመልመሉን ቀጥሏል፤ ይህም በዜጎች ላይ የጣለው እገዳና ግዴታ ነው ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩትን መረጃ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል። ቡድኑ አሁንም በአማራና አፋር ክልሎች የሚገኙ ቦታዎችን እንደያዘም አመልክተዋል።

የተናጠል ሰብአዊ ተኩስ አቁም ውሳኔ ያሳለፈው የኢትዮጵያ መንግሥት እንጂ ሕወሓት አይደለም ያሉት ፕሮፌሰሯ ተኩስ አቁሙ በሁለቱም ወገኖች ሊከበር ይገባል ብለዋል።
23.7K views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 22:09:04
ልዩ መረጃ

ከሀዲው እና በአማራ ስም የሚነግደው ካሳ ተክለብርሀን አማራን ለሁለተኛ ጊዜ ሊሸጥ መሆኑ በውስጥ መረጃ ተደሰበት ።ከዚህ በፊት ወልቃይት እና ሁመራ የትግራይ ነው ይህ በህገመንግስቱ የተዘጋ ነው ብሎ በአማራ ላይ ሲያላግጥ የነበረው ካሳ ተክለብርሀን ዛሬም እንደለመደው አማሮችን ማታለሉን ቀጥሏል። የአማራ ህዝብ በህልውና ዘመቻ በእጁ ያስገባቸውን ያባቶቹን ርስት ወልቃይት እና ጠገዴን ለህወሀት (ለትግራይ ) መልሱ እና ላስታርቃችሁ ፥አንድ ሁኑ፣ አማራና ትግራይ ድሮም አንድ ናቸው ። ዛሬም ይህ አንድነታችሁ እንዲጠናከር እና በፍቅር ለመኖር ከያዛችሁት የወልቃይት እና ሁመራ መሬት ለትግራይ አስረክባችሁ ውጡ በማለት የማጭበርበር ስራ እየሰራ እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ገልፀዋል።

ይህ ካሳ ተክለብርሀን የሚባል ጉድ የአማራን ህዝብ ስንቴ ይሆን የሚበድለው? ስንቴ ይሆን የሚያጭበረብረው ?የድሮው አልበቃ ብሎት ዛሬ ደግሞ በደም መስዋዕትነት የተያዙትን ወልቃይት እና ጠገዴን ለትግራይ አስረክቡና ላስታርቃችሁ ሲል ምንም ይሉኝታ እንኳን አይነበብበትም ብለዋል ውስጥ አዋቂዎቻችን።

https://t.me/NatnaelMekonnen21
23.4K viewsedited  19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 21:58:02
ፊንላንድ እና ሩስያ ... ሌላኛው የዓለም ስጋት !

" ፊንላድ NATOን ከተቀላቀለች የአፀፋ እርምጃ እንወስዳለን " - ሩስያ

የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ምንም ሰላማዊ መፍትሄ ሳያገኝ ወራትን ያሳለፈ ሲሆን ጦርነቱ ለሺዎች ሞት ፣ ለሚሊዮኖች መፈናቀል፣ ለመላው ዓለም የከፋ የኢኮኖሚ መናጋት ምክንያት ሆኗል።

ሩስያ ከዩክሬን ጋር ጦርነት ከገጠመችበት አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት NATOን እቀላቀላለሁ ማለቷ እንደነበር አይዘነጋም።

ከዩክሬን ጦርነት በኃላ ሩስያ ፥ ፊንላንድ እና ስውዲን NATOን ለመቀላቀን ብታስቡ እጅግ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ] ይኖራል ስትል አስጠንቅቃቸው ነበር።

በኃላም ሀገራቱ NATOን ለመቀላቀል ለማመልከት መወሰናቸውን ተከትሎ ሌላ ውጥረት አንግሷል።

በዛሬው ዕለት ይፋ በሆነ መረጃ ፊንላንድ ያለምንም መዘግየት NATOን ለመቀላቀል ለማመልከት እንደምትፈልግ ገልፃለች። ስውዲንም ፊንላንድን ትከተላለች እየተባለ ነው።

ይህ ደግሞ ሩስያን ክፉኛ አስቆጥቷል።

ሞስኮ ፊንላንድ NATOን ለመቀለቀል ያሳየችውን ፅኑ ፍላጎት እና ዝግጁነት " ቀጥተኛ ስጋት " ስትል የጠራችው ሲሆን " ወታደራዊ-ቴክኒካል " እርምጃዎችን ጨምሮ አፀፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ አስፈራርታለች።

የዩክሬንና ሩስያ ጦርነት አንዳች መፍትሄ ባላገኘበት ሁኔታ ሌላ ዓለም አቀፋዊ ውጥረት እየተፈጠረ ይገኛል ፤ ይህ በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረው ጫና ለታዳጊ ሀገራትና ለመላው ዓለም የሚተርፍ ነው።
23.8K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 20:03:36
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከሶፍሌት ማልታ ኢትዮጵያ ሼር ካምፓኒ ስራ አስኪያጅ ጃን ቦንት ቪቬት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል÷ ብቅል አማራች ካምፓኒው ሶፍሌት ማልታ በኢትዮጵያ እደረገ ያለውን ጥሩ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በመገንዘብ ሚኒስቴር መስሪ ቤቱ ለድርጅቱ የኢንቨስትመንት እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
የሶፍሌት ማልታ ጀነራል ማናጀር ጃን ቦንት ቪቬት በበኩላቸው÷ 60 ሚሊየን ዩሮ ኢንቨስት በማድረግ ከውጪ የሚገባውን የምርት ግብዓት ለመቀነስ ከአርሶአደር ማህበረሰብ ጋር ትስስር በመፍጠር ጥሬ ዕቃዎችን ለማግኘት ዘመናዊ አሰራር ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የቢራ ፋብሪካዎችን የብቅል ፍላጎትን ለመሙላት ሶፍሌት ማልታ ኢትዮጵያ ሼር ካምፓኒ በዓመት ከውጪ ከሚገባው ብቅል 50 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያድንም መግለፃቸውን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
31.1K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 19:25:30
Good News

በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ዓሳ የማርባት ሥራ ተፈቀደ

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የዓሳ ማርባት ሥራ መፈቀዱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የዓሳ ሀብት ልማት ዕድሎችና ተግዳሮቶችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከዘርፉ ባለድርሻዎች ጋር ማክሰኞ ግንቦት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ምክክር ያደረገ ሲሆን፣ በዚሁ ወቅትም ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዓሳ ሀብት ያላት ቢሆንም በተገቢው መንገድ ያልተያዘና ጥቅም ላይ ያልዋለ መሆኑ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት የህዳሴ ግድብን ሳይጨምር በተደረጉ ጥናቶች ኢትዮጵያ በዓመት 94,500 ቶን ዓሳ የማምረት አቅም እንዳላት፣ በግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት አስቻለው ላቀው (ዶ/ር) ገልጸዋል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት እየተመረተ የሚገኘው በዓመት ከ60 ሺሕ ቶን ያልበለጠ ዓሳ መሆኑን አክለዋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ 200 ያህል የዓሳ ዝርያዎች መኖራቸውንና 40 የሚሆኑት በኢትዮጵያ ብቻ እንደሚገኙ ገልጸው፣ ከእነዚህም ውስጥ ስድስቱ ዝርያዎች አሁን ባለው ገበያ ተፈላጊ ናቸው ብለዋል። ነገር ግን ዓመታዊ ምርቱ በቂ ባለመሆኑ የአንድ ሰው ዓመታዊ የዓሳ ፍጆታ ግማሽ ኪሎ ግራም በታች መሆኑን ጠቁመው፣ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች የአንድ ሰው ዓመታዊ የዓሳ ፍጆታ እስከ 12 ኪሎ ግራም መድረሱን ተናግረዋል። በመሆኑም ያሉትን ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ የውኃ ሀብቶች በመጠቀም የተሻለ የቁጥጥር ሥርዓት ሊኖር እንደሚገባ አክለዋል።

ሪፖርተር
32.9K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ