Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.49K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-04 16:56:54
13.0K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 16:56:49 የፕሪቶሪያ ስምምነት መቆመሪያቸው ነው!

ስምምነቱ እነ ጌታቸው ረዳ ከአማራ ለመንጠቅ የሚፈልጓቸውን ግዛቶች "የተወረሩ" አይላቸውም። "አወዛጋቢ" ነው የሚላቸው። በዚሁ ስምምነት መሰረት የጥላቻና የጦርነት ቅስቀሳ የተከለከለ ነው። በትህነግ በኩል ፈራሚው ጌታቸው ረዳ ግን አሁንም "ወራሪ" እያለ እየፃፈ ነው። የሰላም ስምምነት ተብሎም ለእሱ አማራ ወራሪ ነው። ስምምነቱ መቋመሪያ ካርድ እንጅ እንደማያከብሩት ይታወቃል። በጓዳ ግዛቶቹን አሳልፎ ለመስጠት የሚስማማው የአብይ አገዛዝም በስምምነቱ መሰረት ባቋቋመው ኮሚቴ ይህን እንደማይገመግም ይታወቃል።

የአማራ ክልል ጉልት ካድሬ ደግሞ በስምምነቱ መሰረት በስሩ እንዲቆይ የተወሰነውንም አስተዳደር አፍርሶ ትግራይ ውስጥ አንድ ቀበሌ በቅጡ ለማያስተዳድረው፣ ስካይ ላይት መቀመጫውን ላደረገው ጌታቸው ረዳ አሳልፎ ሰጥቷል። በዚህ ከቀጠለ አብይ አጠቃላይ አማራ ክልልን ለጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ቢሰጠውም ከዝምታ የተሻለ ከአማራ ክልል ካድሬ እንደ አማራጭ የሚቆጠር ስልት ያለ አይመስልም።

በዚህ በዓል መልዕክት ቀርቶ በሌላም ጊዜ በአማራ ላይ አፍ መክፈትን የህዝብ መሰብሰቢያ ካደረጉት የትህነግ አመራሮች ውጭ ጦርነት እየቀሰቀሰ ያለ አይመስልም። ለትንሳኤ በዓል መልዕክት እንኳን አማራን በለመዱት ክፍታፍነታቸው ከመዝረፍና ከመውቀስ የሚመለሱ አይደሉም።
12.6K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 08:57:26 የባልደራስን ንቁ አባላት ያሳሰረው ኤርሚያስ ለገሰን ተንኮል ተመልከቱ!

የኤርሚያስ ወዳጅ የነበረው ቴድሮስ ፀጋዬ ሰሞኑን ኤርሚያስ የባልደራስ ንቁ አባላትንና የአዲስ አበባ ወጣቶችን እየጠቆመ እያሳሰረ እንደሚገኝ በቀጥታ ስርጭት ተናግሯል። ይህን የባልደራስ የቅርብ አመራሮችም አረጋግጠውልኛል።

ትናንት የሰራውን ፕሮግራም እንኳን ተመልከቱ። ያሳሰራቸው የባልደራስ ንቁ አባላት መካከል ናቲን ፎቶ የፊት ገፅ ላይ ሆን ብሎ አቀናብሮ ከሚከሳቸው የፋኖ አባላት ጋር አቅርቧል። ኤርሚያስ ለፕሮፖጋንዳ የሚጠቀምበትን እያንዳንዱን ጉዳይ የሚያውቅ ሰው ነው። የፊት ገፅ ሲያሰራ ምን ማስተላለፍ እንደፈለገ ግልፅ ነው። ከሰላማዊ መንገድ ውጭ የትጥቅ ትግሉ ላይ ፈፅሞ የሌሉበትን ወጣቶች ፎቶ ሾፕ እየሰራ ጭምር የሀሰት ጥቆማውን እውነት ለማስመሰል እየሰራ ያለ አደገኛ ሰው ነው።

ከቅርቡ የአዲስ አበባ ክስተት በኋላ አዲስ አበባ ላይ ሽብር የሚፈፅሙት የከተማው ተወላጆች ጭምር አሉ ብሎ የአዲስ አበባን ወጣት በሀሰት ከስሷል። በተለይ በተለይ ባልደራስ ሰልፍና ስብሰባ ሲያደርግ ንቁ እንቅስቃሴ ያደርጉ የነበሩ፣ በሚዲያ ያግዛል ተብሎ መረጃ የሚሰጡትና ለፓርቲው ሰላማዊ እንቅስቃሴ በተለያያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ግሩፕ ውስጥ የነበሩትን ለአገዛዙ እየጠቆመ አሳስሯል። የባልደራስ አመራሮችም ያረጋገጡት መረጃ ነው።
12.8K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-03 19:17:25 ይህንማ አላያችሁትም! አላያችኋትም!

ታደሰ ወረደ በቀደም አብይ ጋር ተሰብስቦ፣ ትናንት ደግም ከሳምንት በፊት "መወገድ አለበት" ብላ ፕሮግራም ከሰራችው ሴትዮ ጋር አመሸ። በቀደም ተመስገን ጥሩነህ ጋር ተገማግም፣ ተመስገን በጀኖሳይድ መጠየቅ አለበት ካለችው ጋር ተመሰጋገነ።

እንዲች ናትና!

በነገራችን ላይ ታደሰ ወረደ ከኮሚቴው ጋር የሚገማገመውን ለትህነግ/ህወሓት ሚዲያዎች ያደርሳል። ትናንት ማታ ግምገማውን በሙሉ ለኤርሚያስ ሰጥቶ ለእነሱ በሚጠቅም መልኩ አሰራው፣ ራሱ ደግሞ በዚህ ሚዲያ ቀረበ።

ልጨምርላችሁ! በዚህ ሚዲያ ለታደሰ የቀረበው ጥያቄ ኤርሚያስ የሰራበት ነው።
12.9K views16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-02 09:00:35
14.5K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-02 09:00:21 የሚገርሙ፣ የሚያሳዝኑም ጉዳዮች ናቸው!

1) የጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ከመቀሌ ውጭ ተንቀሳቅሶ ስብሰባ ማድረግ እንደማይችል ራሱ ጌታቸው ለትግራይ ሕዝብ ተናግሯል። ትግራይን የሚያስተዳድረው ከጦርነቱ በፊት የነበረው፣ ወንጀለኛ የተባለው መዋቅር ነው። ይህን ጌታቸው ረዳ በሚዲያ ወጥቶ ያረጋገጠው ነው። ይህ ህገወጥ መዋቅር ስለሆነ ነው ጊዜያዊ አስተዳደር ማዋቀር ያስፈለገው።

ትግራይ ውስጥ ከመቀሌ ውጭ ስብሰባ እንኳ ማድረግ የማይችለው የጌታቸው ረዳ አስተዳደር፣ በህጋዊ ስምምነት የተሰጠውን ትግራይን እንዳያስተዳድር ተደርጎ፣ በማያገባው ከትግራይ ውጭ ያሉትን የአማራ ግዛቶች እንዲያስተዳድር ነው የተደረገው። ሰሞኑን ትህነግ በወረራቸው የአማራ አካባቢዎች ጊዜያዊ አስተዳደሩ መዋቅሩን አሰማርቷል። ትህነግ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ የፈቀደለት የወረራ አላማ ስለሆነ ነው። ትግራይ ውስጥ አንድም ቀበሌ እንዳያስተዳደር የተደረገው ጌታቸው የአማራን አካባቢዎች ግን በህገወጥ መንገድ እንዲይዝ ተደርጓል።

2) ሰሞኑን በትግራይ ፖለቲካ አጀንዳ የሆነ ጉዳይ አለ። ትህነግ የአማራ አካባቢዎች ተወልደው ያደጉትን አመራሮቹን "ትግሬ አይደላችሁም" እንዳላቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራር ረዳኢ ሓለፎም ቃል በቃል ተናግሯል። የትግሬ ካባ የሚሰጠንም የሚቀማንም ሌላ ቡድን አለ ብሏል። የአድዋውን ቡድን ነው። ታዲያ ራያ ያደጉትን አመራሮቹን "ትግሬ አይደሉም። ባንዳ ናቸው።" ወዘተ እያለ የሚፈርጅ ራያን መሬቱንና መሬቱን ብቻ እንደሚፈልግ ግልፅ ነው። አመራሮቹን በጠላትነት የፈረጀ ለሕዝቡማ ያለው ጥላቻን መገመት ቀላል ነው። በተደጋጋሚ በተግባርም የታየ ነው።

3) ራያን የወረረው የትህነግ ታጣቂ "አርሚ 24" ይባላል። መከላከያን በመታበት ጥቅምት 24 የተሰየመ ነው። መከላከያ የተገደለበትን ቀን ማስታወሻ ያደረገውን
ኃይል ነው እያገዘ የሚገኘው።

4) የሰላም ስምምነቱ ያለ ምንም ማወላዳት የደነገገው፣ የጊዜ መንዛዛት ያልተቀመጠበት የትጥቅ መፍታት ነው። በማያሻማ መልኩ በአንድ ወር ውስጥ ትጥቅ ይፍቱ ተብሎ ነበር። ጭራሽ አስታጠቋቸው። መከላከያ ትግራይን ይረከብ ተብሎ ነበር። ጭራሽ መከላከያ ከትግራይ ወጥቶ አማራ ላይ ዘምቶ፣ ትጥቅ መፍታት የነበረበት ትህነግ አማራ ክልልን በኃይል እንዲይዝ ተደረገ

5) ትህነግ ባለፉት ወረራዎች ዘረፋ የሚፈፅሙትን በየጦሩ አደራጅቶ አሰማርቷል። በዘረፉት ልክ ጥቅም አግኝተዋል። እንደ ጀግና ታይተዋል። ይህ ኃይል ግን ወደ ትግራይ ተመልሶ አረመኔ ሆነ። የአርሶ አደር በሬ አርዶ መብላት፣ የተቋማትን ብረታብረት መዝረፍ ወዘተ። ሰሞኑን የትግራይ ክልል ውሃ መሳቢያ ብረቶች እየተዘረፉ መሆኑ በስፋት እየተሰራጨ ነው። ይህን የራሴ የሚለውን ትግራይን እየዘረፈ ያለ ኃይል ነው ጠላቴ ወደሚለው አማራ ይዘውት የመጡት። ከራያ ብቻ ከ50 ሺህ በላይ ሕዝብ የተፈናቀለውም ይህ አረመኔ ኃይል በሚፈፅመው ወንጀል ምክንያት ነው።

ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው አማራ ላይ ነው!
13.2K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-01 17:52:17
13.1K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-01 17:52:06 የወረራ ዝግጅት!

ራያን የወረረው ትህነግ ጠለምትንና ወልቃይትን ለመውረር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። በዚህም መሰረት በሱዳን በኩል፣ አርሚ 11 ጠለምትን ለመውረር፣ አርሚ 17 ወልቃይትን ለመውረር ዝግጅት ላይ ነው፣ አርሚ 35 ከአክሱም ወደ ሽሬ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ጥቅምት 24 መከላከያን የመቱበትን ማስታወሻ ያደረጉት "አርሚ 24" ደግሞ ራያን የወረረው ነው።

ይህ በሆነበት ብልፅግና የአማራ አስተዳደሮችን በሕገወጥ መልኩ አፍርሶ በተፈናቃይ ስም የወረራ በር እየከፈተና እያገዘ ይገኛል። እንደ ገለልተኛ "ትጥቅ መፍታት አለባቸው" እያለ የሚቀልደውም ዝግጅታቸውን ስለማያውቅ አይደለም። ማዘናጊያ ነው።

በሌላ በኩል በተቃዋሚም ሆነ በሌላ ስም ትህነግ ጋር ስምምነት ለመፈፀም የሚደረግን ሂደት የህዝብ ለህዝብ እያስመሰለ፣ የትህነግን ወረራ የሚያድበሰብስም የትህነግና ብልፅግናን የጓዳ ውልና የወረራ አላማ የሚያስፈፅም የአማራ ጠላት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
14.1K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-01 14:35:07 ያዘዝነውን ካላስፈፀመ መከላከያንም እናቀምሰዋለን ብለዋል! በአማርኛ ነው! ቀጥታ ትዕዛዝ ነው!


ሰሞኑን ትህነግ ባደረገው ሰልፍ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር መከላከያ በተገኘበት በአማርኛ ጭምር ያስተላለው ዛቻ ነው። መከላከያ የምንፈልገውን ካላስተገበረ ሱሪያችን ያውቃታል። ይቀምሳል ተብሏል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር የአማራን ርስቶች ለመያዝ ህፃናትና አዛውንቶች ይዘን እንደማንመጣ ይታወቃል ብሏል። እንዳሉት ተፈናቃይ ይዘው አልመጡም። ታጣቂ ነው ይዘው የመጡት። መከላከያም ባዘዝነህ መልኩ ካልሰራህ ሱሪያችን ታውቃታለህ ተብሏል። ይህ ጌታቸው ረዳ የሚያዘው ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር ነው።


በጓዳ ውሉ ብቻ እንሄዳለን አላሉም። አለፍ ብለዋል። መከላከያን እንደ ቀበሌያቸው ሚሊሻ እናዘዋለን፣ ካልሆነ እናቀምሰዋለን ብለዋል።
14.0K viewsedited  11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-01 13:44:25
15.0K views10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ