Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የቴሌግራም ቻናል አርማ getachewshiferaw — Getachew shiferaw
የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.30K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2024-03-24 12:22:20 በቅርብ አመት ታዩታላችሁ!

ይህ ከአብይ አህመድ ጋር የሚተሻሸው ውሃብያ፣ ይህ ክርስትያኖችን በየቀኑ የሚያርደው ካዋርጃ በቅርብ አመት ወደ ምንነት እንደሚቀየር ታዩታላችሁ። በቱርክና በአረብ ኢሜሬትስ እየተደገፈ አሁን አደባባይ ላይ በስልት የመጣው ኃይል በቅርብ ምን አይነት ቅርፅ እንደሚይዝ ታዩታላችሁ።

በነገራችን ላይ ከ7 አመት በፊት በርካታ የአሸባሪው ISIS "ሴል" የተገኘው ኮልፌ ቀራኒዮ ነበር። አምነው የተከራከሩበት መዝገብ ልደታ ፍርድ ቤት አለ።

ዛሬ ሞስኮን ያስደነገጣት ሽብር ያኔ የትም ትሰሙታላችሁ።
22.4K views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-23 15:16:03
20.8K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-23 15:15:47 አርሶ አደሩን እንደጨፈጨፉ እየነገሩን ነው!

አርሶ አደሩን ቤት ለቤት እየገቡ፣ ባገኙበት ቦታም ሁሉ ይገድላሉ። ቤቱን ፈትሸው ህጋዊ መሳሪያውን ቀምተው ይሰበስባሉ። የፋኖ አስመስለው ዜና ይሰሩበታል። ፋኖ መትረየስ፣ ስናይፐርና ዲሽቃ በታጠቀበት ሁኔታ ምንሽር፣ አብራራው፣ ጓንዴና አልቤን መሳሪያን ፋኖን ገድለን የማረክነው እያሉ በይፋ የፈፀሙትን ወንጀል ዜና ያደርጋሉ።

ፋኖ ሲያንስ ክላሽ ከፍ ሲል ዲሽቃና ሌላም ታጥቋል። ይህ የቃታ ብረት አርሶ አደሩን እየገደሉ ቤቱን ፈትሸው የሰበሰቡት ነው። እየነገሩን ያለው አርሶ አደሩን መጨፍጨፋቸውን ነው!
19.4K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 21:48:18
16.5K views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 21:48:01 ጊዜያዊ አስተዳደሩ አረጋግጧል። ግን የታሰሩት 122 ብቻ አይደሉም!

ከትህነግ ጋር በነበረው ጦርነት ምክንያት ተይዘው ያልተለቀቁ ከአንድ ሺህ በላይ እስረኞች መቀሌ ጨለማ ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ሲገለፅ ቆይቷል። አማራ ክልል ላይ "ጥቁር ክላሽ" እያለ ሰበብ የሚፈልገው መቀሌ ላይ ወታደሮቹ በቀን አንድ ዳቦ እየተጣለላቸው በሚሰቃዩበት ሁኔታ ነው።

በትህነግ/ህወሓት ከታሰሩት ወታደሮች መካከል ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር 122ቱን ፈትቻለሁ ብሏል። እስር ላይ ያሉት ግን ከአንድ ሺህ በላይ ናቸው። አገዛዙ የሰላም ስምምነት ወዘተ ሲል በጀት የለቀቀለት በስሬ ያለ ነው የሚለው የእነ ጌታቸው ረዳ አስተዳደር ግን በልመና የተወሰኑትን ብቻ ነው የፈታለት። አማራ ክልል ላይ ምንም ሳይፈጠር ሰበብ ሲፈልግ "አስገድጀ ወደ ድርድር አስመጥቸዋለሁ" የሚለው ትህነግ ግን እስካሁን በልመና ሁሉንም አልፈታለትም። ያውም አገዛዙ ትግራይ ውስጥ ኃይል አለኝ እያለ።

እስካሁን ስንለው የቅየነውን ጊዜያዊ አስተዳደሩ በግልፅ ወጥቶ አረጋግጧል። 122 ፈትቸለታለሁ ብሏል። ሌሎቹን በመደራደሪያነት ይዞለታል።
16.3K views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-13 22:31:14

12.7K views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-11 18:00:00
18.1K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-11 17:59:51 አንድም የአማራ ተወካይ እንዳይገኝ ተደርጓል!

በአፍሪካ ህብረቱ የስምምነቱ መገምገሚያ ስብሰባ ላይ አንድም የአማራ ተወካይ እንዳይገኝ ተደርጓል። በስምምነቱ ወቅት ያልነበረው ደብረፅዮን እንኳ ሲገኝ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ሄደው የተደራደሩት የአማራ ተወካዮች እንዳይገኙ ተደርገዋል። ይህ የጀመረው ከድርድሩ ማግስቴ በተደረገው የኬንያው ስብሰባ ሲሆን ያ ስብሰባ የትህነግና ኦህዴድ የጓዳ ስምምነት በግልፅ የተፈፀመበት ነው።
18.4K views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 13:22:20
13.2K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 13:22:14 ወፍ ብቻ ሳይሆን አውሮፕላኑም መሳሪያ እያመላለሰበት ነው!

ይልማ መርዳሳ "ያለ እኛ ፈቃድ አየር ክልላችን ወፍ እንኳን አያልፍበትም" ብሎ ነበር። ወፍ ብቻ ሳይሆን መሳሪያ የጫነ አውሮፕላን መሳሪያ አራግፎ ተመልሷል። ሰሞኑን ከሱዳን በኩል ወደ ትግራይ በሌሊት አውሮፕላኖች ተመላልሰዋል። ሲጣራ ደግሞ እስካሁን ዘግይቶ "ትጥቅ ፍታ" እየተባለ ያለው ትህነግ ተጨማሪ ትጥቅ እያስገባ ነው።

ሰሞኑን አውሮፕላኖች በሌሊት ተመላልሰው ሽሬና አክሱም አርፈው መሳሪያ አራግፈው ተመልሰዋል። በአየር ክልላችን ወፍ አያልፍም የሚለው ጀኔራል ተራ ወሬ እንጅ እውነቱን አይደለም። አሊያም በእነሱ ትብብር ነው መሳሪያ የሚገባው ማለት ነው።

ነገ የሰላም ስምምነቱ ለመገምገም ስብሰባ ይደረጋል። ከስምምነቱ ማግስት ትጥቅ መፍታት የነበረበት ትህነግ ግን መሳሪያ በአውሮፕላን እየገባለት "የሰላም ስምምነቱ ይከበር" ማለቱ አይቀርም።
14.3K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ