Get Mystery Box with random crypto!

ለሚመለከተው ክፍል ጥቆማ አቶ ናትናኤል ሰላም ለአንተ ይሁን ዛሬ ለአንተ ለማድረስ የፈለግኩት ጉ | Natnael Mekonnen

ለሚመለከተው ክፍል ጥቆማ

አቶ ናትናኤል ሰላም ለአንተ ይሁን ዛሬ ለአንተ ለማድረስ የፈለግኩት ጉዳይ ከሳርቤት (ፑሽኪን አደባባይ)ወደ ጎተራ ማሳለጫ የሚወስደው መንገድ ተሰርቶ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለምዶ ከጎፋማዞሪያ ወደ መብራትኃይል እንዲሁም ከጎፋማዞሪያ ወደ ጨርቆስ እየተሰራ ያለው መንገድም በከፊል እየተጠናቀቀ ይገኛል ነገርግን የተሰራው ስራ ጥሩ ቢሆንም በቀጣይ የመንገዱን እድሜ የሚያሳጥር አካባቢውንም ወደፊት በጎርፍ እንዲጥለቀለቅ የሚያደርግ ስራ እየተከናወነ ነው ይህም የመንገዱን ስራ የሚቆጣጠር ሃላፊ የሌለ በሚመስል መልክ አዲስ የተሰሩ የፍሳሽ መስመሮች (ፖሴቲዎች)ከአፍ እስከ ገደፋቸው ድረስ (ሙሉበሙሉ) በኮረትና በድንጋይ እንደተሞላ ክዳን እየተገጠመላቸው ነው ። በአካባቢው በቅርብ ርቀት ላይ ያሉ የወረዳ አመራሮች ሳያዩ ቀርተው ነው ብዬ ለማመን ይቸግረኛል ባለቤቱ ማነው አቶ ናትናኤል ባንተ በኩል መድረስ ከቻለ ክረምት ከመግባቱ በፊት እንዲስተካከል ቢደረግ ። እንደለመደብን ጨረስን ብለን በማግስቱ ወደ ቁፋሮ እንዳንገባ በህዝብና በመንግሥት ገንዘብ መቀለድም እንዳይሆን ብዬ ነው ።