Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የቴሌግራም ቻናል አርማ getachewshiferaw — Getachew shiferaw
የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.30K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-05-12 11:03:33 ነገሩ ይበልጥ ግልፅ ሆኗል!

ለእነ አልቡርሃን መሳሪያ የሚያቀብለው ባለሀብት ታስሯል። የትህነግ/ህወሓት ባለስልጣን ሚስጥር ያወጣብን ጌታቸው ረዳ ነው ሲል ከስሷል።

1) ሰሞኑን ታደሰ ወረደ ቀርቦ በተናገረበት ሚዲያ ከሶስት ወር በፊት ጌታቸው ረዳ ከስልጣን ያባረረው የህወሓት አመራርም ቀርቦ ጌታቸው ሚስጥር እንዳወጣ ጠቁሟል። ሚዲያውም ርዕሱን በግልፅ ጌታቸው ለአረብ ኢሜሬትስ ባለስልጣናት መናገሩን በሚገልፅ መልኩ ነው ያስቀመጠው።

2) የህወሓት ባለስልጣን የሆነው አባዲ ዘሙ ልጅ ዳዊት ገብረእግዚያብሔር የሚባለው የሞንጆሪኖ ወንድም በሌላ አገር በኩል ወደ ትግራይ ሲገባ የተቀበለው ጌታቸው ረዳ እንደሆነና ከእነ ጌታቸው አሰፋ ጨምሮ ከትህነግ/ህወሓት አመራሮች ጋር መምከሩን ሰሞኑን ፅፎ ነበር። ይህ ባለሀብት በትህነግ የስልጣን ዘመን ለመከላከያ ጭምር መሳሪያ ደላላ የነበረ ሲሆን ከትህነግ/ህወሓት ጋር በነበረው ጦርነት ለትህነግ በሱዳን በኩል በአልቡርሃን ድጋፍ መሳሪያ አስገብቷል። ከአረብ አገር የመሳሪያ ደላላዎች ጋር የሚሰራ ሰው ነው። በጦርነቱ ወቅት ከትግራይ በጀት መዳቢዊ እህቱ ሞንጆሪኖ ነበረች። በአንድ ግምገማቸው ሞንጆሪኖ ወደ ሱዳን የላከችው የፀረ ድሮን መግዢያ መበላቱ ታምኖበታል። ዳዊትና እህቱ በሱዳን በኩል በአልቡርሃን እገዛ መሳሪያ ሲገዙ የከረሙ ናቸው። አሁንም ለአልቡርሃን መሳሪያ ማስገባታቸውን መቀጠላቸው ተሰምቷል።

3) የኤርትራ ደህንነት መስሪያ ቤት መረጃ የሚሰጠው አንድ ሁነኛ የኤርትራ ሚዲያ ደግሞ ባለሀብቱ በቅርቡ የሱዳን ጦርነት ወቅት ለአልቡርሃን መሳሪያ እያስገባ እንደሆነ ተደርሶበታል ብሏል። በዚህ ምክንያት ሰሞኑን ባለሀብቱ የታሰረው በአረብ ኢሜሬትስ ሲሆን አረብ ኢሜሬትስ የፈጥኖ ደራሹ ደጋፊ፣ ትህነግ በእነ ዳዊት በኩል ለአልቡርሃን መሳሪያ አድራሽ ሆነው የጥቅም ግጭት ውስጥ እንደገቡ ተፅፏል። የኤርትራው ደህንነት ምንጭ ዳዊት የተያዘው ከመቀሌ በወጣ ሚስጥር እንደሆነ ገልፆአል።

4) የትህነግ/ህወሓት አክቲቪስቶች ደግም ባለሀብቱን ያስያዘው ጌታቸው ረዳ ነው ብለው እየፃፉ ነው።

5) ለአልቡርሃን መሳሪያ የሚያቀርበው የሞንጆሪኖ ወንድም በህገወጥ መንገድ ድንበር አቆራርጦ ትግራይ ገብቶ ከትህነግ/ህወሓት አመራሮች ጋር መነጋገሩ ከዚህም ከፍ ያለ አላማ መኖሩን ያሳያል። ሰሞኑን የታሰረው ጅቡቲ ውስጥ ነው ወዘተ የተባለው ከትግራይ በጅቡቲ በኩል ሲሸኙት ይሁን ደጋግሞ ሲመላለስ አልታወቀም። ነገር ግን ወደ ትግራይ የተመላለሰበትን አላማ ለመደበቅ "ጅቡቲ ያለውን ፕሮጀክቱ ሲጎበኝ ተያዘ" እያሉ ለመሸፋፈን ጥረዋል።

አጠር ሲል!

1) ትህነግ ከታጣቂ አልፎ በትጥቅም ከአልቡርሃን አቅርቦት በማገዝ ጋር መሆኑን አመራርና አባላቱ አምነዋል።

2) እነ ጌታቸው ረዳ ከትህነግ/ህወሓት አላማ ስለተለዩ ሳይሆን በአካሄድ ልዩነትና ስልጣን ጉዳይ በሱዳን ጦርነት መሳተፋቸውን ያመኑ መሆኑን።

3) በጊዜያዊ ስልጣን ከጌታቸው ረዳ ጋር ልዩነት ያላቸው ጌታቸው ረዳ አሳልፎ ሰጠን ማለታቸውን

4) የትህነግና የአልቡርሃን ጉዳይ የዓለም አቀፍ መሳሪያ ዝውውርንም የሚጨምር፣ በዚህ ጉዳይ በተጨባጭ የተሳተፈው ባለሀብት መታሰሩንም የሚያሳይ ነው።

5) ባለሀብቱ ለሱዳኑ ጀኔራል መሳሪያ ከማቅረብ አልፎ በህገወጥ መንገድ ድንበር አቆራርጦ ትግራይ ድረስ መጥቶ ከእነ ጌታቸው አሰፋ ጋር የመከረው መቀሌ ናፍቃው ሊሆን አይችልም።
17.0K views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 21:55:52
17.4K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 21:55:41 በራሳቸው አክቲቪስት ተጋለጡ!

የእነ ጌታቸው ረዳ የቅርብ ሰው፣ ዳዊት ከበደ ትህነግ በመግለጫ ሊያስተባብለው የማይችለውን ሚስጥር አውጥቷል። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ትህነግ/ህወሓት ከአልቡርሃን ጋር ሆኖ ወጋኝ በማለቱ ማስተባበያ የተሰጠ ቢሆንም ውስጥ አዋቂያቸው ዳዊት ግን የባሰ ነገር ይዞ መጥቷል።

ጌታቸው ረዳ UAE ሄዶ ከአልቡርሃን ጋር ሆነው እየተዋጉ መሆኑን አምኖ እንደመጣ አስቀምጧል። ዳዊት ከበደ። የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጌታቸው ረዳ ካመነ በኋላ ነው መግለጫ ያወጣን ይላችኋል የትህነግ ሚስጥረኛ።

ጌታቸው ረዳ አልቡርሃንን እኛ እየደገፍነው እንገኛለን ብሎ በትህነግ/ህወሓት ላይ መረጃ አውጥቷል ብሎ ነው የፃፈው። የሰሞኑ ማስተባበያ በህወሓት አመራሮች ዘንድ ጌታቸው ረዳ ነው ጠቋሚ እየተባለ እንደሆነ ነው የተገለፀው።

ትህነግ/ህወሓት በሱዳን ጉዳይ እጁ እንደሌለበት ቢናገርም ውስጥ አዋቂያቸው ግን እነ ደብረፅዮን የሰጡትን መረጃ ፅፎታል። ስለሆነም ራሱ ጌታቸውረዳ ከአልቡርሃን ጋር እየሰራን ነው ብሎ አምኗል። ይህን ዜና ሊያስተባብሉ የጣሩት እነ ኤርሚያስ ለገሰ ውሃ በላቸው ማለት ነው።
16.5K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-06 19:11:34 ብልፅግና ይህን ጉድ መሸፈን አይችልም! ፈፅሞ! ታደሰ ወረደ ሳይሸፋፈን ጥሬውን ዘርግፎታል።


"ትጥቅ አልፈታንም። ፍቱ ያለንም የለም።"


ታጣቂም በሰፋሪ ስም ይመለሳል። ንፁሃንን የጨፈጨፉት ከእነ መሳሪያቸው እንዲገቡ ከብልፅግና ጋር መስማማታቸውንም ገልፆአል።


ይመለሱ የተባሉት ተፈናቃይ ሳይሆኑ አዲስ ሰፋሪዎች ናቸው!

ታደሰ ወረደ ወደ አማራ ግዛቶች ተፈናቃይ ተብሎ ይመለስ የተባለው ሰፋሪ እንደሆነ ሳያስበው አውጥቶታል። ወልቃይትና ራያን የማያውቁ ከተለያዩ የትግራይ ክፍሎች የነበሩ አካላት ናቸው ተፈናቃይ ተብለው እንደ አዲስ የሚሰፍሩት። ሊያስተካክል ሞክሯል። እውነታው ግን አምልጦታል።


በጓዳ ውል የተፈፀመውን ታደሰ ወረደ ተናግሮታል። ብልፅግና ይህን መረጃ ማስተባበል አይችልም።
13.5K viewsedited  16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-06 05:10:01
14.4K views02:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-06 05:09:32 የሱዳን ዋና ዋና ሚዲያዎችኀ ትህነግ/ህወሓት የአልቡርሃን ቆጥረኛ ሆኖ በሱዳን እየተዋጋ መሆኑን ቀዳሚ አጀንዳ አድርገዋል። ይህን ቅጥረኛ ኃይል ነው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተፈናቃይ ብላችሁ መልሱ እየተባለ ያለው።
13.3K views02:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 16:56:54
13.0K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 16:56:49 የፕሪቶሪያ ስምምነት መቆመሪያቸው ነው!

ስምምነቱ እነ ጌታቸው ረዳ ከአማራ ለመንጠቅ የሚፈልጓቸውን ግዛቶች "የተወረሩ" አይላቸውም። "አወዛጋቢ" ነው የሚላቸው። በዚሁ ስምምነት መሰረት የጥላቻና የጦርነት ቅስቀሳ የተከለከለ ነው። በትህነግ በኩል ፈራሚው ጌታቸው ረዳ ግን አሁንም "ወራሪ" እያለ እየፃፈ ነው። የሰላም ስምምነት ተብሎም ለእሱ አማራ ወራሪ ነው። ስምምነቱ መቋመሪያ ካርድ እንጅ እንደማያከብሩት ይታወቃል። በጓዳ ግዛቶቹን አሳልፎ ለመስጠት የሚስማማው የአብይ አገዛዝም በስምምነቱ መሰረት ባቋቋመው ኮሚቴ ይህን እንደማይገመግም ይታወቃል።

የአማራ ክልል ጉልት ካድሬ ደግሞ በስምምነቱ መሰረት በስሩ እንዲቆይ የተወሰነውንም አስተዳደር አፍርሶ ትግራይ ውስጥ አንድ ቀበሌ በቅጡ ለማያስተዳድረው፣ ስካይ ላይት መቀመጫውን ላደረገው ጌታቸው ረዳ አሳልፎ ሰጥቷል። በዚህ ከቀጠለ አብይ አጠቃላይ አማራ ክልልን ለጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ቢሰጠውም ከዝምታ የተሻለ ከአማራ ክልል ካድሬ እንደ አማራጭ የሚቆጠር ስልት ያለ አይመስልም።

በዚህ በዓል መልዕክት ቀርቶ በሌላም ጊዜ በአማራ ላይ አፍ መክፈትን የህዝብ መሰብሰቢያ ካደረጉት የትህነግ አመራሮች ውጭ ጦርነት እየቀሰቀሰ ያለ አይመስልም። ለትንሳኤ በዓል መልዕክት እንኳን አማራን በለመዱት ክፍታፍነታቸው ከመዝረፍና ከመውቀስ የሚመለሱ አይደሉም።
12.6K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 08:57:26 የባልደራስን ንቁ አባላት ያሳሰረው ኤርሚያስ ለገሰን ተንኮል ተመልከቱ!

የኤርሚያስ ወዳጅ የነበረው ቴድሮስ ፀጋዬ ሰሞኑን ኤርሚያስ የባልደራስ ንቁ አባላትንና የአዲስ አበባ ወጣቶችን እየጠቆመ እያሳሰረ እንደሚገኝ በቀጥታ ስርጭት ተናግሯል። ይህን የባልደራስ የቅርብ አመራሮችም አረጋግጠውልኛል።

ትናንት የሰራውን ፕሮግራም እንኳን ተመልከቱ። ያሳሰራቸው የባልደራስ ንቁ አባላት መካከል ናቲን ፎቶ የፊት ገፅ ላይ ሆን ብሎ አቀናብሮ ከሚከሳቸው የፋኖ አባላት ጋር አቅርቧል። ኤርሚያስ ለፕሮፖጋንዳ የሚጠቀምበትን እያንዳንዱን ጉዳይ የሚያውቅ ሰው ነው። የፊት ገፅ ሲያሰራ ምን ማስተላለፍ እንደፈለገ ግልፅ ነው። ከሰላማዊ መንገድ ውጭ የትጥቅ ትግሉ ላይ ፈፅሞ የሌሉበትን ወጣቶች ፎቶ ሾፕ እየሰራ ጭምር የሀሰት ጥቆማውን እውነት ለማስመሰል እየሰራ ያለ አደገኛ ሰው ነው።

ከቅርቡ የአዲስ አበባ ክስተት በኋላ አዲስ አበባ ላይ ሽብር የሚፈፅሙት የከተማው ተወላጆች ጭምር አሉ ብሎ የአዲስ አበባን ወጣት በሀሰት ከስሷል። በተለይ በተለይ ባልደራስ ሰልፍና ስብሰባ ሲያደርግ ንቁ እንቅስቃሴ ያደርጉ የነበሩ፣ በሚዲያ ያግዛል ተብሎ መረጃ የሚሰጡትና ለፓርቲው ሰላማዊ እንቅስቃሴ በተለያያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ግሩፕ ውስጥ የነበሩትን ለአገዛዙ እየጠቆመ አሳስሯል። የባልደራስ አመራሮችም ያረጋገጡት መረጃ ነው።
12.8K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-03 19:17:25 ይህንማ አላያችሁትም! አላያችኋትም!

ታደሰ ወረደ በቀደም አብይ ጋር ተሰብስቦ፣ ትናንት ደግም ከሳምንት በፊት "መወገድ አለበት" ብላ ፕሮግራም ከሰራችው ሴትዮ ጋር አመሸ። በቀደም ተመስገን ጥሩነህ ጋር ተገማግም፣ ተመስገን በጀኖሳይድ መጠየቅ አለበት ካለችው ጋር ተመሰጋገነ።

እንዲች ናትና!

በነገራችን ላይ ታደሰ ወረደ ከኮሚቴው ጋር የሚገማገመውን ለትህነግ/ህወሓት ሚዲያዎች ያደርሳል። ትናንት ማታ ግምገማውን በሙሉ ለኤርሚያስ ሰጥቶ ለእነሱ በሚጠቅም መልኩ አሰራው፣ ራሱ ደግሞ በዚህ ሚዲያ ቀረበ።

ልጨምርላችሁ! በዚህ ሚዲያ ለታደሰ የቀረበው ጥያቄ ኤርሚያስ የሰራበት ነው።
12.9K views16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ