Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 173.42K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 398

2022-05-17 14:23:22
የማዕከላዊ ዕዝ በሀገራችን ሉዓላዊነት ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩ አሸባሪዎችን መደምሰስ በሚያስችል ወታደራዊ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተለገፀ። FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

#Ethiopia : ማዕከላዊ ዕዝ "ስልጠና ለተሻለ የግዳጅ አፈፃፀም" በሚል መርህ በተሠጠው የአመራር ስልጠና በምንም የማይበገር አዋጊና ተዋጊ አባላት ማፍራት እንደተቻለ የዕዙ ዋና አዛዥ ሌ/ጀኔራል ዘውዱ በላይ አረጋግጠዋል።

"በሳል አመራር ብቁ ተዋጊ የሠራዊት አባላትን ለማፍራት አይቸገርም።" ያሉት ጀኔራል መኮንኑ የማዕከላዊ ዕዝ አመራሮች የሠራዊቱን ሞራላዊና ስነ ልቦናዊ ዝግጁነት በመገንባት ለማንኛውም ግዳጅ ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።

"ዕዙ በአሁኑ ሰዓት የታጠቀው መሣሪያ ብቻ ሳይሆን የአሸናፊነት ስነ ልቦና ጭምር ነው" ያሉት ደግሞ በዕዙ የኮር ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል ተስፋዬ ረጋሳ በስልጠና የተገኘውን የተሟላ ዝግጁነት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

የማዕከላዊ ዕዝ በተሰጠው የግዳጅ ቀጣና በሀገራችን ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩ አሸባሪዎችን መደምሰስ በሚያስችለው አስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።
37.2K views11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 14:20:26
በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሽብርተኛነት የተፈረጀዉ የሸኔ ቡድን ባስከተለው የፀጥታ ችግር በዘጠኝ ወረዳዎች በርካታ ሰዎች ከቤት ንረብታቸው ከመፈናቀላቸውም ባለፈ ለረሃብ እና ለድርቅ ተዳርገው ቆይተዋል፡፡ ሆኖም አሁን ላይ የሸኔ ቡድን አባላት ለመንግስት እጅ እየሰጡ በመሆኑ በዞኑ የፀጥታው ሁኔታ በከፊል መሻሻሉ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም በዞኑ ከ23ሺ ኩንታል በላይ ይጠበቅ የነበረዉ ምርት በተከሰተው ድርቅ የተነሳ ሙሉ በሙሉ በመውደሙ የአካባቢው ማህበረሰብ ለረሀብ አደጋ መዳረጉ ይታወሳል።የመጣዉን አንጻራዊ መረጋጋት እና ወቅቱ የግብርና ስራ የሚከናወንበት በመሆኑ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው ተመልሰው እርሻቸው እያረሱ እንደሚገኝ የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ሀላፊ አቶ ዮሀንስ ወርቁ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ማረስ ላልቻሉና አቅም ላጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የክረምት ወቅት በመምጣቱ መንግስት እርዳታ በማድረግ እርሻቸው እንዲታረስ እያደረገ መሆኑንም ኃላፊው አክለዋል፡፡አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች የሰላሙ ሁኔታ የተረጋጋ ባለመሆኑ ተፈናቃዮች በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ሲሆን ተገቢዉ ድጋፍ እየደረሳቸዉ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ በዞኑ በረሃብ የተነሳ የተመዘገበ ሞት ባይኖርም ከ459 ሺ በላይ ሰዎች ለረሃብ እና ድርቅ መጋለጣቸውን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።
33.8K views11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 14:07:46
ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ዐዋጅ ቁጥር 1133/2011 እና በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ ኃላፊነት ተሰጥቶታል።
በዚሁ መሠረት በእነ ዶ/ር አዲሱ መኮንን “አገው ለፍትሕና ዲሞክራሲ ፓርቲ (ፍትሕ)” በሚል ስያሜ የክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባ ጥያቄ ያቀረቡ በመሆኑ በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀፅ 68 ንዑስ አንቀፅ ሁለት እና ሦስት መሠረት በፓርቲው ስም፣ ዐርማ ወይም ሌሎች ጉዳዮች ተቃውሞ ያለው ሰው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከዛሬ ግንቦት 09 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን ለቦርዱ ጽሕፈት ቤት እንዲያቀርብ ቦርዱ ሳስባል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 09 ቀን 2014 ዓ.ም.
31.8K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 13:01:18 ከሰሞኑን በአሶሳ ከተማ ውስጥ በግለሰቦች ቤት በተደረገ ፍተሻ የተከማቸ 50 በርሜል ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የአሶሳ ከተማ ፖሊስ ለኢዜአ በሰጠው ቃል ፤ በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸው 50 በርሜል ነዳጅ (ቤንዚን እና ናፍጣ) ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በህብረተሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድቷል።

በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በከተማው #ቤንዚን እና #ናፍጣ በጥቁር ገበያ በሊትር እስከ 200 ብር እየተሸጠ መሆኑን ፖሊስ የጠቆመ ሲሆን የዚህ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ምንጭ በህጋዊ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች ተቀድቶ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ጥቂት ግለሰቦች እጅ መግባት መሆኑን አስረድቷል።
32.5K views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 13:00:29
"በሱዳን የተወሰደው ግዛታችን በየትኛውም መመዘኛ ይመለሳል" - አቶ ደመቀ መኮንንሱዳን የህዝብ ስብጥርን (ዴሞግራፊ) ለመቀየር መሰረተ ልማትን እየገነባች ነውም ተብሏል

በሱዳን የተወሰደው የኢትዮጵያ ግዛት "በየትኛውም መመዘኛ" እንደሚመለስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ኢትዮጵያ ያላት የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ላይ ያተኮሩ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን የኢትዮጵያ እና ሱዳን አሁናዊ ግንኙነት ላይም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
31.1K views10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 13:00:17
የጆሮ የመስማት አቅም ማነስ ድምፅን ከሩቅ ለመስማት እንዳነቸገር 0911284905 ይደውሉል
HEARING AID
በተመጣጣኝ ዋጋ 6800birr ከ 2 አመት ዋስትናጋ
ይደውሉልን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን

-በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ላለ የሚሆን
-በዛላይ ለአደራረግ እና ቢታይ ቀለል ያለ
-ለሁለቱም ጆሮ ለሚፈልጎ ማድረግ የሚችሉት
-ቻርጅ ተደርጎ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ
-እራሱላይ ፓወር ባንክ ያለው

በተለያያ ምክንያት በአደጋም በተፈጥሮ ለሚከሰት የመስማት ችግር ላጋጠማቸው

ተጨማሪ የማዳመጫ መሳሪያ ይዘንላቹ ቀርበናል
ይዘዙ ከፃን እስከ አዋቂ መጠቀም ይችላሉ ክፍለ ሀገር አንልካለን አዲስ አበባ በነፃ እናደርሳለን
28.7K views10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 12:59:58
Tedsport ቴድ-ስፖርት Tedsport

መልካም ዜና! ቦርጭን ባጭር ጊዜ!

SWEAT MAKER
(ውፍረት እና ቦርጭን መቀነስ ፈልገዋል?)

በእንቅስቃሴ ወቅት የሰውነት ሙቀት በመጨመር ውፍረትን ባጭር ጊዜ ይቀንሳል
በትንሽ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ካሎሪ ያቃጥላል
ሆዳችን ላይ ያለን ስብ (Fat) በማቅለጥ ያማረ የሆድ ቅርፅ ያላብሰናል

ያሉበት በነፃ እናደርሳለን
(1200ብር 0961276575 @theo41)

አድራሻ
ቁ-1: ቦሌ ት/ቤት ፊት ለፊት አለምነሽ ፕላዛ ምድር ላይ ሱ.ቁ - 014
ቁ-2:ቦሌ(አትላስ) ግሬስ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ ላይ

ሌላ እቃ https://t.me/tedtechofficial
26.7K views09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 12:59:31
ለ 3 ቀን ብቻ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ ከ @habmartofficial

አዳዲስ ዘመናዊ ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ከ HABMART :: ከሙሉ አክሰሰሪ እና ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር

REDMI 9A ( 64/4gb ) … 10,800br

A51 5g (128/6gb )….. 17,000br
A71 5g (128/8gb )….. 19,500br
A90 5g (128/6gb )…. 16,000br

Iphone X 256gb … 25,500br
Iphone 11 128gb …. 37,000br

Note 10+ 5g ( 256gb/12gb )… 29,000br

Redmi note 7 pro (128/6gb )… 14,500br
Redmi note 9 ( 128/4gb )…. 16,000br
Redmi note 10 pro (128/6gb 108mp camera ) … 18,800br
Redmi note 10 ( 128/6gb )…. 16,900br

ሌሎችም አሉን ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን 0913849228 @habworld
Join our channel for more products @habmartofficial

ቦሌ መድሃኒአለም Selam city mall, 3rd floor
ልደታ AIA የገበያ ማዕከል , ground floor
26.5K views09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 12:51:59
ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞን በተመለከተ !!!

#Ethiopia : የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ በሰሞኑ በተለያዩ ሚድያዎች በስራ ቆይታቸው የነበሩ ተግዳሮት እና ፈተናዎች ያሏቸውን ሲያጋሩ መቆየታቸው ይታወቃል። እናም ከትላንትና ምሽት ጀምሮ ጀኔራሉ ወደ ቤታቸው እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ አለመመለሳቸውን እና ስልክም እንደማይመልሱ ባለቤታቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ጠቅሰው በማህበራዊ ሚድያ እየተስተጋባ እያየን እንገኛለን ፤ ይህን ሚድያ ከተቆጣጠረው አብዝሃኛው ምንም እንኳን የጀኔራሉ ህይወት እና ደህንነት የሁላችነም ፍላጎት እና ሃሳብ ቢሆንም ሃገር አፍራሽ ግለሰብ እና ተቋማት ዜናውን ወደ አመፅ እና ሰልፍ መቀስቀሻ እየተጠቀሙበት ይገኛል።

ስለዚህ መንግስትን
»ለሀገራችን ሰላም ስንል
» ለጀኔራሉ ደህንነት ስንል
» ለህዝባችን መረጋጋት ስንል የሚከተለውን ጥያቄ እንጠይቃለን !!!

1ኛ ጀኔራሉ በመንግስት ደረጃ በህግ ጥላ ስር ካሉ ተጠርጥረው የተያዙበትን ምክኒያት ጠቅሶ ደህንነታቸውን እና ያሉበትን የጤንነት ሁኔታ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ

2ኛ ከጄኔራሉ መታፈን እና መጥፋት ጀርባ የመንግስት ቀጥተኛ እጅ ከሌለበት እና በመንግስት ጥላ ስር ካልሆነ " ጀኔራሉን መንግስት እንዳላሰራቸው " በማንኛውም መንገድ መግለጫ በመስጠት ሀገር እና ህዝብን እንዲያረጋጋ እንድሁም የጀኔራሉን ያሉበትን ሁኔታ ከህዝብ ጎን ሆኖ ደህንነታቸውን እንዲያስጠብቅ እንጠይቃለን !!!

ይህ መሆን ሲችል ሀገር አፍራሹ ቡድን ያቀደው ሴራ ከሽፎ ሀገር ሰላም መሆን ትችላለች !!!
27.5K views09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 12:43:29 ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ አበባ ውስጥ ከቤታቸው እንደወጡ አለመመለሳቸውን ባለቤታቸው ገለፁ

የ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የትዳር አጋር ወ/ሮ መነን ስለ ባለቤታቸው ሲናገሩ ትናንት ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው 5፡15 አካባቢ የወጡት ከጓደኛቸው ጋር ቀጠሮ እንደነበራቸው ገልፀው መሆኑን ያስረዳሉ።

ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤታቸው ባለመመለሳቸው ደጋግመው ወደ ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ቢደውሉም ምላሽ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።

ጄኔራል ተፈራ ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም በቅርቡ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው መስራታቸው ይታወሳል ።

እንደ ወ/ሮ መነን ገለፃ ከሆነ ጄኔራል ተፈራ ያገኟቸው ሰዎች በዕለቱ አስከ 10 ሰዓት ድረስ አብረው መቆየታቸውን እና ከዚያ በኋላ እንደተለያዩ ነግረዋቸዋል።

ከዚያ በኋላ ግን የደረሱበትን ለማወቅ እንዳልቻሉ ባለቤታቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ጄኔራል ተፈራ ሞሞ ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥነት ከተነሱ በኋላ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ በመቅረብ አስተያየታቸውን ይሰጡ ነበር።

ወ/ሮ መነን የባለቤታቸውን መጥፋት አስመልክቶ ወደ ፌደራል ወንጀል ምርመራ እንዲሁም አዲስ አበባ ፖሊስ በመሄድ ቢጠይቁም ግለሰቡ "በቁጥጥራቸው ስር እንደማይገኝ" እንደገለፁላቸው ይናገራሉ።

በአሁኑ ሰዓትም ባለቤታቸውን ለማግኘት ሊኖሩበት ይችላሉ ወደተባሉ የተለያዩ የደኅንነትና የፀጥታ ተቋማት በመሄድ ፍለጋቸውን መቀጠላቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ናቸው።

ጄኔራል ተፈራ የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውን የገለፁት ባለቤታቸው የታዘዘላቸውን መድኃኒት እየወሰዱ አንደነበር አመልክተው፣ መድኃኒታቸውን ካልወሰዱ አንደሚታመሙ በመጥቀስ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከሚኖሩበት ባሕርዳር ወደ አዲስ አበባ የመጡት በእግራቸው ውስጥ የሚገኙትን ጥይቶች በተመለከተ የሕክምና ክትትል ለማድረግ እንደነበረም ጨምረው አስረድተዋል።

"እስሩን ለምዶታል ያለፈበትም ነው፤ የሚያሳስበን የጤናው ሁኔታ ነው" ብለዋል።

የጄነራሉን መሰወር በተመለከተ የፌደራልም ሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስካሁን ያሉት ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባል ሆነው ለዓመታት በከፍተኛ መኮንንነት ያገለገሉት ብርጋዲዬር ጄነራል ተፈራ ማሞ ከአስር ዓመት በፊት መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ አሲረዋል በሚል ከሌሎች ጋር ተከሰው ለዓመታት በእስር ላይ ቆይተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎም ከእስር ተለቀው በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በቅርቡም የህወሓት ኃይሎች ወደ አማራና አፋር ክልሎች በመግባት ጥቃት በሰነዘሩበት ጊዜ የክልሉን ልዩ ኃይል በበላይነት ሲመሩ የነበሩ ሲሆን፣ ከጥቂት ወራት በፊት ደግሞ ከዚሁ ኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጋቸው ይታወሳል።

Via BBC
29.6K views09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ