Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 173.42K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 404

2022-05-13 19:48:43
#AddisAbaba

የፓርኪንግ ብቃት ማረጋገጫ በወሰዱ ከ200 በላይ የህንፃ ስር ፓርኪን አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ፍተሻ ተካሄደ።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የህንፃ ስር ተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ስፍራውን ለታለመለት አላማ ማዋለቸውን ለመለየት በ214 ህንጻዎች ላይ ፍተሻ አድርጓል።

በተካሄደው ፍተሻ ከ214 ህንፃዎች ውስጥ ፦

86 (40.2%) የህንፃ ስር ፓርኪንግ አገልግሎት ስፍራውን ለታለመለት አላማ ማዋላቸው ተረጋግጧል።

74 (34.6) ህንፃዎች ከታለመለት ዓለማ ውጭ በከፊል ለሌሎች አገልግሎቶች ማዋላቸው ተረጋግጧል።

54ቱ (25.2%) ህንፃዎች ለምን አላማ እንዳዋሉ ማወቅ አልተቻለም ተብሏል።

የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታውን በከፊል ለሌላ አገልግሎት የቀየሩት ፦

ለውኃ ታንከርና ጀነሬተር ማስቀመጫ፣
ለእቃ ማከማቻ፣
ለቢሮ አገልግሎት፣
ለንግድ ስራ፣
ለቆሻሻ ማጠራቀሚያ እና ተረፈ ምርት ማከማቻ እና ለሌሎች ያልታወቁ አገልግሎት የዋሉ መሆናቸው ተረጋግጧል።

በ11ዱም ክ/ ከተማዎች የህንፃ ስር ፓርኪንግ ብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷቸው ለሌላ አገልግሎት ያዋሉ ተቋማት ላ እርምጃ ለመውሰድ ኤጀንሲው እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
10.1K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 19:20:29

12.5K views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 18:34:33 ግንቦት 05/2014 ዓ/ም

ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
***
ወራሪዉ የትግራይ አሸባሪ መንጋ ኃይል ወልቃይት ጠገዴንና አከባቢውን ከ16 ዓመት ታዳጊ ጀምሮ እስከ 70 ዓመት አዛውንት የሆነ ማንኛውንም ትግራዋይ፤ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብን እንዲወር የክተት አዋጅ አውጇል።

ማንነታችን እንደ ወንጀል ተቆጥሮ የአማራ ተወላጅ የሆነ ሁሉ በየሄደበት እንደ ዶሮ አፍኖ በመሰወር፣ በመግደል፣ አካልን በማጉደል፣ ከሰማይ በታች ከመሬት በላይ አለ የሚባል ግፍ ሁሉ ተፈፅሞብናል። በሺዎች የሚቆጠሩ ታሪክ አዋቂዎች፣ ስለ ህዝብ መብት ተከራካሪ የሆኑትን የሀይማኖት አባቶችን የት እንደደረሱ ሳይታወቅ ደብዛቸው ጠፍቷል።

ስለሆነም በኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል፣ በአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እንዲሁም ሚሊሻና ሌሎች የፀጥታ አካላት ጥምር ተጋድሎ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማህበረሰብ ነፃ ወጥቷል። ይህ የትናንት አኩሪ ገድላችን ነው።

መላው የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ ሆይ!!

ወራሪውና ተስፋፊው የትግራይ ኃይል ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ህልውናህን ሊያጠፋ ቆርጦ ተነስቷል። በመሆኑም በጠላት ዝግጅት መጠን ልክ በተጠንቀቅ እንድትቆም የወቅቱ አስገዳጅ ሁኔታ ሆኗል።

የተከበርከው የአማራ ህዝብ ሆይ!!

በህብረት፣ በአንድነት፣ በፅናት ስለታገልክ የስርዐት ለውጥ አምጥተኃል። ነፃነትም አግኝተኃል። ይሁን እንጂ ድጋሚ ህልውናህን ሊያጠፋ ከመላ ትግራይ የከተተ ወራሪ ኃይል በይፋ ጦርነት አውጆብኃል።

የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!!
የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የትግራይ ተስፋፊ ኃይል ባወጀው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብቷል። ከአሁን በፊት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ስቃዩ ስቃዬ፣ በደሉ በደሌ ነው ብለህ ከፍተኛ ዋጋ ከፍለኃል። ይህን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ያደንቃል እውቅናም ይሰጣል። ኃብት ማፍራት ይሁን በህይወት መኖር መኖርም አገር ሲኖር ነውና፤ ይህንን አገር አጥፊ ወራሪ ቡድን ለመመከት በምናደርገው ተጋድሎ ከጎናችን እንድትቆም ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

ይህንን የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ጥሪ ተቀብያለሁ የሚል ሁሉ የአንድ ወር ስንቅ በማዘጋጀት በየቤቱና በየቀበሌው ሆኖ ለምናቀርበው የፈጥነህ ድረስ ጥሪ ዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ ሲል ኮሚቴው መልዕክቱን ያስተላልፋል።

''ከአማራነታችን ዝቅ የሚያደርገን ምድራዊ ኃይል የለም!!''

የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ አየለ
17.9K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 16:41:53
ትግስት ተስማ የተባች ልጃችን ትምህርትቤት እንደወጣች አልተመስችም
እባካችሁ ያያችሁት በሉዕል እግዚአብሔር ስም በዚህ ስልክ አሳውቁን ወረታውን እንከፍላለን ቤተሰቦቻ
0910988234
0911865666
0911699034
ቄራ አካባቢ ቀን 03/9/14
3.4K views13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 15:57:26
አንድ የውጪ ሃገር ዜግነት ባለው ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
በብርበራው ከ71 ሺህ ብር በላይ የኢትዮጵያ ብር መያዙንም ነው ያስታወቀው።
ግለሰቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው 24 ኮንዶሚኒየም ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለ 3 ወለል ፎቅ ተከራይቶ የሚኖር መሆኑን ገልጿል።
 
ተጠርጣሪው ግለሰብ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎችን እየተቀበለ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራትን ሲፈጽም እንደነበር ከህብረተሰቡ ጥቆማ ማግኘቱንም ነው የገለጸው።
ጥቆማውን መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ተቀናጅተው ባደረጉት ክትትል ግንቦት 4 ቀን 2014 ዓ.ም በግለሰቡ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ በመኝታ ክፍል ውስጥ የተገኘ 5 ሺህ 335 የአሜሪካ ዶላር፣ 380 ዩሮ፣ 1 ሺህ 435 የቻይና የን እና ሌሎች የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦችን ጨምሮ 71 ሺህ 635 የኢትዮጵያ ብር መያዙን ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
10.9K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 15:40:59
በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ ስርቆት በፈፀሙና ጉዳት ባደረሱ ግለሰቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ ስርቆት በፈፀሙና ጉዳት ባደረሱ 20 ግለሰቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በአገልግሎቱ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አበበ ተስፋ÷ 20 ተከሳሾች ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጦ ከ6 ወር እስከ 12 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑንና ቀሪዎቹ ክሶች በሂደት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የቅጣት ውሳኔ…

https://www.fanabc.com/በኤሌክትሪክ-መሠረተ-ልማት-ላይ-ስርቆት-በ/
12.4K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 15:40:39
Tedsport ቴድ-ስፖርት Tedsport

መልካም ዜና! ቦርጭን ባጭር ጊዜ!

SWEAT MAKER
(ውፍረት እና ቦርጭን መቀነስ ፈልገዋል?)

በእንቅስቃሴ ወቅት የሰውነት ሙቀት በመጨመር ውፍረትን ባጭር ጊዜ ይቀንሳል
በትንሽ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ካሎሪ ያቃጥላል
ሆዳችን ላይ ያለን ስብ (Fat) በማቅለጥ ያማረ የሆድ ቅርፅ ያላብሰናል

ያሉበት በነፃ እናደርሳለን
(1200ብር 0961276575 @theo41)

አድራሻ
ቁ-1: ቦሌ ት/ቤት ፊት ለፊት አለምነሽ ፕላዛ ምድር ላይ ሱ.ቁ - 014
ቁ-2:ቦሌ(አትላስ) ግሬስ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ ላይ

ሌላ እቃ https://t.me/tedtechofficial
11.8K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 14:37:43
#Ethiopia : "ለአገሩ ነፍሱን ሳይሰስት የሰጠን ወታደር በአካል ስመለከት እግሬ እየተላጠ ህመሙን ተቋቁሜ ለአገሬ ሮጥኩ ብዬ ማውራቴን አፈርኩ!" -

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ

ኢዜአ
17.1K views11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 14:12:49
ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ዛሬ አርብ በ73 ዓመታቸው ማረፋቸው ተሰምቷል ዩኤኢ የፕሬዝዳንቷን ሞት ተከትሎ ለቀጣዮቹ 40 ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ወስናለች

ጽህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ ሼክ ኸሊፋ በማረፋቸው ማዘኑን በመግለጽ ለተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ለአረብ እና ለተቀረው ዓለም መጽጽናናትን ተመኝቷል፡፡
18.8K views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 14:02:25
በኬሌ ከተማ በተከሰተው የእሳት አደጋ ቤቶች መቃጠላቸው ተገለጸ

በአማሮ ልዩ ወረዳ በኬሌ ከተማ አስተዳደር በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ አንድ ምግብ ቤት ሙሉ ለሙሉ እና 3 ቤቶች ደግሞ በከፊል መውደማቸውን የከተማው ፖሊስ አስታውቋል።

የኬሌ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኢንስፔክተር ጌታነህ ተስፋዬ ትላንት በግምት ከቀኑ 4:30 በንግድ ባንክ አካባቢ አቶ ባይሳ ካሌብ በተባለ ግለሰብ ሱቅ ቤንዚል ሲቀዳ ከሙቀት ጋር ተያይዞ ድንገተኛ የእሳት አደጋ እንደተነሳ አስረድተዋል፡፡

ተመሳሳይ አደጋ ሲከሰት ይህ ለ3ኛ ጊዜ እንደሆነ ያስታወሱት ዳይሬክተሩ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰባቸውን የወረዳው ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።
19.0K views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ