Get Mystery Box with random crypto!

የሚገርሙ፣ የሚያሳዝኑም ጉዳዮች ናቸው! 1) የጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ከመቀሌ ውጭ ተንቀሳ | Getachew shiferaw

የሚገርሙ፣ የሚያሳዝኑም ጉዳዮች ናቸው!

1) የጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ከመቀሌ ውጭ ተንቀሳቅሶ ስብሰባ ማድረግ እንደማይችል ራሱ ጌታቸው ለትግራይ ሕዝብ ተናግሯል። ትግራይን የሚያስተዳድረው ከጦርነቱ በፊት የነበረው፣ ወንጀለኛ የተባለው መዋቅር ነው። ይህን ጌታቸው ረዳ በሚዲያ ወጥቶ ያረጋገጠው ነው። ይህ ህገወጥ መዋቅር ስለሆነ ነው ጊዜያዊ አስተዳደር ማዋቀር ያስፈለገው።

ትግራይ ውስጥ ከመቀሌ ውጭ ስብሰባ እንኳ ማድረግ የማይችለው የጌታቸው ረዳ አስተዳደር፣ በህጋዊ ስምምነት የተሰጠውን ትግራይን እንዳያስተዳድር ተደርጎ፣ በማያገባው ከትግራይ ውጭ ያሉትን የአማራ ግዛቶች እንዲያስተዳድር ነው የተደረገው። ሰሞኑን ትህነግ በወረራቸው የአማራ አካባቢዎች ጊዜያዊ አስተዳደሩ መዋቅሩን አሰማርቷል። ትህነግ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ የፈቀደለት የወረራ አላማ ስለሆነ ነው። ትግራይ ውስጥ አንድም ቀበሌ እንዳያስተዳደር የተደረገው ጌታቸው የአማራን አካባቢዎች ግን በህገወጥ መንገድ እንዲይዝ ተደርጓል።

2) ሰሞኑን በትግራይ ፖለቲካ አጀንዳ የሆነ ጉዳይ አለ። ትህነግ የአማራ አካባቢዎች ተወልደው ያደጉትን አመራሮቹን "ትግሬ አይደላችሁም" እንዳላቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራር ረዳኢ ሓለፎም ቃል በቃል ተናግሯል። የትግሬ ካባ የሚሰጠንም የሚቀማንም ሌላ ቡድን አለ ብሏል። የአድዋውን ቡድን ነው። ታዲያ ራያ ያደጉትን አመራሮቹን "ትግሬ አይደሉም። ባንዳ ናቸው።" ወዘተ እያለ የሚፈርጅ ራያን መሬቱንና መሬቱን ብቻ እንደሚፈልግ ግልፅ ነው። አመራሮቹን በጠላትነት የፈረጀ ለሕዝቡማ ያለው ጥላቻን መገመት ቀላል ነው። በተደጋጋሚ በተግባርም የታየ ነው።

3) ራያን የወረረው የትህነግ ታጣቂ "አርሚ 24" ይባላል። መከላከያን በመታበት ጥቅምት 24 የተሰየመ ነው። መከላከያ የተገደለበትን ቀን ማስታወሻ ያደረገውን
ኃይል ነው እያገዘ የሚገኘው።

4) የሰላም ስምምነቱ ያለ ምንም ማወላዳት የደነገገው፣ የጊዜ መንዛዛት ያልተቀመጠበት የትጥቅ መፍታት ነው። በማያሻማ መልኩ በአንድ ወር ውስጥ ትጥቅ ይፍቱ ተብሎ ነበር። ጭራሽ አስታጠቋቸው። መከላከያ ትግራይን ይረከብ ተብሎ ነበር። ጭራሽ መከላከያ ከትግራይ ወጥቶ አማራ ላይ ዘምቶ፣ ትጥቅ መፍታት የነበረበት ትህነግ አማራ ክልልን በኃይል እንዲይዝ ተደረገ

5) ትህነግ ባለፉት ወረራዎች ዘረፋ የሚፈፅሙትን በየጦሩ አደራጅቶ አሰማርቷል። በዘረፉት ልክ ጥቅም አግኝተዋል። እንደ ጀግና ታይተዋል። ይህ ኃይል ግን ወደ ትግራይ ተመልሶ አረመኔ ሆነ። የአርሶ አደር በሬ አርዶ መብላት፣ የተቋማትን ብረታብረት መዝረፍ ወዘተ። ሰሞኑን የትግራይ ክልል ውሃ መሳቢያ ብረቶች እየተዘረፉ መሆኑ በስፋት እየተሰራጨ ነው። ይህን የራሴ የሚለውን ትግራይን እየዘረፈ ያለ ኃይል ነው ጠላቴ ወደሚለው አማራ ይዘውት የመጡት። ከራያ ብቻ ከ50 ሺህ በላይ ሕዝብ የተፈናቀለውም ይህ አረመኔ ኃይል በሚፈፅመው ወንጀል ምክንያት ነው።

ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው አማራ ላይ ነው!