Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 173.42K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 397

2022-05-19 12:44:44
የጆሮ የመስማት አቅም ማነስ ድምፅን ከሩቅ ለመስማት እንዳነቸገር 0911284905 ይደውሉል
HEARING AID
በተመጣጣኝ ዋጋ 6800birr ከ 2 አመት ዋስትናጋ
ይደውሉልን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን

-በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ላለ የሚሆን
-በዛላይ ለአደራረግ እና ቢታይ ቀለል ያለ
-ለሁለቱም ጆሮ ለሚፈልጎ ማድረግ የሚችሉት
-ቻርጅ ተደርጎ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ
-እራሱላይ ፓወር ባንክ ያለው

በተለያያ ምክንያት በአደጋም በተፈጥሮ ለሚከሰት የመስማት ችግር ላጋጠማቸው

ተጨማሪ የማዳመጫ መሳሪያ ይዘንላቹ ቀርበናል
ይዘዙ ከፃን እስከ አዋቂ መጠቀም ይችላሉ ክፍለ ሀገር አንልካለን አዲስ አበባ በነፃ እናደርሳለን
25.2K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 02:33:15

7.1K views23:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 02:32:54
የኢትዮጵያ አለኝታዎች

ስለእናት ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት ስለሕዝቧ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም መከበር ያለእረፍት ሁሌም ተጓዥ ናቸው። ቆላ ይወርዳሉ። ደጋ ይወጣሉ። ጋራሸንተረሩን ያቋርጣሉ።
ሁሌም ስለኢትዮጵያ ክብር አንድያ ሕይወታቸውን መደበው ጠላትን በግንባሩ እየበረቀሱ ወደፊት በድል ይገሰግሳሉ

ኢትዮጵያ በእናንተ የጦር ሜዳ ጀግኖች ነፃነቷን ጠብቃ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች Good Night #Ethiopiaዬ
7.1K views23:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 01:49:29
7.5K views22:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 01:49:20 ኢትዮጵያ እና ቱርክ ወታደራዊ ትብብሮችን ለማድረግ የሚያስችላቸውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም በቱርክ አንካራ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

ከስምምነቱ መካከል በጥቂቱ ፦

(የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት)

ዓላማ፦ በ2ቱ አገሮች መካከል በመከላከያ ዘርፍ የሚደረገው ግንኙነት የሚመራበትን ግልጽ ማዕቀፍ ለመፍጠር ነው።

የስምምነቱ ይዘት ፦ በሁለቱ ሀገራት በትምህርት እና ስልጠና በተናጠልና በጋራ በሚዘጋጁ ወታደራዊ ልምምዶች ስለመካፈል፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪ፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የሎጅስቲክ፣ የጤና አገልግሎት፣ የመረጃ ስርአት እና የሳይበር ጥቃትን መከላከልና በሌሎች ተያያዥ መስኮች ፣ ከመደበኛ ጦርነት ውጭ ባሉ የሰላም ማስከበር ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን ያካተተ ነው።

በኢትዮጵያ ላይ የሚጥለው ግዴታ ፦ ሚስጥራዊ መረጃዎች፣ ሰነዶች እና ማቴሪያሎች ፣ አእምሮአዊ ንብረቶችን አስፈላጊውን ጥበቃ የማድረግ ኢትዮጵያ ለትምህርት እና ስልጠና ወደ ቱርክ ለምትልካቸው የመከላከያ አባላት እና ተማሪዎች በተቀባይ ሀገር የማይሸፈኑትን የህክምና ወጪዎችን ፣ ሌሎችንም የትምህርት እና ስልጠና ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጥላል።

ከዚህ ስምምነት ኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅም ፦ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ፣ የሎጅስቲክ አቅርቦቶችን እና ድጋፎችን ለማግኘት የሰራዊት ትጥቆችን እንዲሁም በሰው ኃይል እና አስተዳደር ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ፣ የትምህርትና ስልጠና እድሎችን ለማግኘት ያስችላል።

(የወታደራዊ ፋይናንስ ትብብር ስምምነት)

ዓላማው ፦ በሁለቱ ሀገራት መካከል በመከላከያ ዘርፍ የሚደረገው ግንኙነት የሚመራበት ግልፅ የህግ ማዕቀፍ በመፍጠር የቱርክ መንግስት 100 ሚሊዮን የቱርክ ሊሬ ተመጣጣኝ የሆነ የአሜሪካ ዶላር ለኢትዮጵያ መንግስት ፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ለመከላከያ ዓላማ የሚውል 100% በቱርክ ሀገር የተመረቱ የመከላከያ ቁሳቁሶችን እና አገልግሎቶችን መግዛት የሚችልበትን መርዕ ለመወሰን ነው።

የስምምነቱ ይዘት ፦ የቱርክ መንግስት 100 ሊሬ ተመጣጣኝ የአሜሪካ ዶላር ለኢትዮጵያ መንግስት ስለሚሰጥበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት በዋናነት በቱርክ ከሚገኙ ኩባንያዎች 100% በቱርክ የተመረቱ የመከላከያ ቁሳቁሶችንና አገልግሎቶችን መግዛት የሚችልበትን መርህ ይደነግጋል።

በኢትዮጵያ ላይ የሚጥለው ግዴታ ፦ በሁለቱ ሀገራት የመረጃ ልውውጥ የተገኙ እና ሚስጥራዊ ተብለው የተለዩ መረጃዎችን ከሌላኛው ወገን የፅሁፍ ፍቃድ ሳይገኝ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያለ መግለፅ እና ሚስጥራዊ መረጃዎችን መጠበቅ እንዲሁም ከቱርክ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የተላለፈ ሀብት ፣ እቃ ወይም አገልግሎት ያለ ቱርክ መንግስት የፅሁፍ ፍቃድ ለሌላ ሀገር ወይም ሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ ወይም ጥቅም ላይ እንዳይውል የማድረግ ግዴታን ይጥላል።

ከስምምነቱ ኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅም ፦ ኢትዮጵያ ከቱርክ መንግስት የምታገኘው 100 ሚሊዮን የቱርክ ሊሬ ተመጣጣኝ የአሜሪካ ዶላር ወታደራዊ ቁሳቁስ እና አገልግሎት ከቱርክ ድርጅቶች በመግዛት ለአስፈላጊ አገልግሎት ማዋል እንድትችል ያደርጋታል።
7.6K views22:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 01:43:08
አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምስጋና አቀረቡ!!

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምስጋና አቀረቡ።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

"ክቡርነትዎ ከእርስዎ ጋር በመሆን የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዊና የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎችን እሰራለሁ" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በዚሁ መልዕክታቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፕሬዝዳንቱ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ማስተላለፋቸውም ይታወሳል።
7.6K views22:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 01:40:19
ቂጡን በሳንጃ ቢወጋ..... አለ ኮረኔል መንግስቱ :) አይ አቶ ያሬድ እንዲህ አስቂኝና የሶሻል ሚዲያ መጫዎቻ ይሁን? ከሁሉ የገረመኝና ያሬድ ምን ያህል ጥቅመኛና ነውረኛ ህዝብን እንዴት እንደሚንቅ እምታውቁት ውለታ ለማያቅ ህዝብ ብሎ የጻፋት ነገር ነች ዘይገርም ነው
7.8K views22:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 20:22:27

24.6K views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 19:24:00 ቤተ ክርስቲያኗን ከተኩላዎች ታደጉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብራና ዳምጣ፣ቀለም በጥብጣ ፊደል ቀርጻ ለዘመናዊት ትምህርት መሰረት የጣለች፤ ዜጎች በስነ ምግባር ታንጸው ሀገራቸውን እንዲያገልግሉ ሚናዋን የተወጣች፣፤ ሉዓላዊነትና ክብር እንዳይደፈር የሀገር ፍቅርን ያስተማረች፤ በሥነ ሕንጻ፣ በቱሪዝም፣ በአካባቢ ጥበቃና በሌሎችም ትላልቅ ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች የድርሻዋን ያበረከተች የሀገር ምሰሶ ናት፡፡
ዛሬ ዛሬ ቤተክርስቲያኗ ከውጭ ከሚገጥማት መሰናክል ባልተናነሰ ከውስጥ የተደቀነባት ፈተና ህልውናዋን የሚገዳደር ሆኗል፡፡ ቤተክርስቲያኗ በቅንነት የሚያገለግሏት ታማኝ አባቶች በብዛት የማፍራቷን ያህል ከጉያዋ ተሸሽገው ክብሯን የሚያጎድፉ፤ መንፈሳዊነትን ለፖለቲካ አላማ ማስፈጸሚያ ያደረጉ እንዲሁም በነዋይ ለመበልጸግ የሚያውሉ ሙዳየ ምጽዋት እስከ መቦጥቦጥ በየሚያደርስ ርካሽ ተግባር ላይ የተሰማሩ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎችም ከቤቷ አልጠፉም፡፡
በወርሃ ግንቦት በሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አፍራሽ አጀንዳ በሚያራምዱ አካላት እንዳይጠለፍ ስጋቶች ተስተውለዋል፡፡ አንዳንድ አባቶች ከበስተጀርባ የፖለቲካ ተልዕኮ ያነገቡ ሰዎች በቤተክርስቲያኗ በተለያዩ የአገልግሎት ኃላፊነቶች ላይ እንዲቀመጡ ከወዲሁ በህቡህ እየቀሰቀሱና እያደራጁ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ በዚህ ምርጫ ለማሸነፍን ካሰፈሰፉት አካላት መካከል ከምዕመናን የተሰበሰበን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እና ለምረጡኝ ቅስቀሳ  እያዋሉ ያሉ ስላሉ ህዝበ ክርስቲያኑ በተለያየ መንገድ መረጃው እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡
በምርጫው እንደዚህ አይነት የቤተክርስቲያኗን ክብር ዝቅ የሚያደርጉ ሰዎች ሰርገው እንዳይገቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡ አባቶች በቤተክርስቲያኗ አገልግሎትና መንፈሳዊ ተልዕኮ ላይ ጥቁር ጥላ እንዳያጠላም በእኩይ ተግባር የተጠመዱትን ለዘመናት በዳበረው የጥበብ ወንፊት በመለየት ቤተ ክርስቲያኗን ከተኩላዎች ሊታደጉ ይገባል ይላሉ ጉዳዩ ያሳሰባቸው አንድ የሲኖዶስ አባልና ሊቀ ጳጳስ፡፡ በቀጣይ በዚህ ተግባር እየተሳተፈ ያለውን ቡድን አሰላለፍና ስም ዝርዝራቸውን እኚህ የሲኖዶስ አባልና ሊቀ ጳጳስ የሰጡንን መረጃ በመንተራስ እናጋራችኋለን
30.5K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 19:21:13 ልዩ መረጃ!

ኤርትራ ከህወሓት ጥቃት እራሷን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

የኤርትራ መንግሥት በማስታወቂያ ሚኒስቴሩ በኩል ዛሬ ግንቦት 09/2104 ዓ.ም. ባሰፈረው መልዕክት ህወሓት በኤርትራ ድንበር በኩል እና በምዕራብ ትግራይ አቅጣጫ በሁለት ግንባሮች ጦርነት ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው ብሏል።

ጨምሮም በዚህ በህወሓት ሊሰነዘር ይችላል ላለው ጥቃት የመጀመሪያው ዒላማ "ኤርትራ እና የኤርትራ ሕዝብ ናቸው" ሲል አቋሙን አንጸባርቋል።

ከወራት በፊት ከተደረገው ከባድ ውጊያ በኋላ ጋብ ብሎ የቆየው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዳግም ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት እየጨመረ በመጣበት ጊዜ ነው የኤርትራ መንግሥት ይህንን ያለው።

ከቀናት በፊት የአማራ ክልል ከህወሓት በኩል ሊሰነዘር ይችላል ላለው ሌላ ዙር ወረራ የክልሉ የፀጥታ መዋቅር ዝግጁ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥት ኃይሎች መካከል ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም አልፎ አልፎም ግጭቶች ሪፖርት መደረጋቸው እንዳሳሰበው ገልጾ ነበር።

እያየለ ከመጣው የዳግም ጦርነት ስጋት በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ለጥቂት ሰዓታት የቆየ ጥቃት ሰንዝረው የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ቢቢሲ መዘገቡ ይታወሳል።

ዛሬ በኤርትራ መንግሥት ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሑፍ ላይ ግን ሚያዚያ 30/2014 ዓ.ም. ራማ እና ባድመ አካባቢ ከህወሓት ኃይሎች ጋር ግጭት አጋጥሞ ነበር ስለመባሉ ያለው ነገር የለም።

የኤርትራ መንግሥት ባስተላለፈው መልዕክት በዓለም አቀፍ ሕግ የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛት እንደሆነ ያረጋገጠወን አካባቢ ህወሓት ዳግም ለመውረር በዝግጅት ይገኛል ሲል ከሷል።

ከዚህ በተጨማሪም፤ ህወሓት ሊከፍት ነው ላለው አዲስ ጥቃት በምዕራብ ወልቃይት፣ ጸገዴ እና ሑመራን መልሶ በመቆጣጠር ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን ድንበር ለመክፈት አቅዷል ብሏል።

በመጨረሻም ከህወሓት ሊሰነዘር የሚችልን ጥቃት የኤርትራ ሕዝብ እና መንግሥት እራሱን መከላከል ይችላል በማለት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

ለዚህ ከኤርትራ መንግሥት በኩል በይፋ ለቀረበው ወረራ ለመፈጸም የመዘጋጀት ክስ ከህወሓት በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም ሲል ቢቢሲ ዘግቦታል።
28.8K views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ