Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የቴሌግራም ቻናል አርማ getachewshiferaw — Getachew shiferaw
የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.30K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-04-29 13:48:11
15.6K views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 13:48:04 የትህነግ ታጣቂ ራያ ላይ እየፈፀመው ያለው ሰቆቃ በገለልተኛ ሚዲያ እይታ!

ከስር ያለው መረጃ ዓል አይን አማርኛ የትህነግ ታጣቂ እየፈፀመው ያለውን ተነግሮ የማያልቅ ሰቆቃ በወረራ ስር ያሉትን ነዋሪዎች አናግሮ ከዘገበው የተወሰደ ነው።

#የትግራይ ታጣቂዎች ከመጡበት ዕለት አንስቶ ንብረታችን እየተነጠቀ ነው፡፡ ለገበያ የደረሰ ሀብ ሀብ አትክልቴን በልተውብኛል ሲጠግቡ ደግሞ በያዙት ጦር መሳሪያ በሰደፉ እና በአፈሙዙ እየመቱብኝ ነው”

#በቀበሌያችን ከገቡበት ከሰኞ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በገበሬው ቤት እየገቡ እየደበደቡን ነው። አርሶ አደር ጦር መሳሪያ አምጡ እያሉ እኛ ገበሬዎች ነን ፖለቲካ አናውቅም ብንልም ሊተውን አልቻሉም"

#ከዚህ በፊት አብረውን ይኖሩ የነበሩ ነገር ግን በስጋት ምክንያት ወደ ትግራይ ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች ካሳለፍነው ሰኔ እና ግንቦት ወር ጀምሮ እየገቡ መኖር ጀምረዋል፣ ሳይገቡ የቀሩት ከዚህ በፊት በነበረው አስተዳድር ጊዜ ህዝብን ሲያንገላቱ እና ሲያማርሩ የነበሩት ብቻ ቀርተው ነበር"

#ታጣቂዎች ሲቪል እየለበሱ ወደ ከተማዋ ነዋሪ መስለው እየገቡ ነው፣ የመንግስት ተቋማትን እየዘረፉ እና ፋይሎችን እያወደሙ የከተማዋ ነዋሪዎችንም ፍርሃት ውስጥ እንዲገባ የተለያዩ ጫናዎችን እያደረጉ ነው። በከተማዋ ያለው የፌደራል የጸጥታ ሀይል ቢኖርም ነዋሪውን ከመሰደድ አልታደገውም"

#የፌደራል መንግስት ለራያ እና አላማጣ ጉዳይ ዘለቄታዊ መፍትሔ ይሰጠዋል ብለን እየጠበቅን ለትግራይ ታጣቂዎች አሳልፎ ሰጥቶናል።

#በሰሌን ውሃ ቀበሌ የሚኖረው ሌላኛው አስተያየት ሰጪ በበኩሉ የትግራይ ታጣቂዎች የራያ እና አላማጣ የገጠር ቀበሌዎችን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ መቆጣጠራቸውን፣ በየቀኑ አዳዲስ እና ተጨማሪ ታጣቂዎች ወደ አካባቢዎቹ እየገቡ መሆኑን አክሏል፡፡
ታጣቂዎቹ በየሰው ቤት እየገቡ የልጆችን ምግብ ሳይቀር እየበሉ እንደሆነ፣ ለባሏ የምሳ እቃ ለማድረስ ወደ እርሻ ቦታ እየሄደች ያለችን እናት ለአማራ ታጣቂ ልትሰጪ ነው በሚል እያንገላቱ ነው ያሉት እኝህ አስተያየት ሰጪ ታጣቂዎቹ ይህን ሲያደርጉም የፌደራል የጸጥታ ሀይሎች እያዩ የማስቆም ፍላጎት እንደሌላቸውም ነግሮናል፡፡

#ከዚህ በፊት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ወደ መቀሌ እና ሽሬ የሄዱ ነዋሪዎች ወደ ቀድሞ ቤታቸው ተመልሰው አብረን በጋራ እያረስን እና እየኖርን ቢሆንም ታጣቂዎቹ በድንገት መጥተው ለእንግልት እንደዳረጓቸውም አክሏል፡፡

#ታጣቂዎቹ በየጊዜው እየሰበሰቡም ከእንግዲህ እምናስተዳድራችሁ እኛ ነን፣ የያዛችሁትም የአማራ ክልል የነዋሪነት መታወቂያ ከእንግዲህ አይጠቅማችሁም፣ ልጆቻችሁን አምጡ እና ለአማራ ታጣቂዎች ድጋፍ እያደረጋችሁ ነው የሚሉ ወከባዎችን እያደረሱባቸው እንደሆነም እኝህ አስተያየት ሰጪ ተናግረዋል፡፡

#ወቅቱ የሚያዚያ ወር አዝመራ የምናዘምርበት ቢሆንም እርሻችንን ትተን በየቀኑ ምን እንሆን ይሆን የሚል ስቃይ ውስጥ ነን"
16.2K views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 09:43:57
14.1K views06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 09:43:47 ተፈናቃይ ብለው የሚያስገቡት ይህንን ዘራፊ ኃይል ነው!

ትህነግ በወረራው ወቅት አማራና አፋርን መዝረፍን ጀብዱ አድርጎ ለወጣቱ አስተማረው። አትክልትና ፍራፍሬ ጭምር "ከአማራ ክልል የመጣ" እየተባለ በሞንታርቦ እየተጮኸ ሲሸጥ ነበር። የአማራ ክልል ታርጋን አንስተው ታርጋ አልባ መኪና የሚነዱት "አምጥቶ ነው" እየተባሉ በጀብድ ተነገረላቸው። እርጉዝ ሳይቀር ለዘረፋ መጥታ አማራ ወልዳ ተይዛለች። ወጣቱ "እኔም ይህን አምጥቻለሁ" እያለ በጀግንነት እንዲያወራ ተደረገ። ከጦርነቱ በኋላ ግን ዘረፋውን ትግራይ ውስጥ ቀጠሉት። አማራ ላይ ጀግና የተባሉበት ነዋ! የቀራቸው ነገር የለም። ፍርድ ቤት ስላልቻለ እንደ ድሮው በአደባባይ በዚህ መልክ መቅጣት ጀምረዋል።

ታዲያ ወደ ራያ የላኩት ይህን ዘራፊ ኃይል ነው። አዲስ ልብስና ጫማ ሳይቀር እያስወለቀ ሲወስድ የሚታወቅ ዘራፊ ራያን እያራቆተ ነው። በወረራው ወቅት ሲዘርፍ ጀግና ያሉትና ከወረራ በኋላ ትግራይን ያስመረረውን ነው ወደ ራያ የላኩት። ወደ ጠለምትና ወልቃይትም ለማስገባት የወሰኑት ይህ ሰው በላ የሆነን ኃይል ነው።
13.4K views06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 17:40:00
15.2K views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 17:39:51 አላማቸው ተፈናቃይ መመለስ አይደለም! ማፈናቀል ነው! እየተተገበረ ያለው የጓዳ ውል እንጅ የሰላም ስምምነት አይደለም!

ተፈናቃይ በመመለስ ሰበብ ከ50 ሺህ በላይ ንፁሃን አፈናቅለዋል። ድሮም ይህ ነው የሚባል ተፈናቃይ አልነበረው። ወደራያ አካባቢዎች የገባው የትህነግ ገዳይና ዘራፊ ታጣቂ፣ ትግራይ ውስጥ በወንጀል ያስቸገራቸው ዘርፎ እንዲሄድ የተደረገ ኃይልና የትህነግ መዋቅር ነው። ሁሉም ከመግደል፣ ከመዝረፍና ከማፈናቀል ውጭ መጀመሪያ የተባለውን ተፈናቃይ መመለስ ሲናገሩ አይሰሙም! አላማቸውም በቀል፣ ዝርፊያና ርስት መቀማት እንጅ ተፈናቃይ መመለስ አይደለም።

እንደ አንድ ጠላት ብለው እንደፈረጁት አካባቢ መግደል፣ መዝረፍና ማሳደድ ነው የተያያዙት። የያዙት አካባቢ ሀብትና ንብረት ወደ ትግራይ እየተጫነ፣ መጫን ያልቻሉትን እያወደሙ ነው። አላማቸው ተፈናቃይ መመለስ አይደለም። ማፈናቀል ነው። ትህነግ በቀሉን ይወጣል። አብይ ለምዕራባውያኑ "የአማራን ግዛት ሰጥቻቸዋለሁ" ብሎ እርዳታ ይለምናል።

አላማው የጓዳው ውል ማስፈፀም እንጅ በአደባባይ በመግለጫ የሚነግሩን ተፈናቃይ መመለስ አይደለም። አብይ በአማካሪዎቹ በኩል በአንድ ስልክ ትዕዛዝ ፀጥ ረጭ የሚያደርገው ብአዴን ደግሞ ይህ ሁሉ እየተፈፀመ እንዳላየ ዝም ብሏል። አንድ ቀን የሰጣት መግለጫ እንኳን ቁጣ አስተናግዳበት ከዛ በኋላ ይህ ሁሉ ህዝብ ሲፈናቀል ትንፍሽ አላለም።
15.1K views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 22:47:54 ጥብቅ ሚስጥር ነው!

ዳንኤል ብርሃነ ወደ ምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ነው ያደገው። ሌሎች የትህነግ ሰዎች ለመግለፅ የማይደፍሩትን ሚስጥር ዘረገፈው! የሰምኑ ወረራም የሌላው ችግር ምንጭ ይህ ዳንኤል የነገረን አካሄድ ነው!

1) ትህነግ ስምምነቱ በተለይም ትጥቅ ማስፈታቱን ጨምሮ ሌሎችን በጓዳ ውል እንዲዘገይ ያደረገው በእርዳታና ብድር መሆኑን በራሱ ተሞክሮ ይነግረናል። ዳንኤል የአውሮፓውን ዲፕሎማት በብድርና እርዳታ ጫና አድርገልን ያለው በራሱ ተነሳሽነት አይደለም። የዋናው ትህነግ መጫዎቻ ስለሆነ ነው። የኦሮሞ ብልፅግና ካለው ፀረ አማራ ፍላጎት ባሻገር፣ ትህነግ ትጥቅ መፍታቱንም ሌላውንም በጓዳ ውል ያስቆየው በዚህ መንገድ ነው። ዲፕሎማቶች በየቀኑ ወደ መቀሌ ሲመላለሱ ለዚህ እንደሆነ ብልፅግና ያውቃል። ፍላጎቱም ነው።

2) ዲፕሎማቶቹም ሌላ ጥያቄ ሲጠየቁ ያለምንም ማወላዳት "ትጥቅ አትፈቱም" የሚሉት የትህነግ የመጀመሪያ ፍላጎት እንደሆነ ስለሚያውቁ ነው። ብልፅግናም በጓዳ የተዋዋለው፣ የአማራን ርስቶች ለብድርና እርዳታ ቀብድ ያደረጋቸው መሆኑን ማሳያ ነው።

3) ሰሞኑን ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት የአማራን ርስቶች አሳልፎ የመስጠት የአብይ አህመድ እና የትህነግ የጓዳ ውል ተግባራዊ እንዲሆን የሚደረገው አብይ ብድርና እርዳታ ሲፈልግ፤ የሞቀ ድርድር ላይ ሲሆን ነው። የሰሞኑ የራያና የሌሎች አካባቢዎች ወረራ አብይ ከዓለም የገንዘብ አበዳሪዎች ጋር ሲደራደር የተፈፀመ ነው። ዳንኤል ያወጣው ሚስጥርም ከዚሁ ጋር የተገናኘ ነው።

4) እየተተገበረ ያለው የሰላም ስምምነት አይደለም። አብይ የአማራን ርስቶች በብድርና እርዳታ፤ በጓዳ ውል ከሰላም ስምምነቱ በተቃራኒ አሳልፎ ነው እየሰጠ ያለው።

ዳንኤል በግልፅ ተናገረው እንጅ የምናውቀው ነው። ዳንኤል ያወጣው ዲፕሎማቶቹ በትህነግ የሚነገራቸውንና እየሆነ ያለውን እውነታ ነው። ይህ ቀላል ጉዳይ አይደለም። ጥብቅ ሚስጥር ነው!
12.9K viewsedited  19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 20:23:40
15.6K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 11:00:39 በመስዋዕትነቱ ልክ ብስለት ያስፈልጋል!

ባለፈው አንድ አመት ገዥዎቹ አማራውን በሀሰት በክፉ ጎን ለማሳየትና ለመድፈቅ ያደረጉት ጥረት እንዳይሳካላቸው የተደረገውን ያህል በሂደቱ በርካታ መስዋዕትነት ተከፍሏል። አገዛዙ በጥላቻ በርካታ ሕዝብ ጨፍጭፏል። በርካቶች ተሰውተዋል። የምናውቃቸው የፋኖ አመራሮች፣ ቤተሰቦቻቸውና ጓዶቻቸውን ገብረውበታል። ሕዝባችን በርካታ ውጣ ውረድ አይቷል። በአማራው ላይ የተፈፀመው ወረራና የአማራው ተቃውሞ በብልሃት ከተኼደበት ለሌሎች ተስፋ በርካታ ጊዜ ታይቷል። ይህ የሚሆነው ግን ትግሉ በዋጋው ልክ ስሌት የደረገበት ሲሆን ነው።

1) ትግሉ የህልውና እንደመሆኑ መረር ያለ ግምገማ ያስፈልገዋል። አፍኖ ቆይቶ ግለሰቦች ወይ ቡድኖች ላይ መዝመት አያዋጣም። የሚያዋጣው አጠቃላይ አካሄድን መገምገም ነው። ለአብነት ያህል ብልፅግና ህዝብ ላይ ከሚያደርሰው ጥቃት ባለፈ ፕሮፖጋንዳው ላይ በርትቷል። የሚጠላውን ሕዝብ እየሰበሰበ ነው። ከአማራ ክልል አልፎ ለይምሰልም ይሁን በተግባር በውጭ አገር ጭምር ስብሰባ እያደረገ ነው። እንዴት? ለምን? ተብሎ መጠየቅ አለበት። በፖለቲካ "ይታወቃልኮ"፣ "ምንም አያመጣም" ወዘተ የሚሉ ማቃለያዎች፣ ጥቅል ፍረጃዎች ትግልን ገዳይ ናቸው። ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ ብቻ ማሳበብም የእለት ማስተንፈሻ ነው። ትግል እንደ አጠቃላይ በየጊዜው ይገመገማል። ግምገማ የኢህአዴግም፣ የብልፅግናም አይደለም። የትግል ማከሚያ ስልት ነው!

2) መሬት ላይ ያሉትን አንድ ካልሆኑ እያለ የሚጨነቀው፣ የሚወቅሰው የማህበራዊም ሆነ የሌላው ሚዲያ አካል ራሱ ዕዝ ሊኖረው ይገባል። መሳሪያ ከያዙት፣ ውጊያ ላይ ከሚውሉት፣ ብዙ የመነጋገር እድል ከሌላቸው ይልቅ ሚዲያ ላይ ያለው የመነጋገር እድልም አቅምም አለው። ለየራሱ ሰበር ዜና፣ ለየራሱ አጀንዳ ያልተናበበ አካሄድን እየመረጠ፣ በግምትና ባልተሰላ መንገድ እየሄደ መሬት ላይ ያሉት አብረው ቢሰሩ እንኳን ትግሉን የሚያበላሸው የሚዲያ ትርምስ ነው።

3) ትግሉ የህልውና ነው ካልን፣ ስለ አራት ኪሎ ካሰብን የከበደ ነገር የሚገጥመን ጠላት ካልነው ኃይል ብቻ አይደለም። የመጀመሪያው ፈተና ለዛ አላማ ብቁ ለመሆን ራስን መግዛት ነው። በዛ አላማ ልክ ራስን ማስተካከል ነው። ባለፉት ወራት የተወሰኑ ምክሮችን ፅፌ ነበር። ትግል ላይ ያሉ አካላት አማራ ውስጥ ያሉትን ኃይሎች ለመያዝ ዋጋ መክፈል ካልቻሉ እንቅፋት የከበደ ይሆናል። ለአብነት ያህል የሀይማኖት አባቶች ጋር ያለው አንዱ ነው። ሚሊሻ ሌላኛው ችግር ሆኗል። እነዚህ አካላት ጋር ተቃርኖ በጨመረ ቁጥር ብልፅግና ቦታ ያገኛል። ጦርነት ነውና የግዳቸውን ወገን ይፈልጋሉ።

የሰፈርህን ሚሊሻ ሳታሳምን የብሔር ድርጅቶች ጋር ተስማምተህ አገር ልትመራ አትችልም። ሚሊሻ ጓዶቻችን ስለገደለ፣ ስለሚጠቁም ወዘተ በብስጭት ካየነው ሌላ ጉዳይ ነው። የሌላ ብሔር የመከላከያ አባላት መርሯቸው መሳሪያ ሸጠው እየጠፉ ሰው በሰው የምታውቀው፣ ሰፈሩ የሚደበደበው፣ ራሱም ደጋፊ ነህ ተብሎ ሲገረፍ የከረመው፣ ክብር የማይሰጡትን ሚሊሻ ጋር የሚኖረውን ነገር ቁጭ ብሎ ማጤን ያስፈልጋል። አራት ኪሎን የሚመለከት ሚሊሻ የሚባልን እንቅፋት ማለፍ ካልቻለ ለአገዛዙ ምቹ መሆኑ ነው። እርስ በእርስ እያታኮሰ፣ የማህበረሰብ ደም እያቃባ ጊዜ ይገዛል። ትግሉን አራት ኪሎ ድረስ ያደረገ ሌላ አዋጭ አማራጭ መፈለግ አለበት። ዝርዝር ግምገማ ያስፈልገዋል።

በገጠር ያስቸገረን ባላንጣ አንድ አድርጌው ቤቴም ይፈርሳታል ብሎ የሚወስን አለ። የግል ጠብ ሲሆን ነው። ይህኛው አላማ ግን ቤት የመስራት ነው። ስርዓት የመስራት ነው። ይህን ለማድረግ የተነሳ አካል አካሄዱን ማጤን አለበት። የአማራን ጥያቄ ለሚሊሻው አስረድተን፣ ጥያቄውን ካልተረዳም ከእኛ ጋር የሚሆንበትን መንገድ ካልቀየስን፣ ካልሆነም የከፋው ጠላቱ ሌላ መሆኑን ማሳየት ካልቻልን ትግሉ ትርምስ ውስጥ ይገባል። ሚሊሻው በርካታ ቁጥር ያለው ነው። ከፋኖ አባላት ጨምሮ ዘመዶች አሉት። ከአርሶ አደሩ በክፉም በበጎም ይቀርባል። እጅግ አደገኛው ደግሞ አንዳንዴ በሚሊሻውና መሳሪያ በያዘው አርሶ አደር መካከል ያለው ድንበርም ቀጭን መስመር ይሆናል። በዚህ በኩል አንዳንድ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች እየታዩ ነው። ባለፈው ጦርነት ሚሊሻ ተብሎ የዘመተ አርሶ አደር፣ አገዛዙ መሳሪያውን እንዳይቀማው ስብሰባ የሚሄድም ሆነ ሌላው እና ዋናው ሚሊሻ ጋር ያለው ልዩነትንና ድንበር የሚጠፉበት ሁኔታ ይኖራል። ከዚህ ሁሉ አንፃር ከትግሉ ዋጋና አስፈላጊነት አንፃር መረር ያለች ግምገማ፣ ጥናት፣ ምክክር ያስፈልጋል። ከእርስ በእርስ ጭቅጭቅና መፈራረጅ ይልቅ የውስጥ ኃይል አሰላለፍ ላይ ሰከን ብሎ፣ ከብስጭት ወጥቶ ማሰብ ያስፈልጋል። ሕዝብ ሲወደውና ሲያደንቀው የነበረው ኢሕአፓ በተወሰኑ አባላቱ፣ ከዕዝ ባፈነገጠ መንገድ፣ በብስጭት እርምጃዎች፣ በመሰላቸት፣ ፍረጃ ወዘተ ሕዝብ ጋር ተቃርኖ መግባቱን መተለያዩ ሰነዶች አንብበናል። ከቆየውም ከአሁኑ ተጨባጭ ሁኔታም መማር ያስፈልጋል።

መስዋዕትነት ብቻ ድል አያመጣም፣ ጀግንነት ብቻውን አሸናፊ አይደለም፣ ብልጠት፣ ብስለት፣ ጊዜውን የዋጀ ግምገማ፣ የውስጥ ኃይልን ማሰባሰብ፣ ጠላትን መቀነስ ለድል ያበቃል። ጀብዱ ብቻውን አላማን አያሳካም። ከብስጭት ያለፈ አካሄድ ግድ ይላል። ትግሉ የተከፈለበትን ዋጋ ያህል ብልጥነትና ብልሃት፣ ጥንቃቄም ያስፈልገዋል።
14.8K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 19:07:55
13.8K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ