Get Mystery Box with random crypto!

Natnael Mekonnen

የሰርጥ አድራሻ: @natnaelmekonnen21
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 175.28K
የሰርጥ መግለጫ

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-04-20 13:09:24
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561
17.7K views10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 10:57:23
የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ሩጫው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በውድድሩ ወቅት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገውና የአዲስ አበባን ዋና ዋና መንገዶችን የሚያካልለው የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ከዚህ ቀደም በርካታ ህዝብ በብዛት የተሳተፈባቸው ተመሳሳይ ሩጫዎች በሰላም መጠናቀቃቸውን ያስታወሰው ፖሊስ በመጪው እሁድ በከተማችን የሚካሔደው የሩጫ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራ ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ መነሻውን ከመስቀል አደባባይ በማድረግ በለገሃር ፣ ሜክሲኮ አደባባይ ፣ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ፣ ቄራ ፣ ጎተራ ማሳለጫ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ጥላሁን አደባባይ አድርጎ መዳረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ውድድር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ
• ከመገናኛ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
• ⁠ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል
• ⁠ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ አጎና መስቀለኛ
• ⁠ከጎርጎሪዎስ አደባባይ ወደ ጎተራ
• ⁠ከጎተራ ሼል ወደ ጎተራ
• ⁠ከማሞ ማቋረጫ ወደ ጎተራ
• ⁠ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ⁠ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ቄራ በረት
• ⁠ከመካኒሳ አቦ አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
• ⁠ከካርል አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
• ⁠ከልደታ ፀበል ወደ ኤዩ መብራት
• ⁠ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደኤዩ መብራት
• ⁠ከኦርቢስ መታጠፊያ/ጮራጋዝ/ መስቀለኛ ወደ ሲጋራ ፋብርካ
• ⁠ከጠማማ ፎቅ ወደ ጥይት ፋብርካ
• ⁠ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ወደ ገነት መብራት
• ⁠ከከፍተኛ ፍ/ቤት /ባልቻ ሆስፒታል/ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
• ⁠ከአረቄ ፋብርካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
• ⁠ከሠንጋ ተራ 40/60 መስቀለኛ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት
• ⁠ከበድሉ ህንፃ ወደ ቴሌ ባር
• ⁠ከብሔራዊ ቲያትር መብራት ወደ ለገሃር መብራት
• ⁠ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት
• ⁠ከብ/ቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
• ⁠ከኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ እና ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ውድድሩ ፍፃሜ ድረስ ጎፋ ማዞሪያ ድልድይ ፣ በቅሎ ቤት ድልድይ እና ጥላሁን አደባባይ ድልድይ አካባቢ ለረዥም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍጽም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል፡፡ በየአካባቢው ለተመደቡ የትራፊክ ፖሊስ እና የፀጥታ አካላት ተባባሪ በመሆን የሚሰጡትን ትዕዛዝ አሽከርካሪዎች በማክበር የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ አዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡
20.6K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 10:57:02
ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ


+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
17.9K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 10:56:44
ኤልናፍ ትሬዲንግ ኋ.የተ.የግ.ማህበር
ELNAF TRADING PLC
የቱርክ ብሎኬት ማምረቻ
ድርጅታችን በኢትዮጵያ ተመዝግቦ የሚገኝና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማራ  ሲሆን በአሁን ስዓትም በለገጣፎ አካባቢ በ15,000 ካ.ሜ  ላይ በቀን ከ40,000 በላይ ብሎኬቶችን ማምረት የሚያስችል የቱርክ ማሽኖችን ተክሎ ወደስራ የገባ ሲሆን በዚህም ለ150 ሰዎች የስራ ዕድል የፈጠረ ና በኮንስትራክሽን ዘርፉም የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል።
ለየት የሚያደርገን
⨳    በቱርክ ማሽኖች ማምረታችን
⨳    የራሳችንን የከርሰ ምድር ውሃ አውጥተን መጠቀማችን
⨳    በሰዓቱ ምርት ማቅረባችን
⨳    ያሉበት ድረስ በራሳችን ተሽከርካሪዎች ማድረሳችን
⨳    በሚፈልጉት size እናመርታለን
            ባለ 10 cm
            ባለ 15 cm
            ባለ 20 cm
           ባለ 24 cm (ሪብድ)

ይምጡ ይጎብኙን በምርታችንና ዘመናዊነትን በተከተለ አሰራራችን ይረካሉ።
  ቤትና ህንፃዎችዎን በኤልናፍ ብሎኬት ይገንቡ ያትርፉ
አድራሻችን ቁ.1   ለገጣፎ አባ ኪሮስ ቤ/ያን እንዳለፉ
             +251993999999
https://maps.app.goo.gl/kQ884KEndxzVxezaA
                     ቁ.2    ጀሞ 3 ሰይድ ያሲን አደባባይ አከባቢ
             +251985888899
https://maps.app.goo.gl/djEzNajMtsvVA9JY9
19.5K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 21:09:17
የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ እየተገነባ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሌላ መለስተኛ ከተማ የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ

ሁሉንም በሟላው መለስተኛ ከተማ ውስጥ ከሚገነቡት ቤቶች ውስጥ ውስን ቤቶች ለሽያጭ ይቀርባሉ፡፡

በድጋሚ በማይገኘው እድል ውስኝ ቤቶች ለሽያጭ ቀርበዋል። መፍጠን ያዋጣል!!!! ከቦሌ አየርመንገድ በ8 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኘው የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማን እየተገነባ ነው።

ከሚያዝያ 16 – 20 ለ 5 ቀናት ብቻ በአድዋ ሙዚየም 6124 ቤቶች ለገበያ ቀርበዋል። ልብ ይበሉ! ቤትዎን ለመግዛት ቀድሞ መመዝገብ ያስፈልጋል።

የመመዝገቢያ ሊንክ: https://bit.ly/ovid2024

ለበለጠ መረጃ በ 9727 ይደውሉ!

ቀድመው የሚገዙ 1000 ሰዎች ከ 415 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሆናሉ። ኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ የነገ መኖርያዎ!!!
30.8K views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 17:33:19
በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከብክለት ነፃ የሆኑ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የሚኒባስ ተሽከርካሪዎችን ከማዕከል እስከ ወረዳ ላሉ ተቋማት አስረክቧል።

ብክለትን በመከላከል ረገድ ፋይዳቸው ጉልህ የሆኑ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችም ከተማዋን ፅዱ ለማድረግ እንዲሁም ወጪም ለመቆጠብ የሚያስችሉ ሲሆን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግዥና ስርጭትም አዲስ አበባን ውብና ፅዱ እንዲሁም ከአካባቢ ስነምህዳር ጋር የተስማማች ከተማ የማድረግ ውጥን አካል እንደሆነ ክብርት ከንቲባ ኣዳነች ኣቤቤ ተነግሯል። ኣክለውም ከዚህም ባሻገር ያለንን የኤሌክትሪክ ሀይል በመጠቀም ለነዳጅ የሚወጣው የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ ስለሚያስችለን ፊታችንን በኤሌክትሪክ ወደ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ማዞር እንደሚገባ መግለፃቸውን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።
33.4K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 15:00:11 ዶር አስማማው ቀለሙ (ፔድሮ) ነፍስ ይማር ደራሲያን ጸሀፊያን ተዋንያን የዶር አስማማውን እውነተኛ ታሪክ (ህይወትን ለሀገር መስጠትን) በፊልም ብትሰሩትና አሁንም ወደፊትም ትውልድ ቢማርበት ጥሩ ነው::

32.5K views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 14:27:45
የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ኢንዱስትሪን ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጡ።

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከተመሰረተ በርካታ ዓመታትን ያሳለፈው የመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘመኑ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ለማድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀው፣ የፋብሪካው ግንባታ ለሀገርና ለተቋሙ የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢንዱስትሪው በአዲስ መልኩ ከተደራጀ በኋላ በተሰሩት ስራዎች ከኪሳራ ወደ ትርፋማነት መሸጋገሩን የገለፁት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የኮርፖሬሽኑ አመራርና አባላቶች ለነበራቸው ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ተቋሙ የራሱን ገቢ በማመንጨት ለሰራዊቱ መሰረታዊ ጥቅም ለማሟላት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የሰራዊቱን የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለማድረግና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በኢንዱስትሪ ፤ በግብርና ፣ በማዕድንና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ለመስራት የተቀመጠው አቅጣጫ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።

የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ሀይለማርያም የመከላከያ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ከሽርሽር ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመሆን የሚገነባው መሆኑን ተናግረዋል።

ኢንዱስትሪው በሰላሳ ሄክታር ላይ የሚያርፍና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ መታቀዱንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

አለም አቀፍ ስታንዳርዳቸውን ያሟሉ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ከመገጣጠምና ከማምረት ባለፈ በቀጣይ ፕሮጀክቱን የማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸው የገለፁት ዳይሬክተሩ ለፕሮጀክቱ ስኬት ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

በዝግጅቱ ላይ የመከላከያ ሚንስቴር ዲኤታ አቶ ቶማስ ቶት የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ ወታደራዊ አታሼዎችና ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች ተገኝተዋል።
33.5K views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 10:02:56
በቀጠናው የሚገኘው መከላከያ ሠራዊት እየወሰደ በሚገኘው ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እየፈረሰ እንደሚገኝ ተገለፀ።

የደቡብ ዕዝ አንድ ኮር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ግርማ አየለ እንደገለፁት ሠራዊቱ በምስራቅ ጉጂና በምስራቅ ቦረና ዞኖች ህዝብን ሲያሸብር በነበረው ኦነግ ሸኔ ላይ በወሰደው ተከታታይነት ያለው ወታደራዊ እርምጃ በአንድ ወር ውስጥ ከ150 በላይ የቡድኑ ታጣቂዎች ለሰራዊቱ እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ቡድኑ እየፈረሰ ይገኛል።

ኮሎኔል ግርማ የሠራዊቱን ብርቱ ክንድ መቋቋም ያቃተው ኦነግ ሸኔ በርካታ ታጣቂዎቹ በሠላማዊ መንገድ እጅ እየሰጡ መሆኑን አስታውሰው ፤ ቡድኑ ተደራጅቶ የመዋጋትም ሆነ የማድረግ አቅም እንደሌለው አብራርተዋል።

ሠራዊቱ የህዝባችንን አንድነትና ሰላም በሚያውኩ ፀረ ሠላም ሃይሎች ላይ እያስመዘገበ የሚገኘው ድርብ ድልና ስኬት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል።

የምስራቅ ጉጂ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቦጌ ታፈሰ በበኩላቸው ፤ ህዝባዊ መሰረት የሌለው የኦነግ ሸኔን እኩይ ተግባር የተገነዘቡ በርካታ የቡድኑ ታጣቂዎች የሠላም አማራጭን በመገንዘብ ለሠራዊቱ እጅ እየሰጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በተሳሳተ ትርክት የሸኔን ቡድን እንደተቀላቀሉ የሚገልፁት የሽብር ቡድኑ አባላት  ፤ የህዝቦችን ስቃይ ከማብዛት ውጭ ያገኘነው ጥቅም ባለመኖሩ በሰላማዊ መንገድ እጅ ልንሠጥ ችለናል ብለዋል።

የቡድኑ ዓላማ ህዝባዊ አለመሆኑን ጠቁመው ፤ ተበታትነው የሚገኙ ርዝራዥ የቡድኑ ታጣቂዎች የሸኔን የጥፋት ዓላማ በመገንዘብ ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።
32.1K views07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 07:27:25
በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮ-አሜሪካ የቢዝነስ እና የኢንቨስትመንት ፎረም ተካሄደ

ዋሽንግተን ዲ.ሲ. የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ ከዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ-አሜሪካ ቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በዋሽንግተን ዲሲ አካሄደ። በዚሁ ፎረም ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልድ ኢትዮጵያውያን እና አሜሪካውያን ባለሀብቶች ተገኝተዋል።

ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ ባለፉት ጥቂት አመታት የተለያዩ የውጭ እና የውስጥ ፈተናዎች ቢያጋጥሙም የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ እነዚህን ተግዳሮቶች ተቋቁሞ አሁንም ዕድገት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸው ኢኮኖሚያችን እነዚህን ችግሮች ተቋቁሞ የማለፍ አቅም የፈጠረበት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ በመንግስት እየተተገበረ ያለው መጠነ ሰፊ የሪፎርም ስራ እና በመሰረተ ልማቶች ላይ በተከናወኑ ትልልቅ የኢንቨስትመንት ስራዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥን ከመቋቋም፣ በምግብ ራስን ከመቻል እንዲሁም ዘላቂ የግብርና ምርታማነትን ከማሳደግ እና ከተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደር ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ከመፍታት አንጻር ትልቅ ድርሻ የሚይዘው የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም አሜሪካውያን ባለሀብቶች አገራችን ኢትዮጵያን መጥተው እንዲጎበኙ እና ያሏትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲያዩ ግብዣቸውን አስተላልፈዋል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክቡር ዶ/ር ስለሺ በቀለም በበኩላቸው አገራችን ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ያላት መሆኗን እና በተለያዩ ጊዜያት የከፍተኛ ባለስልጣናት የስራ ጉብኝቶች የተካሄዱ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ባለፈው ዓመት በዩ.ኤስ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተሳትፎ ማድረጉን እና በወቅቱ ክቡር ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዓብይ ከአሜሪካ አስተዳደር፣ ኮንግረስ፣ እና በግሉ ኤኮኖሚ ዘርፍ ከተሰማሩ አካላት ጋር ውጤታማ ውይይቶች ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።

በዚህ ፎረም ላይ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ ሀብት እና የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሁም ኢንቨስተሮች ሊያገኙ የሚችሉትን የተለያዩ ማበረታቻዎችን አስመልክቶ ሰፊ ገለጻ ቀርቧል። በተጨማሪም በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ስኬታማ ትውልድ ኢትዮጵያውያንን እና የተለያዩ አሜሪካውያን የስራ ሃላፊዎችን ያካተተ የፓናል ውይይትም ተካሂዷል።

ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ የተሰጠ ሲሆን፤ በፎረሙ የተሳተፉ አሜሪካውያን ባለሀብቶች መንግስት እያካሄደ ያለው ሪፎርም በተለይም የውጭ ኢንቨስተሮች መዋእለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ምቹ ሁኔታዎች እንዲኖሩ የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው በቀጣይ ከኢትዮጵያውያኑ ባለሀብቶች ጋር ለሚኖራቸው ፍሬያማ ግንኙነት መሰረት የሚጥል ነው በማለት በሀገሪቱ ያሉ አማራጮችን ለማየት ፍላጎታቸው መሆኑን ገልጸዋል። The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia
20.2K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ