Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 173.42K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 395

2022-05-20 08:14:13
ለ 3 ቀን ብቻ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ ከ @habmartofficial

አዳዲስ ዘመናዊ ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ከ HABMART :: ከሙሉ አክሰሰሪ እና ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር

REDMI 9A ( 64/4gb ) … 10,800br

A51 5g (128/6gb )….. 17,000br
A71 5g (128/8gb )….. 19,500br
A90 5g (128/6gb )…. 16,000br

Iphone X 256gb … 25,500br
Iphone 11 128gb …. 37,000br

Note 10+ 5g ( 256gb/12gb )… 29,000br

Redmi note 7 pro (128/6gb )… 14,500br
Redmi note 9 ( 128/4gb )…. 16,000br
Redmi note 10 pro (128/6gb 108mp camera ) … 18,800br
Redmi note 10 ( 128/6gb )…. 16,900br

ሌሎችም አሉን ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን 0913849228 @habworld
Join our channel for more products @habmartofficial

ቦሌ መድሃኒአለም Selam city mall, 3rd floor
ልደታ AIA የገበያ ማዕከል , ground floor
30.2K views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 02:10:05
2.8K views23:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 02:00:43
"በትግራይ የሽግግር መንግስት ገለ መሌ የሚሉት በውጭ ያሉ ናቸው። የሽግግር መንግስት ይቋቋም ቢባልስ ማንን ነው የምናስቀምጠው??"

ጌታቸው ረዳ ዛሬ የተናገረው
3.1K views23:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 01:37:02
ጆርጅ ቡሽ በንግግራቸው የሩሲያን ወረራ ከኢራቅ ማምታታታቸው እያነጋገረ ነው በኢራቅ ጦርነት ከሚወቀሱት መካከልም ጆርጅ ቡሽ ቀዳሚው ናቸው

ቡሽ አሜሪካ እ.ኤ.አ በ 2003 ወታደሮቿን ወደ ኢራቅ እንድትልክ ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ሩሲያ `ዩክሬንን ወረረች` በማለት ፋንታ የኢራቅ ስም ማንሳታቸው አለምን እያነጋገረ ነው:: ጉዳዩን አነጋጋሪ ያደረገው ደግሞ እ.አ.አ በ 2003 አሜሪካ ወታደሮቿን ወደ ኢራቅ ስትልክ ትዕዛዙን የሰጡት ቡሽ መሆናቸው ነው፡፡

የ75 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት በአሜሪካ ዳላስ በተዘጋጀ የዴሞክራሲ ውይይት ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲንን ለመተቸት`` ሩሲያ ዩክሬንን ወረረች`` በማለት ፋንታ የኢራቅ ወረራ ብለው ነበር፡፡

ቡሽ ከወቅታዊው የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ጋር በተያያዘ፤ የሩሲያውን ፕሬዝዳንት እያወገዙ ሳለ ነው ስህተቱን የፈጸሙት፡፡ በዳላስ ባደረጉት ንግግር የፈጸሙትን ስህተት ወዲያው ቢያርሙትም መነጋገሪያነቱ ግን ቀጥሏል፡፡ የቀድሞው ፕሬዝዳንት `ምክንያታዊ ያልሆነና ጭካኔ የተሞላበት አንድ ሰው የጀመረው የኢራቅ ወረራ` ካሉ በኋላ የመድረኩ ተሳታፊዎች ሲስቁ ወዲያው ዩክሬን በሚል አስተካክለዋል፡፡ የቀድሞ ፕሬዝዳንት የኢራቅን ስም ከጠሩ በኋላ ዕድሜያቸው 75 ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የተከሰተ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አሜሪካ በኢራቅ አድርጋው በነበረው ጦርነት ከፍተኛ ትችት የሚቀርብባቸው ጆርጅ ደብሊው ቡሽ የኢራቅን ስም ካነሱ በኋላ የ 2003 የጦርነት ትዝታዎች እንደተቀሰቀሱ ነው፡፡

ጦርነቱ በ 2003 ከመጀመሩ አስቀድሞ የቀድሞው የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ሀገራቸው ለአሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸው እንደነበር ከአንድ ማስታወሻ ላይ መገኘቱ ይታወሳል፡፡
3.5K views22:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 00:10:12

5.7K views21:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 22:31:08
ግብፅ ለአራት ወር የሚሆን የስንዴ ክምችት እንዳላት አስታወቀች

ግብፅ ለአራት ወራት የሚሆን የስንዴ ክምችት እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ አስታውቀዋል። ዩክሬን እና ሩሲያ በአለም ከፍተኛ የስንዴ አቅርቦት ፍላጎትን የሚሸፍኑ ሲሆን 80በመቶ ያህል ድርሻ አላቸው።

ሆኖም ግን ባለፈው የካቲት ወር ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ጦርነት መግባታቸውን ተከትሎ የምርት አቅርቦት መስተጓጎል እንዲፈጠር አድርጓል።ዩክሬን ውል ካሰረችው ምርቶች መካከል በከፊል ወደ ፖላንድ በባቡር ለማጓጓዝ ጥያቄ አቅርባ የነበረች ሲሆን ግብፅ የማጓጓዣ ወጪዬን በእጅጉ ይጨምራል ስትል አስታውቃለች።

ግብፅ ከህንድ 500,000 ቶን ስንዴ እየገዛች ቢሆንም የህንድ መንግስት ከተከፈለ የስንዴ ውል በስተቀር ወደ ውጭ ሀገራት ስንዴ እንዳይሸጥ ከልክሏል። በትላንትናው እለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ሩሲያ በዩክሬን ወደቦች ውስጥ የተከማቸ እህል ለውጭ ገበያ እስካልለቀቀች ድረስ በዩክሬን ያለው ጦርነት በአለም አቀፍ ደረጃ የምግብ እጥረት ስጋት እየጨመረ መሆኑን አስጠንቅቀዋል።
16.2K views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 22:29:59
"#ፑቲን እባክዎትን የሚራራ ልብ ካለዎት ወደቦቹን ይክፈቱና ደሃዎችን እንመግብ አስከፊውን ርሃብም እናስቁመው" :- የአለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሌይ

ምእራብያውያን ፑቲንን መለማመጥ ጀምረዋል።

ፑቲን የዩክሬን ወደቦችን ለእህል ጭነት ክፍት እንዲያደርጉ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ጠይቋዋል። ጉዳዩ ብዙዎችን ለርሃብ ከመዳረግም በላይ አለመረጋጋቶችን ሊያስከትልና የህገ ወጥ ስደተኞን ቁጥር ሊያንር እንደሚችል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ፕሮግራሙ ወደቦቹ ካልተከፈቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለከፋ ርሃብ ሊጋለጡ ይላሉ ብሏል፡፡ ይህን አለመፍቀድ በዓለም የምግብ ዋስትና ላይ "የታወጀ ጦርነት" ተደርጎ ይወሰዳልም ብሏል ፕሮግራሙ።እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ዩክሬን ብቻዋን 4 መቶ ሚሊዮን ያህል ሰዎችን ለመመገብ የሚያስችል አቅም አላት ብለዋል።
15.2K views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 22:26:49 ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ስልጣናቸውን በመጠቀም የሕወሓትን አላማ ማስፈጸማቸውን እንዲያቆሙ ተጠየቀ

#Ethiopia : የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ስልጣናቸውን በመጠቀም የሕወሓትን አላማ ለማስፈጸም የሚያከናውኑትን ተግባር እንዲያቆሙ ዘጠኝ ተቋማት ለዳይሬክተሩ በጋራ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ጠየቁ።

ደብዳቤውን የጻፉት የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር፣ የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር፣ ’አሜሪካን ኢትዮጵያን ፐብሊክ አፌርስ ኮሚቴ’(ኤፓክ)፣ ’ኢትዮጵያን ዳያስፖራ ሃይ ሌቭል አድቫይዘሪ ካውንስል ኦን ኮቪድ-19’፣ ’ኢትዮጵያን ስኮላርስ ኢን ኖርዲክ ካንትሪስ’፣ የደቡብ አፍሪካ የሕክምና ማህበር፣ የሌሴቶ ሕክምና ማህበር እና ‘ፒፕል ቱ ፒፕል’ የተሰኙ ተቋማት ናቸው።

በሰሜን ኢትዮጵያ ባለፈው 18 ወር በነበረው ግጭት የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ፖለቲካዊና ግልጽ ወገንተኝነት ያለው አካሄድን መከተላቸውን ተቋማቱ ገልጸዋል።

በንግግርና በድርጊታቸውም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ የተሳሳተና የተዛባ አቋም እንዲይዙ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በሚሰጧቸው መግለጫዎች፣ በሚጽፏቸው ጽሁፎችና በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች ሕወሓት በአማራና አፋር ክልሎች በፈጸመው ድርጊትና በሕዝብ ላይ ባደረሰው መከራ ላይ ዝምታን መርጠዋል ብለዋል።

ሕወሓት በፈጸመው ወረራ በርካታ የጤና ተቋማትን ማውደሙንና መዝረፉን አስታውሰው፤ ቡድኑ ንጹሃንን በመግደልና አስገድዶ በመድፈር ወንጀሎችን መፈጸሙን አመልክተዋል።

ዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ ሕወሓት በክልሎቹ የፈጸመውን ድርጊት በሚያወጡት ሪፖርት እየገለጹ በሚገኙበት ወቅት ዶክተር ቴድሮስ በጉዳዩ ላይ ያሉት ነገር አለመኖር አድሎአዊነታቸው ለአንድ አካል የሚያሳይ እንደሆነ ነው ተቋማቱ በደብዳቤው ላይ የገለጹት።

ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር እንዲሰሩ በተደጋጋሚ ጊዜ ለሚቀርብላቸው ጥሪ ምላሽ አለመስጠታቸው የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል።

ሕወሓት ወደ ትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ እየተደረገ ያለውን ጥረት እያደናቀፈ እንደሚገኝ የጠቀሰው ግልጽ ደብዳቤው፤ ዶክተር ቴድሮስ በአሜሪካ በነበራቸው ጉብኝት ከባለስልጣናትና ከሕግ አውጪ ምክር ቤት አባላት ጋር ያደረጉት ውይይት አላማው በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ለመጎትጎት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ጉብኝቱ የ’ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ሕጎች እንዲጸድቁ ግፊት ለማድረግ መሆኑን እንረዳለን ነው ያሉት ተቋማቱ።

ዶክተር ቴድሮስ የዓለምን ሕዝብ ጤና ለመጠበቅ የተሰጣቸውን ኃላፊነት የሕወሓትን አላማ ለማስፈጸም እየተጠቀሙበት ነው፤ ከዚህም ድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ብለዋል።

አፍራሽ የፖለቲካ እንቅስቃሴና የዘር ውግንናቸውን በመተው በሁሉም ኢትዮጵያውያን ጤና መጠበቅ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ተቋማቱ ጠይቀዋል።

ዘጠኙ ተቋማት በአማራና አፋር ክልሎች በሕወሓት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ በማቋቋምና ሕክምና ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በሥነ ምግባር ጥሰት እንዲጠየቁ በጥር ወር 2014 ዓ.ም ለድርጅቱ የበላይ ጠባቂ ቦርድ የቅሬታ ማመልከቻ ማስገባቱ ይታወሳል።

በማመልከቻው ላይ የኢትዮጵያ መንግስት በዋና ዳይሬክተሩ ላይ የሕግ እና የሙያዊ ሥነ ምግባር እንዲሁም የሞራል ጥያቄዎች እንዳሉት ገልጿል።

ዶክተር ቴድሮስ ለአንድ ወገን የያዙት አድሏዊ አቋም ከፍተኛ ኃላፊነት በያዙበት ቦታ ያላቸውን ሙያዊ ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚከተው በማመልከቻው ላይ ተጠቅሷል።

በኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበውን ቅሬታ አስመልክቶ የዓለም ጤና ድርጅት እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም።
15.7K views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 22:13:29

16.2K views19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 19:39:52 ለሚመለከተው ክፍል ጥቆማ

አቶ ናትናኤል ሰላም ለአንተ ይሁን ዛሬ ለአንተ ለማድረስ የፈለግኩት ጉዳይ ከሳርቤት (ፑሽኪን አደባባይ)ወደ ጎተራ ማሳለጫ የሚወስደው መንገድ ተሰርቶ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለምዶ ከጎፋማዞሪያ ወደ መብራትኃይል እንዲሁም ከጎፋማዞሪያ ወደ ጨርቆስ እየተሰራ ያለው መንገድም በከፊል እየተጠናቀቀ ይገኛል ነገርግን የተሰራው ስራ ጥሩ ቢሆንም በቀጣይ የመንገዱን እድሜ የሚያሳጥር አካባቢውንም ወደፊት በጎርፍ እንዲጥለቀለቅ የሚያደርግ ስራ እየተከናወነ ነው ይህም የመንገዱን ስራ የሚቆጣጠር ሃላፊ የሌለ በሚመስል መልክ አዲስ የተሰሩ የፍሳሽ መስመሮች (ፖሴቲዎች)ከአፍ እስከ ገደፋቸው ድረስ (ሙሉበሙሉ) በኮረትና በድንጋይ እንደተሞላ ክዳን እየተገጠመላቸው ነው ። በአካባቢው በቅርብ ርቀት ላይ ያሉ የወረዳ አመራሮች ሳያዩ ቀርተው ነው ብዬ ለማመን ይቸግረኛል ባለቤቱ ማነው አቶ ናትናኤል ባንተ በኩል መድረስ ከቻለ ክረምት ከመግባቱ በፊት እንዲስተካከል ቢደረግ ። እንደለመደብን ጨረስን ብለን በማግስቱ ወደ ቁፋሮ እንዳንገባ በህዝብና በመንግሥት ገንዘብ መቀለድም እንዳይሆን ብዬ ነው ።
30.5K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ