Get Mystery Box with random crypto!

TPLF ወልቃይትን ይቅርና በትግራይ ክልል መከላከያ ይዞት የነበረን 1 ኢንች መሬት በጦርነት መያዝ | Natnael Mekonnen

TPLF ወልቃይትን ይቅርና በትግራይ ክልል መከላከያ ይዞት የነበረን 1 ኢንች መሬት በጦርነት መያዝ አይችልም። ጦርነት ከፍቶ አንድ ኢንች መሬት ልያዝ ካለ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ለመጣሱ ማረጋገጫ ይሰጣል። የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት TPLF ጦርነት እንዲከፍት አይደለም ትጥቅ እንዲኖረው አይፈቅድለትም። የስምምነት አስኳሉና ቀዳሚው ጉዳይ ተኩስ ማቆም ትጥቅ መፍታት ነውና።

TPLF ይህን የሰላም ስምምነት ላለመፈፀም ያለውን ትጥቅ ይዞ ለመቀጠል ቀድሞ በእኔ ስር ለነበሩት ለወልቃይት ወይም ለራያ መሬት ነው ጦርነት የምከፍተው ችግሬ ከአማራ ክልል ጋር ነው በሚል እንደለመዱት ሌላውን እንደሞኝና እንደአላዋቂ በመቁጠር ከፋፍሎ የፖለቲካ ወታደራዊ ድል ለማስመዝገብ ጦርነት እከፍታለሁ ብሎ ከገፋበት ግጭቱ በቀጥታ ከፌደራል መንግስቱ ጋር ይሆናል። TPLF ም ራሱን ለማጥፋት በፈቃዱ እንደወሰነ ይቆጠራል።

መንግስት የአማራን የኦሮሚያን የሲዳማን የአፋርን የሶማሌን የቤንሻንጉልን እንዲሁም የሌሎቹን ክልሎች ልዩሃይል ትጥቅ ያስፈታውና የልዩሃይል አባላትን ወደፖሊስ መከላከያ እንዲቀላቀሉ ወይም ምርጫቸውን እንዲከተሉ ያደረገው እነሱ በታጠቀው TPLF ወይም ሌላ አካል እንዲጠቁ አይደለም። ከመከላከያ ጋር ተገዳዳሪ የሆነ ሃይል በአንድ ሐገር ውስጥ እንዳይኖር ነው። እነሱን ትጥቅ አስፈትቶ ለዛውም በሰላም ስምምነቱ ዋና ጉዳይ የሆነውን ተኩስ የማቆምና ትጥቅ የመፍታት ስምምነትና አጀንዳን ደርቦ የትግራይ ክልል እስከ ትጥቁ ይቀጥል ሲፈልግ በተመቸው ጊዜ ጦርነት ይክፈት ሊባል አይችልም። የኢትዮጵያ መከላከያ መቀሌ ሊገባ ጫፍ ደርሶ እንዲቆም የተደረገው በጉልበት አሸንፎ ሁሉንም ነገር ከመቆጣጠር በጉልበት ለተሸነፈው TPLF በ1/5 ጥርነፋ አንድ አይነት መረጃ እየተጋተ ለደገፈው ቁጥሩ ለማይናቅ የትግራይ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ቀጣይ ሁኔታ ጉዳዩን በሰላም መጨረስ የተሻለ ዕድል ይዞ ይመጣል የአሸናፊ ተሸናፊ ትርክት ቀርቶ የኢትዮጵዬ አሸናፊነት ይታወጃል ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ የፖለቲካ ባህል ይገነባል በሚል ነበር።

ከሰሞኑም በራያ በኩል የጦርነት ትንኮሳ ሲደረግ የፌዴራል መንግስቱ መከላከያ ምላሽ ያልሰጠው መላሽ የሚሰጥ ከሆነ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚሆን በመሆኑ አሁንም የጥሞና እና የሰላም ዕድል በተለይ ለትግራይ ሕዝብ የሰላም ፍላጎት ቦታ በመስጠት ነው። TPLF በሁሉም በኩል ላለው የፖለቲካ ኤሊት ከፍተኛ ንቀት ስላለውና ራሱን እንደብልጥ አዋቂ አድርጎ የሚያስብ ከመሆኑ አንፃር በመከፋፈል በተናጠል ቀስ ቀስ እያልኩ የፖለቲካ ወታደራዊ ድል አስመዘግባለሁ ብሎ የሚያደርገው ሙከራ የመጨረሻው ሊሆን ይችላል።