Get Mystery Box with random crypto!

የወረራ ዝግጅት! ራያን የወረረው ትህነግ ጠለምትንና ወልቃይትን ለመውረር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ | Getachew shiferaw

የወረራ ዝግጅት!

ራያን የወረረው ትህነግ ጠለምትንና ወልቃይትን ለመውረር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። በዚህም መሰረት በሱዳን በኩል፣ አርሚ 11 ጠለምትን ለመውረር፣ አርሚ 17 ወልቃይትን ለመውረር ዝግጅት ላይ ነው፣ አርሚ 35 ከአክሱም ወደ ሽሬ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ጥቅምት 24 መከላከያን የመቱበትን ማስታወሻ ያደረጉት "አርሚ 24" ደግሞ ራያን የወረረው ነው።

ይህ በሆነበት ብልፅግና የአማራ አስተዳደሮችን በሕገወጥ መልኩ አፍርሶ በተፈናቃይ ስም የወረራ በር እየከፈተና እያገዘ ይገኛል። እንደ ገለልተኛ "ትጥቅ መፍታት አለባቸው" እያለ የሚቀልደውም ዝግጅታቸውን ስለማያውቅ አይደለም። ማዘናጊያ ነው።

በሌላ በኩል በተቃዋሚም ሆነ በሌላ ስም ትህነግ ጋር ስምምነት ለመፈፀም የሚደረግን ሂደት የህዝብ ለህዝብ እያስመሰለ፣ የትህነግን ወረራ የሚያድበሰብስም የትህነግና ብልፅግናን የጓዳ ውልና የወረራ አላማ የሚያስፈፅም የአማራ ጠላት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።