Get Mystery Box with random crypto!

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ | Natnael Mekonnen

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ኢንዱስትሪን ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጡ።

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከተመሰረተ በርካታ ዓመታትን ያሳለፈው የመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘመኑ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ለማድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀው፣ የፋብሪካው ግንባታ ለሀገርና ለተቋሙ የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢንዱስትሪው በአዲስ መልኩ ከተደራጀ በኋላ በተሰሩት ስራዎች ከኪሳራ ወደ ትርፋማነት መሸጋገሩን የገለፁት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የኮርፖሬሽኑ አመራርና አባላቶች ለነበራቸው ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ተቋሙ የራሱን ገቢ በማመንጨት ለሰራዊቱ መሰረታዊ ጥቅም ለማሟላት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የሰራዊቱን የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለማድረግና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በኢንዱስትሪ ፤ በግብርና ፣ በማዕድንና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ለመስራት የተቀመጠው አቅጣጫ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።

የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ሀይለማርያም የመከላከያ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ከሽርሽር ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመሆን የሚገነባው መሆኑን ተናግረዋል።

ኢንዱስትሪው በሰላሳ ሄክታር ላይ የሚያርፍና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ መታቀዱንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

አለም አቀፍ ስታንዳርዳቸውን ያሟሉ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ከመገጣጠምና ከማምረት ባለፈ በቀጣይ ፕሮጀክቱን የማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸው የገለፁት ዳይሬክተሩ ለፕሮጀክቱ ስኬት ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

በዝግጅቱ ላይ የመከላከያ ሚንስቴር ዲኤታ አቶ ቶማስ ቶት የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ ወታደራዊ አታሼዎችና ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች ተገኝተዋል።