Get Mystery Box with random crypto!

ለፉሲካ በአል ወደ ሀገር እየገቡ ላሉ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት አቀባ | Natnael Mekonnen

ለፉሲካ በአል ወደ ሀገር እየገቡ ላሉ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት አቀባበል እየተደረገላቸው ነው::

በአቀባበል ስነ ስርዓት ላይ የቱሪዝም ሚንስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

“Back to your origins” የሚል ስያሜ የተሰጠው እና ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ በውጭ ለሚኖሩ የ2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ያቀረቡት ጥሪ በሶስት ዙሮች የሚካሄድ ነው::

በዚህም እከታህሳስ 20 እስከ ጥር 30 በመጀመሪያው ዙር ከብዝኃ ባህል መሰረትዎ ጋር ይገናኙ በሚል በተሰየመው መርሃ ግብር ወደ ሀገራቸው ገብተው እንደነበር ይታወሳል።

አሁን ደግሞ ታሪካዊ መሰረትዎን ይወቁ (connect to your historical roots) በሚል በተሰየመው መርሀግብር በሁለተኛ ዙር ወደ ሀገር እየገቡ ይገኛሉ::

በሁለተኛው ምዕራፍ ኢትዮጵያውያን የእረፍት ጊዜያቸውን (Spring Break) ተጠቅመው የሀገራቸውን ታሪክ እንዲያውቁ፣ የአያቶቻቸውንና ቅድመ አያቶቻቸውን አይበገሬነትና መስዋዕትነት
እንዲሁም ከራሳቸው አልፎ ለጥቁር ህዝቦች ነፃነት ያበረከቱትን አስተዋፅዖ አንዲረዱ በማድረግ የሀገር ፍቅር ስሜታቸው እንዲዳብር ብሎም በዚህ አኩሪ
ታሪክ ተነሳስተው በዘመናቸው ፍሬያማ አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ለማስቻል ያለመ ነው::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ትኬት፣ሆቴሎች፣ አስጎብኚ ድርጅቶች የዋጋ ቅናሽ በማድረግ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያኑን ተቀብለው በማስተናገድ ላይ ናቸው::